አማራ
አማራን <ከብአቱ!> የሚጎትቱ የዘመኑ
ፊልም
.
የታሪክ ምሁራን ለአማራ የአክሱም ሥልጣኔ
መውደቅ ዋነኛ ምክንያት አድርገው
የሚያቀርቡት የአክሱማውያን አማሮች የቀይ
ባህር የንግድ መስመር በ7ኛው ክ/ዘ
በሙስሊሞች መያዙን ነው፡፡ እኔ ደግሞ ዋናው
ምክንያቱ አማራ መመንኮሱና ወደ ባእቱ
መግባቱ ይመስለኛል፡፡ የቀይ ባህር የንግድ
መስመር እኮ ከሙስሊሞቹ በፊት በ6ኛው ክ/
ዘ አጋማሽ ላይ በፐርሺያኖች ተይዞ ነበር፡፡
በሌላ በኩል አፄ ካሌብ በ525 ዓ.ም ወደ
የመን ከመዝመቱ በፊት ፐርሺያኖችን ከቀይ
ባህር የንግድ መስመር ለማባረር ከቢዛንታይኑ
ንጉስ ጀስቲኒያን ጋር በ517 ዓ.ም ስምምነት
አድርጎ ነበር፡፡
ሆኖም ግን አፄ ካሌብ ለዚህ ስምምነት ተገዥ
ከመሆን ይልቅ የመንን ድል ካደረገ በኋላ
ሥልጣኑን ለልጁ ለአፄ ገ/መስቀል በማውረስ
እንደ አባቱ እንደ ዳግማዊ አፄ እለ አሚዳ
መመንኮስን መርጧል፡፡ የአፄ ገ/መስቀልም
ዋነኛ ትኩረት ገዳማትን ወደ ደቡብ ማስፋፋት
ሆነ፡፡ በስተመጨረሻም እሱም እንደ አባቱና
እንደ አያቱ የብሕትውና ህይወትን መረጠ፡፡
መነኮሰ ቢጫ ለበሰ፡፡ ይሄም የሚያሳየን 6ኛው
ክ/ዘ ላይ ሰማይ የነካ ስም የቀረፀው አማራ
አክሱም ላይ ስር ነቀል የሆነ አዲስ ዓይነት
የባህልና የእሴት ለውጥ መምጣቱን ነው፡፡
.
ይሄ አዲስ ዓይነት የባህልና የእሴት ለውጥ
አማራ ምድር ላይ በ9ኙ ቅዱሳን አማካኝነት
5ኛው ክ/ዘ መጨረሻ የገባ ሲሆን 6ኛው ክ/ዘ
ላይ ደግሞ ከአክሱም አማራ አልፎ በመላው
አማራ ተስፋፍቷል፡፡ 9ኙ ቅዱሳን ከመጡበት
ከዳግማዊ አፄ እለ አሚዳ እስከ አፄ እለ ገበዝ
ባሉት 130 ዓመታት ውስጥ ከነገሱት አምስት
ነገስታት አራቱ መንኩሰዋል፡፡ ይሄም
የምንኩስና ትምህርት በህብረተሰቡ ውስጥ
ምን ያህል ጉልበት እንደነበረው የሚያሳይ
ነው፡፡
.
ወደ ዋናው ነጥብ ስመጣ ይሄ የምንኩስና
ትምህርት የአማራን ነገስታት የትኩረት
አቅጣጫ ከዓለማዊ ገናናነት ወደ መንፈሳዊ
ጭምትነት በመቀየር አክሱማዊነት
የተመሰረተበትን “የሰውን ልጅ ምድራዊ
የበላይነት መጎናፀፍ” የሚለውን መርህ
ከውስጥ እየቦረቦረው ሄደ፡፡ ነገስታቱ
ከሥልጣን ገናናነት ይልቅ ግላዊ ነፍሳቸውን
ለማዳን ያደረጉት ሩጫ፣ ለህዝቡ ትልቅ
መልዕክት ነበረው፡፡ የምንኩስና ህይወት
ከእምነት አልፎ ለህብረተሰቡ ዓለምን
መመልከቻ መነፅር ለመሆን የበቃው ነገስታቱ
ከዓለማዊ ድሎት ይልቅ የምንኩስና ህይወትን
ሲመርጡ መታየታቸው ነው፡፡
በዚህም ምክንያት ብሕትውና አማራ ምድር
ላይ ከእምነት ወደ ባህልነት ሰፋ፤ ምንኩስና
የተመረጡ ጥቂቶች የሚኖሩበት እምነት
ከመሆን አልፎ ህዝቡ ገዳም መግባት
ሳያስፈልገው በየዕለቱ የሚኖረው ህይወት
ሆነ፡፡
.
ነገሬን ስቋጭ የአክሱም ዙፋን አልጋ ወራሹ
አማራ በሰራው ልክ ስለ ሰራው ሳይናገር
ዘመናት ማለፍ ጀመሩ፡፡ የአማራ ባህል፣ ታሪክ፣
የኑሮ ዘዴ በሚገባው ልክ ሳይነገር ቀረ፡፡ አሁን
ግን አዲሱ የአማራ ትውልድ ዘፈን፣ ፊልም፣
መፅሐፍ እያደረገ ወደ ቀደመ የበላይነቱ
መገስገስ አለበት፡፡ አለማዊ ኑሮን የሚንቅ
ሳይሆን አለምን እንደ አባቶቹ የሚመራ
የአክሱም ዙፋን አልጋ ወራሽ የአማራ ትውልድ
መነሳት ጀምሯል፡፡ እኛ የአባቶቻችን ልጆች
ነን!!! ልክ እንደ #እንሳሮ ፊልም!
0 Comments:
Post a Comment
Subscribe to Post Comments [Atom]
<< Home