የአዞ እንባ
#የዐዞ ዕንባ አንቢዎችን ሰይጣናዊ አስተሳሰብ አልቀበልም
#ኢትዮጵያ በአማራ ደም ተመስርተሽ አማራን የምትበይ የደም ምድር፡፡
ዐይጥ በበላ ዳዋን መምታት፡፡ ጌታውን ሲፈሩ ገበር ገበሩን ማንገላታቱ ይቁም፡፡
#ኢትዮጵያ በአማራ ደም ተመስርተሽ አማራን የምትበይ የደም ምድር፡፡
ኢትዮጵያ ሰው የማይፈጠርባት በምትኩ ግን አውሬ እየተባዛ እርስ በርሱ የሚተላለቅባት የሰቆቃ ምድር፡፡
ኢትዮጵያ ልጆቿ ወርቅን ቀብረው በላዩ ላይ በዘርና በጎሣ፣ በሃይማኖትና በድንበር የሚፋጁባት ጎስቋላ ምድር፡፡
ኢትዮጵያ እንግዴ ልጅ እንዲያድግ እውነተኛ ጽንስ እንዲጣል የተፈረደባት የመርገምት ምድር፡፡ ኢትዮጵያ አንዱ ከአንዱ የማይማርባት የፖለቲካ ደናቁርት ሁሌም ልጓሙን እየያዙ ሕዝብን ከአንድ የመከራ አዙሪት ወደሌላ የመከራ አዘቅት የሚከቱባት የእውነተኛው ዲያብሎስ ሠገነት፡፡
ያሳዝናል፤ያስለቅሳል
#ሺዎች አማራ በመሆናቸው ውድ ሕይወታቸውን ሰውተዋል፤አካለ ጎደሎ ሆነዋል፤ ለማኝ ሆነዋል፤ አብደው ራቁታቸውን ሄደዋል፤ ሁመራ ተግዘው ለበረሃ አውሬና ለረሱት የግብርና ሥራ ተጋልጠው ሳይሳካላቸው ከርታታና ስደተኛ ሆነው ቀርተዋል፡፡
አማራዎች ኢትዮጵያን አስከብሮ በኖሩ በጥይት የተደበደቡትን፣ በገመድ የታነቁትንና ለጅብ የተሰጡትን፣ ለእሥርና ሥውር ግድያ የተጋለጡትን፣ ቤቱ ይቁጠራቸው ታሪክ እንዲያስታውሳቸው ለባለታሪክ ልተወው
ኢትዮጵያ ከወትሮው በተለዬ በብዙ ነገር የመጀመሪያዋ ሀገር እየሆነች በታሪክ
እየተመዘገበችልን ነው፡፡ በግድ ሳቁና በግድ እየሞታቹሁ ተደመሩ የሚባልባት ይህም ካልሆነ በገጀራ አንገት እሚቀላባት ምናልባትም በዓለም የመጀመሪያዋ ሀገር መሆን አለባት –
ዘይገረም ሻሸመኔ ትብስ ኮፈኔ የተባለው ለካንስ እንደዚህ ያለ የተገላቢጦሽ ነገር ቢገጥም ኖሯል፡፡እነዚህ ደናቁርት ናቸው እንግዲህ ሀገርን የነበረውን የዮዲት ጉዲት አገዛዝ የደረሰበትን ስብራት እንደ ምንም ጠጋግነው በአዲስ መልክ ሊጋልቡን እየሻቱ ያሉት፡፡ ከዚህ ይሠውረን፡፡ ለነገሩ እኛ ከተኛን ለሣልሳይ ቀርቶ ለመቶኛስ ቢሆን እነሱ ምንአለባቸው ምክንያቱና ውጤቱ ምንም ይሁን ምን ከወያኔ ተሞክሮ ወሰደ ወደ #አባቶርቤ የተቀረየው ብልፅግና በሚመራው መጥፎ አገዛዝ ሳቢያ እስካሁን በሚሊዮኖች አማራዎች ቤት ልቅሶና ዋይታ የባህል ያህል ሊቆጠር በሚገባው ሁኔታ የዘወትር ገጠመኝ ነው
አማራዎች ታላቅ ጥበብ ና ጀብድ እንደነበረን የሚያሳዩ አሻራዎች በየስፍራው ቢኖሩም እነርሱ ሲጎዱ ማዬት ደግሞ ‹‹ወይራ ዶግ …›› እንዳያስብሉን ያሰጋል፡፡ ለምን ካሉ አዲስ ታሪክ መሥራትም ሆነ የነበረውን ማስቀጠል እየደከመ መጥቷልና ፡፡ አበው ሲመክሩ ‹‹ልጄ ብትችል ከፍ በል፤ ካበለዚያ ግን ከነበርክበት አትጉደል››
ይላሉ፡፡ አማሬው ሁሉ ቢችል ዘመን የሰጠውን አጋጣሚ በመጠቀም ከአባቶቹ ከፍ ያለ መሥራት አለበት ካልቻለ ግን ከአባቶቹ ክብር ሳይጎድል
መቀጠል ግዴታው ቢሆን መልካም ነው፡ የጎደለ ቀን በታሪክና በአባቶቹ አጽም ይወቀሳል፤ ቢጎድል ታላላቅ አዞዎች እያሳደገች የመጣችው እናቱ ኢትዮጵያ ታዝንበታለች፡፡
ጊዜ ዛሬ ብቻ አይደለም። ትናንትም ሆነ ነገ በጊዜ ባቡር ዉስጥ ነዉ ያሉት። ዛሬ ላይ ሆኖ ጊዜዉ የእኛ ነዉ በሚል ዕብሪት የሚፈጸም ወንጀል
ነገ ሌላ ገጽታ እንደሚኖረዉ አያጠራጥርም።
ዛሬ በቄሮ ስም የሚፈጸመዉ የጅምላ ግድያ፣ ሰዉን ከቀየዉ ማፈናቀል፣መግደል፣ የንጹሃን ንብረት ማዉደም፣ዝርፊያ… ወዘተ ነገ ላይ ሲደረስ እንደዛሬዉ የሚያስፎክር፣ የሚያኩራራና ደረትን ገልብጦ የሚያስኬድ ተግባር ሆኖ አይዘልቅም። ዛሬ “ቄሮ” ነኝ እያለ የሚኩራራ ሰዉ ነገ በቄሮነቱ አፍሮ ራሱንለመደበቅ ሲሯሯጥ ቢገኝ አይገርምም ትናንት በጊዜአቸዉ አይነኬ የነበሩት ግዙፎቹ የደርግ አባላት ምን እንደደረሰባቸዉ አይተናል። በቅርቡም ወያኔ ላይ የደረሰዉን አይተናል።
ብዙዎቻችን አንድ ጉዳይ ለመጨረስ በቢሮክራሲ ዉጣ ዉረድ ስንላጋ ባለጊዜዎቹ የ“ጊዜዉን ቋንቋ” በመናገራቸዉ ብቻ ያልጠየቁትንም ጭምር
ሲፈጸምላቸዉ ስንታዘብ ኖረናል።ትናንትና ሲኩራሩበትና የተዘጋን ኬላ ያስከፍት የነበረ “ቋንቋ” ዛሬ ግን በአደባባይ ተናግረዉ ማንነታቸዉ
እንዳይታወቅ ሲዉተረተሩ ቢታዩ አያስደንቅም። ምክንያቱም የጊዜ ጉዳይ ነዉ። ትናንት ሌላ ዛሬ ሌላ …
በዐማራው ሕዝብ ላይ የሚካሄደው ግፍና በደል ዛሬም አላቆመም ።
(#Prochaka Roman)the Abyssinia Powder Barrel, 1927 በጻፈው መጽሃፉ ላይ
እንዳስቀመጠው የዐማራው ሕዝብ ራሱን ከፈረንጆች በታች አድርጎ የማይቀበል፤ በነጻነቱና በሉዐላዊነቱ የማይደራደር መሆኑን አስምሮበታል
ሆኖም፤ ፋሺስቶችና ናዚዝቶች፤ አስካሪዎችና ከሃዲዎች ይህን ሕዝብ እንደ ጠላት እንዲኮንኑትና እንዲጠፋ፤ ባይጠፋም እንዲሸማቀቅ አድርገው ያልተቆጠበ ፕሮፓጋንዳና ጦርነት አካሂደውበታል
የኢትዮጵያ የውጭና የውስጥ ጠላቶች የዐማራውን ሕዝብ የሚጠሉበትና እንዲጠፋ የሚመኙት ለምንድን ነው?
የዐማራው ሕዝብ የነጻነት፤የአትንኩኝ ባይነት፤ የነጭ ሆነ የቢጫ ሕዝብ የጥቁር ሕዝብ የበላይ ዓይደለም፤ ሆኖም አያውቅም፤ እኔ ለቅኝ ገዢዎች አልንበረከክም ባይነት
በነጮች በኩል ተቀባይነት አግኝቶ አያውቅም። ይህን አመለካከት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የናደው በአጼ ምኒልክ የተመራው የአድዋ ድል ነው።
የአድዋ ድል ግን በተናጠል መታየት የለበትም። ኢትዮጵያ የራሷ ፊደል፤የራሷ የቀን መቁጠሪያ፤ የራሷ የመንግሥት ስርዓት ያላት አገር መሆኑና ጭንቀት እንደፈጠረ ማጤን ያስፈልጋል።
ይህ ታላቅነት ያልተዋጠለት ሙሶሊኒና ተባባሪ የነበሩት የአገር ውስጥ ከሃዲዎችና አስካሪዎች ኢትዮጵያ እንደ ገና እንድትወረር አድርገዋል። ይህ የመጨረሽ የውጭ ወረራ ግን አገሪቱ የጣሊያን አካል እንድትሆን አላደረጋትም። የሃበሻ ጀብዱ የተባለው አስደናቂ መጽሃፍ እንደሚያሳየው
ለአምስት ዓመታት የኢትዮጵያ ጀግኖች በዱር በገደሉ ጣሊያኖችን ተዋግተዋል፤ ጣሊያንን አሸንፈዋል። ሆኖም፤ አሁንም ቢሆን ፋሽስቶችና ናዚዝቶች ተክለውት የሄዱት የዘውግ ጥላቻና የከፈፍለህ ግዛው ስልትና ስሌት መፍትሄ አላገኘም። ኢትዮጵያ ታላቅ አገር እንዳትሆን የሚፈልጉ የውጭና የውስጥ ኃይሎች ዋና መሳሪያ አድርገው የሚጠቀሙበት አማራውንና ኦርቶዶክስ እምነትን ማጥፋት ነው።
የዐዞ ዕንባ አንቢዎችን ሰይጣናዊ አስተሳሰብ አልቀበልም ምክንያትም በጎን በለው ፣በጎን እየየ አይሰራም
0 Comments:
Post a Comment
Subscribe to Post Comments [Atom]
<< Home