<$ambachewmulat5.blogspot.com$> <$pub-7470502258870845$>

Thursday, February 11, 2021

፩•እውነትን በደጋፊ ብዛት እንዳትመዝናት ተጠንቀቅ ።
፪•ለእውነታ እንጂ ለይሉኝታ አትኑር ፤ ያንስልህ የምትኖርበት ሕዝብናባሕል
ከእውነት ጋር እስካልተጋጨ መጋፋት
የለብህም። ሠዎች የሚቀበሉህ
ባሕላቸውን ስታውቅና ስታከብርላቸው ነው 
፫•ልጅነት የለሰለሰ መሬት ፣ ወጣትነት የአዝመራ ዘመን ፣ ሽምግልና ደግሞ የአጨዳ ዘመን መሆኑን አስተውል ።
በሽምግልናህ የምታጭደው የወጣትነትህን አዝመራ ነውና ዛሬ ለምትዘራው ተጠንቀቅ ።
፬•የሰዎችን ያለማወቅ አግዝ ፤ ዕውቀትህ ባላወቁት ላይ እንድትኮራና እንድትፈርድ
አያድርግህ የአዋቂ ኩሩ ቁጥሩ ካላዋቂዎች ነውና ማወቅ ባለዕዳነት እንዳይሆን አላዋቂዎችን እርዳቸው 
፭•ሁሉን ወሬ ላውራ አትበል ፣ የደበቁህን ምስጢር አታውጣጣ ፣ የሰማኽውን ወሬና የተገለጠልህን ምስጢር ምን መፍትሔ ሰጠኸውና  ያየህውን ሥራ ሁሉ እሰራለሁ የሰማኸውን ትምህርት ሁሉ እማራለሁ አትበል ። ይህ የተሰወረው የቅንዓት ጠባይ ነውና ሁሉን ልያዝ ማለትም ዝንጉ አድረጎ እንዳያስቀርህ ሁሉም ውስጥ ልኑር አትበል ።
፮•ቆንጆዎች ቁንጅናቸው ሁሉን የሚተካ እየመሰላቸው ከዕውቀትና ከትሕትና ይርቃሉ ። ሁሉንም ሰው በመልካቸው የሚማርኩት ስለሚመስላቸው ኩሩና ተንኮለኞች ይሆናሉ ። አንተ ግን ቆንጆ ወዳጅን እንጂ ቆንጆ ቁመናን አትሻ ፤ቆንጆ ትዳርን እንጂ ቆንጆ ሴትን አትመኝ ፤የላይ ነገር ከንቱና ኀላፊ ነውናበሚፈርስ አካል ፣ ኑሮ በሚለውጠው መልክ አትደለል ።
፯•እወድሃለሁ ብለህ የምትናገረውን ቃል ውለታ አታድርገው ፣ መውደድህን የምትናገረው እንወድሃለን እንዲሉህ አይሁን ሠላም ያለው አፍቃሪ የራሱን
ፍቅር ያለ ምክንያት መፈፀም የሚችል ብቻ እንደሆነ እወቅ ። መወደድህን ለመስማት አትጠብቅ 
፰•የሰዎችን ያለማወቅ አግዝ ፤ ዕውቀትህ ባላወቁት ላይ እንድትኮራና እንድትፈርድ አያድርግህ የአዋቂ ኩሩ ቁጥሩ ካላዋቂዎች ነውና ማወቅ ባለዕዳነት እንዳይሆን አላዋቂዎችን እርዳቸው 
፱•ዛሬ የመዝራት ዘመንህ ነገ መከርህ ነውና በእምነት እውነትን ዝራ በምታውቀው ቦታ ላይ አገልጋይ
በማታውቀው መልካም ተግባር ላይ ደጀን ሁን ፤
፲•በቦታህ መምህር ያለቦታህ ተማሪ
ሁን ፤ ክብሩ እንዳይቀንስብህ ከዕቃ
ትምክህት ፣ ከዕውቀት ሙግት ራቅ!
ሲያለቅሱልህም ቃልህ ማርኳቸው
ሳይሆን የሞተ ዘመዳቸው ትዝ
ብሏቸው ሊሆን ይችላልና አለቀሱ ብለህ ንግግርህን ድንበር አታሳጣው

0 Comments:

Post a Comment

Subscribe to Post Comments [Atom]

<< Home