<$ambachewmulat5.blogspot.com$> <$pub-7470502258870845$>

Sunday, December 13, 2020

አባባሎች

 አባባሎች

የሀምሌ ብራ የባልቴት ወብራ

የሀምሌን ውሀ ጥም የህዳርን ራብ የሚያውቅ

ያውቀዋል

የሀምሌ ጭቃ ቅቤ ለጋ

የሀር ገመድ የበቅሎ ክበድ

የሀብታም ልጅ ሲጫወት የድሀ ልጅ ይሞታል

የሀብታም ልጅ ወደ ቦሌ የድሀ ልጅ ወደ ባሌ

የሀጢአት ክፉ ጉቦ የበሽታ ክፉ ተስቦ

የሀጥኡ ዳፋ ጻድቁን ያዳፋ

የሁለት ሴቶች ባል ይሞታል ይበላል ሲባል

የሁለት አገር ስደተኛ

የሁለት እዳ ከፋይ

የኋላ የኋላ አይቀርም ዱላ

የህልም ሩጫ የጨለማ ፍጥጫ

የሆነ አይመለስ እሳት አይጎረስ

የሆድ ማበድ ያስቃል በግድ

የሆድ ምቀኛ አፍ ነው

የሆድ ምቀኛው አፍ ነው

የሆድ ብልሀት የጋን መብራት

የሆድ ነገር ሆድ ይቆርጣል

የለመነ መነመነ

የለመነ ያገኛል የነገደ ያተርፋል

የለመኑትን የማይረሳ የነገሩትን የማይረሳ

የለመደ ለማኝ ቁርንጮዬን ቀማኝ

የለመደ ልማድ ያሰርቃል ከማእድ

የለመደ ልማድ ያሰድዳል ከማእድ

የለመደ መደመደ

የለመደ እጅ ጆሮ ግንድ ያስመታል

የለመደ ፈረሰኛ ዛብ አይጨብጥ እርካብ አይረግጥ

የለመደች ጦጣ ሁልጊዜ ሽምጠጣ

የለማኝ ስልቻ ሲንከባለል ከለማኝ እጅ ይወድቃል

የለማኝ ቅንጡ ይላል በወጥ አምጡ

የለም ቀሪ ካለ ፈጣሪ

የለበሰ የማንንም ጎረሰ

የለበሱት ያልቃል የሰጡት ያጸድቃል

የለጋስ ምስክሩ መስጠቱ

የላሜ ልጅ ያውራዬ ውላጅ

የላም መንጃ የሰማ መከንጃ የማር መቅጃ

የላም ወተቱን የጌታ ከብቱን

የላከ እንደ አፉ ያከከ እንደ እጁ አይሆንለትም

የላይ ለምጡን የውስጥ እብጡን ባለቤቱ ያውቀዋል

የላይ አልጋ የውስጥ ቀጋ

የላይኛው ከንፈር ለክርክር የታችኛው ከንፈር ለምስክር

የላጭ ልጅ ጸጉሩ ድሬድ ሆነ

የላጭን ልጅ ቅማል በላት

የላጭን ልጅ ቅማል በላው ያናጢን ልጅ ጅብ በላው

የሌለው ልብም የለው

የሌለው ልብ የለው ወዳጅ የለው

የሌለው ሚስት የለው ወዳጅ የለው

የሌሊት ግስገሳ የቀን ዘለሳ

የሌላት እራት ደግሞ ምሳ አማራት

የሌባ መኝታው አመድ መታሰሪያው ገመድ

የሌባ ምኝታው ካመድ መታሰሪያው ገመድ

የሌባ ሞኝ ከጎተራ ስር ይገኝ

የሌባ አይነደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ

የሌባ እጁን የፍየል ልጁን

የሌባ ዋሻ የቀማኛ መሸሻ

የሌባን ጠበቃ አደባልቀህ ውቃ

የሌባን ጠበቃ ደርበህ ውቃ

የልመና በሬ ትክክል አይሄድም

የልመና እንጀራ ምንጊዜም ከልመና አያወጣም

የልቡ ሳይደርስ እድሜ ይደርስ

የልቡን ሲነግሩት የኮረኮሩትን ያህል ይስቃል

የልቡን አድራጊ አይናደድም

የልብህን ቢያናግሩህ አለ እዳ ቢለቁህ

የልብህን ቢያናግሩህ አለ እዳ ቢሰዱህ

የልብስ ቀላል ባለቤቱን ያቀላል

የልጅ ልጅ እህል ፈጅ ኋላም ጅብ ያስፈጅ

የልጅ ልጅ ጅብ አስፈጅ

የልጅ መልከ ጥፉ በስም ይደግፉ

የልጅ ሞት የእግር እሳት

የልጅ ስጋ በናቷ ቅቤ

የልጅ ቀላቢ የአህያ ጋላቢ

የልጅ ብልጥ እየቀደመ ይውጥ

የልጅ ብልጥ የፊት የፊቱን

የልጅ ብልጥ የሰጡትን

የልጅ እናት አባይ ናት

የልጅ ተሟጋች በፊት ሰማይ ያያል ኋላ መሬት

የልጅ ተሟጋች ጠዋት ሰማይ ማታ ምድር ምድር ያይ

የልጅ ነገር ሁለት ፍሬ አንዱ ብስል አንዱ ጥሬ

የልጅ ነገር ጥሬ በገል

የልጅ ክፉ ዲቃላ የቤት ክፉ ሰቃላ የልብስ ክፉ ነጠላ

የልጅ ክፋቱ አለመከማቸቱ

የልጅ ጥፉ በስም ይደግፉ

የልጅ ፍቅር የሴት ከንፈር እናትን አያስቀብር

የልጅቷን ስጋ በእናቷ ቅቤ

የልጅ ፍሬ አንዱ ብስል አንዱ ጥሬ

የሎሌ አልቃሽ የሴት ቀዳሽ

የሎሌ አልቃሽ የሴት ቀዳሽ የቄስ አውደሽዳሽ

የመልኳን ሲሏት የጠባዩዋን

የመሬት ሴሰኛ ከመንገድ ዳር ይተኛ

የመሬት እርጥብ እሸቱን ደረቅ ምርቱን

የመስከረም ውስጡ በጋ ያረመኔ ልቡ ቀጋ

የመቀናጆ በሬ ሲመሽ ወደ ቤቱ ይስባል

የመበደሪያ አፍ መክፈያ አይሆንም

የመተሩበት እጅ ይወዛል የተማከሩት ዳኛ ያግዛል

የመታሰር ምልክቱ መጋዝ የመዳኘት ምልክቱ መያዝ

የመነነ ከዱር የሞተ ከመቃብር

የመነነ ከዱር የሞተ ከመቃብር አይወጣም

የመነኩሴ ሎሌ የክረምት አሞሌ

የመንማና የለው ገናና

የመንታ እናት ተንጋላ ትሞት

የመንገድ ዳር እሸት ባል የሌላት ሴት

የመንገድ ዳር እሸት ባል የሌላት ሴት ለማንም ናት

የመንዝ ልጅ እራያ ሂዶ ብልቱን አያወዛውዝም

የመከሩበት ሞተ የወርወሩበት ተሳተ

የመከራ ልጅ ሁል ጊዜ መከራ መስሎ ይታያል

የመከራ ሌሊት አያልቅም

የመከራ ሎሌ መከራ መስሎ ይታያል

የመከራ ውዝፍ ያለበት ነጋዴ ከሚወረር አገር ይደርሳል

የመከራን ጉድጓድ ሚዳቋ አትዘለውም

የመኮንን ልጅ በከተማ የድሀ ልጅ በውድማ

የመኮንን ልጅ አዘን ቢነግሩት አደን

የመዝሙር መጀመሪያ ሀሌታ የዘፈን መጀመሪያ

እስክስታ

የመጠጡት ቅልጥም ከብርንዶ ይጥም

የመጣ ሳይመጣ የውሃ ቦይ ጥረግ

የመጣው ቢመጣ ወይ ፍንክች ያባ ቢላዋ ልጅ

የመጣ ቢመጣ ከቤቴም አልወጣ

የመጥረቢያ ልጅ መዝለፊያ

የመጥረቢያ ልጅ ጥልቆ አይደል የሚባለው

የሙሽራ እድሜ ቢያጥር የሰርጉ ድግስ ሆነ ለተዝካር

የሙት ቀናተኛ ሚስቴን አደራ ይላል

የሙት አልቃሹ የቁም ወራሹ

የሙት አልቃሹ የቁም ወራሽ

የሙት የለውም መብት

የሚሆን ቢሆን ዝሆን ይበላ ቢሆን

የሚሉሽን በሰማሽ ገበያም ሳልወጣሽ

የሚሉሽን በሰማሽ ገበያም ባልወጣሽ

የሚመክተው ጋሻ የሚጠጋበት ዋሻ

የሚመክተው ጋሻ የሚጠጋበት ዋሻ የለውም

የሚመጣውን እንድታውቅ ያለፈውን እወቅ

የሚሞት ልጅ አንገቱ ረጅም ነው

የሚሮጡበት ሜዳ የሚወጡበት ቀዳዳ

የሚሰራ ምንም አያወራ

የሚሰርቀውን ያጣ ሌባ ሰላማዊ መስሎ ይገባ

የሚሰርቀውን ያጣ ሌባ ሰላማዊ መስሎ ይገባል

የሚሰርቅ ሰው አደራ ቢያስቀምጡት እጅ ይነሳል

የሚክድ ሰው አደራ ቢያስቀምጡት እጅ ይነሳል

የሚሰጥም እሾህ ይጨብጣል

የሚሰጥም ገለባ ይጨብጣል

የሚስት መናኝ የእናት አገር ለማኝ

የሚስት አንባሻ የጎረቤት ውሻ የደጅ እርሻ

የሚስት አሳቢ የጥንድ በሬ ሳቢ ይስጥህ

የሚስት ወይዘሮ እርሻው ጋራ ዞሮ

የሚስት ዘመድ የማር አንገት

የሚስት ዘመድ የማር እንጎቻ

የሚሸሹበት አምባ ሲሸሽ ተገኘ

የሚበላው ካጣ ይበላለት ያጣ

የሚበላው ካጣ ይበላበት ያጣ

የሚበጀውን ባለቤት ያውቃል

የሚከርመውም የማይከርመውም ባንድነት ዝናብ

ይለምናል

የሚከርመውም የማይከርመውም አንድነት ዝናብ

ይለምናል

የሚካኤል ስለት ለገብርኤል ምኑ ነው

የሚካኤል እለት ለገብርኤል ምኑ ነው

የሚወዱትን ሲያጡ የጠሉትን ይቀላውጡ

የሚወዱትን አቅፎ የሚጠሉትን ነቅፎ

የሚወዱትን እቅፍ የሚጠሉትን ንቅፍ

የሚወጋ ጦር ከእጅ ሲወጣ ያስታውቃል

የሚውል ሆድ ማለዳ ያረግዳል

የሚውል ሆድ ማለዳ ይርበዋል

የሚወጡበት ገደል የሚንጠለጠሉበት ቅጠል

የሚጠጉበት ገደል የሚንጠለጠሉበት ቅጠል

የሚዛንን አባይ ለእሳት የዳኛን አባይ ለሰንሰለት

የሚያልቅ እህል ከማያልቅ ዘመድ ያጣላል

የሚያልፍ ቀን የማያልፈውን ስም ያወርሳል

የሚያልፍ ቀን የማያልፍ ስም ያወርሳል

የሚያልፍ ነገር የማያልፍ ስም ይሰጣል

የሚያልፍ ውሀ አደረገኝ ድሀ

የሚያልፍ ውሀ አደረገኝ ድሀ አለች ልጅዋን ጎርፍ

የወሰደባት

የሚያልፍ ዝናም አይምታህ የሚሞት ሽማግሌ

አይርገምህ

የሚያልፍ ዝናም አይምታህ የሚያድግ ልጅ አይጥላህ

የሚያማ ጠበኛ ዘወር ይበል ከኛ

የሚያስፈራውን ለሚነግርህ የሚያስቀዝነውን ንገረው

የሚያስፈሳውን ለሚነግርህ የሚያስቀዝነውን ንገረው

የሚያብረቀርቅ ሁሉ ወርቅ አይደለም

የሚያድግ ልጅ በእናቱ እጅ

የሚያድግ ልጅ አትበድል የሚሞት ሽማግሌ አታቃልል

የሚያድግ ልጅ አትበድል የሚሞት ሽማግሌ አታቅል

የሚያድግ ልጅ አይጥላህ የሚሞት ሽማግሌ

አይርገምህ

የሚያድግ ልጅ አይጥላህ የሚያልፍ ዝናብ አይምታህ

የሚያድግ ዛፍ በቁጥቋጦው ያስታውቃል

የሚያድግ ዛፍ ከቁጥቋጦው ያስታውቃል

የሚያጠግብ ቂጣ ከምጣዱ የሚወጣ ጥጃ ከገመዱ

የሚያጠግብ ቂጣ ከምጣዱ የሚወጣ ጥጃ ከገመዱ

ያስታውቃል

የሚያጠግብ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል

የሚያፈስ ቤት ጨቅጫቃ ሚስት

የሚዳቋ ብዛት ለነአቶ ውሻ ሰርግ ነው

የሚዳቋ ብዛት ለውሻ ሰርግ ነው

የሚዳቋ ግርግርታ ለውሻ ሰርጉ ነው

የሚዳቋ ግርግርታ ለውሻ ሰርግ ነው

የሚጣፍጥ ምግብ ምንድን ነው ቢሉት ሲርብ የበሉት

የሚጣፍጥ ምግብ ሲርብ የበሉት ነው

የሚጣፍጥ ምግብ ምንድን ነው ቢሉት ሲርብ የበሉት

ነው

የሚፈልግ ያገኛል የሚተኛ ያልማል

የሚያፈስ ቤት ጨቅጫቃ ሚስት

የሚፈርስ ከተማ ነጋሪት ቢመታ አይሰማ

የሚፈታ ከተማ አዋጅ ቢነግሩበት አይሰማ

የማህበር አሽከር በልቶም አይጠገን ታሞም አይድን

የማሚቴን እጅ ያላየ በእሳት ይጫወታል

የማሽላ ዘር ከነአገዳው ቸር

የማታ ማታ እውነት ይረታ

የማታ ማታ ጭምት ይረታ

የማታ ምግብ ለእንግዳ የጠዋት ምግብ ለአገዳ

የጠዋት መጠጥ ለእዳ

የማታ ሩጫ እንቅፋት ትርፉ

የማታርፍ ጣት አር ጠንቁላ ወጣች

የማታድግ ውርንጫ እናትዋን ትመራለች

የማታድግ ጥጃ እናቷ ን ትመራለች

የማታ አፍ ከጋን ይሰፋል

የማታድግ ፍየል አምስት ትወልዳለች ልጆቹዋም

ያልቃሉ እሷም ትሞታለች

የማታፍር ድመት ስሜ ገብረማሪያም ነው ትላለች

የማትሄድ መበለት ዞራ ዞራ ትሰናበት

የማትረባ ፍየል ዘጠኝ ትወልዳለች ዘጠኙም ያልቁና

እሷም ትሞታለች

የማትሰማው ስድብ ከቀረርቶ ይቆጠራል

የማነው እህል ያሰኝሃል ክምር የማነው ቤት ያሰኝሃል

አጥር

የማን እርሻ ብለህ እረስ የማን ሚስት ብለህ ውረስ

የማን ገበሬ ሹሩባ ይሰራል

የማን ዘር ጎመን ዘር

የማያልፍለት ዘበኛ ከዋርካ ስር አይጠፋም

የማያልፍ ነገር የለም ምሽትም በማለዳ ይተካል

የማያመሽ ባል ቅንድብ ይስማል

የማያስተኛ ነግረውህ ተኝተው ያድራሉ

የማያስተኛ ነግረውት ሳይተኛ አደረ

የማያበላ ቢገላምጥ አያስደነግጥ

የማያበድር ደመና የማይመልስ ቀማኛ

የማያበድር ገዳይ የማይመልስ አባይ

የማያዋጣ ማህበር በጠጅ ይጀመራል

የማያዋጣ ባል ቅንድብ ይስማል

የማያውቁት ስድብ ከዘፈን ይቆጠራል

የማያውቁት አገር አይናፍቅም

የማያውቁትን መስራት ከጥቅሙ ጉዳቱ ይብስ

የማያውቁት ምን ያውቅ

የማያዛልቅ ጸሎት ለቅስፈት

የማያደርግ እንትን ከቤተክርስቲያን ይቆማል

የማያድግ ልጅ ባራስ ቤቱ ዳንኪራ ይመታል

የማያድግ ልጅ ታዝሎ ያፏጫል

የማያድግ ልጅ ቅዘን ይበዛዋል የማያጠግብ እንጀራ

ከምጣዱ ያስታውቃል

የማያድግ ጥጃ ከበሬ ፊት ይነጫል

የማያግዙ በፈር ያግዛሉ በከንፈር

የማያጠግብ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል

የማያፍር እንግዳ ባለቤቱን ይጋብዛል

የማይሆን ነገር የተገላቢጦሽ ያችን ላንቺ ማናለሽ

የማይመለስ ማር ሹመኛ ይበደረዋል

የማይመስል ነገር ለሚስትህ አትንገር

የማይመስል ነገር ለሴት አትንገር

የማይመቱት ልጅ ሲቆጡት ያለቅሳል

የማይመቱት ልጅ ቢቆጡት ያለቅሳል

የማይሰማ ሰው ልቤን አፈረሰው

የማይሰማ ጆሮ ከጎረቤት ያጣላል

የማይሰራ አይብላ የማይረዳ አይጥላ

የማይስማሙ ዝንቦች ጥምብ ይልሳሉ የሚስማሙ

ንቦች ማር ይጎርሳሉ

የማይቀርልህን እንግዳ አጥበቀህ ሳመው

የማይቀና ባይወለድ የማያስብ ባይነግድ

የማይቀና ባይወለድ የማያስብ ባይነግድ ይሻላል

የማይቀና ባይወልድ የማያስብ ባይነግድ

የማይቀና ባይወልድ የማያስብ ባይነግድ ይሻላል

የማይበሉት እህል ከአፈር እኩል ነው

የማይበላ የለም የማይጠግብ ባሰ

የማይተማመኑ ባልንጀሮች በየወንዙ ይማማላሉ

የማይተማመኑ ባልንጀሮች እየወንዙ ይማማላሉ

የማይተማመን ባልንጀራ በየወንዙ ይማማላል

የማይተች አይፍረድ የማያተርፍ አይነግድ

የማይቻል ጠላት ስለ ወዳጅ ይቆጠራል

የማይቻል ጠላት ከወዳጅ ይቆጠራል

የማይችሉት ድንጋይ ሲያወጡት ደረት ሲያወርዱት

ጉልበት ይመታል

የማይከፍል ባለእዳ የሰጡትን ይቀበላል

የማይነጋ መስሏት እቋቱ ላይ አራች

የማይዘልቅ ማህበር በጠጅ ይጀመራል

የማይዘልቅ ማህበር አሜሪካ ይጀመራል

የማይዘልቅ ባል ቅንድብ ይስማል

የማይዘልቅ ጸሎት ለቅስፈት

የማይደርሱበትን አያኩም

የማይድን በሽተኛ በጥር እሸት አምጡ ይላል

የማይድን በሽተኛ በበጋ እሸት አምጡልኝ ይላል

የማይድን በሽተኛ የማይመለስ ሀጢአተኛ

የማይድን ባህታዊ ወተት አምጡ የማይድን ፉቅራ

ጠላ ስጡ

የማይገባ ሱሪ የማይበቅል ዘሪ

የማይጠረጥር ቤቱን አያጥር

የማይጣሉ መላእክት የማይታረቁ አጋንንት

የማይጽፍ ደብተራ ክንፍ የሌለው አሞራ

የማይፈርስ ምሽግ የለም

የማይፈወስ ድዉይ የማይመለስ ጊጉይ

የሜዳ ንስንሱን የቤት ጉስጉሱን

የሜዳ ንስንሱን የቤት ጉዝጓዙን

የምህረት ጎደሎ የባሪያ ወይዘሮ

የምላስ ወለምታ ሪፈር የለውም

የምላስ ወለምታ በቅቤ አይታሽም

የምላስ ጦር ቢታከም አይድንም

የምመክተው ጋሻ የምጠጋበት ዋሻ

የምሮጥበት ሜዳ የምወጣበት ቀዳዳ የለም

የምስራች በቃሏ መላች

የምስራች በቃሏ መጣች

የምበላው ሳጣ ልጄ ጥርስ አወጣ

የምበላው ሳጣ ማእቀብ ሊጣል ነው

የምታሸንፈውን ምታ ቢሉት ወደ ሚስቱ ሮጠ

የምትለብሰው የላት ሻንጣ ቆለፈች

የምትለብሰው የላት የምትከናነበው አማራት

የምትመክተው ጋሻ የምትሰወርበት ዋሻ

የምትሮጥበት ሜዳ የምትገባበት ቀዳዳ

የምትበላው እህል ከማታየው መሬት ይበቅላል

የምትታጠቀው የሌላት የምትከናነበው አማራት

የምትነቃነቅ ግንድና የምትስቅ ሴት ልብ ሩቅ ነው

የምትኮነን ነፍስ ጎረቤት ያውቃታል

የምትጠላው ሰው ፈሱ እሆዱ ውስጥ ሳለ ይሸታል

የምትጠላውን የምትወደውን ሰጥተህ ሸኘው

የምትጠባ ጥጃ አትጮህም

የምትጠባ ጥጃ አትጮህም የማይደርሱበትን አያኩም

የምኞት ፈረስ ልጓም አይገታውም

የምናውቃትን ክምር በድባብ ሸፈኑዋት

የምድሩን በአፍ የሰማዩን በመጣፍ

የምጣዱ ሳለ የእንቅቡ ተንጣጣ

የምጣዱ እያለ የእንቅቡ ተንጣጣ

የምጣዱ እያለ የእንቅቡ ተንጫጫ

የምጥ መድሀኒቱ አንድ እግር ማስቀደም ነው

የሞላለት ድመት በሞዝቮልድ ይተኛል

የሞላለት ድመት ሳንባ ያማርጣል

የሞተ ልጅ አንገቱ ረጅም ነው

የሞተ ቢሞት ያለን እንጫወት

የሞተ አይከሰስ የፈስስ አይታፈስ

የሞተው ባልሽ የገደለው ውሽማሽ

የሞተው ባልሽ ገዳዩ ወንድምሽ (ሀዘንሽ ቅጥ አጣ

ከቤትሽ አልወጣ)

የሞተ ያልነበረ ይመስላል ያለ የማይሞት ይመስላል

የሞተን አትርሳ የወደቀን አንሳ

የሞተውን አያ ይለዋል

የሞት በደለኛ አያይዞ በዳኛ

የሞኝ ለቅሶ መልሶ መልሶ

የሞኝ ልቅሶ መልሶ መልሶ

የሞኝ ልጅ ባባቱ ምን ይጫወታል አሉ

የሞኝ ሚስት በምልክት

የሞኝ ምስጋና የግንቦት ደመና

የሞኝ ቄስ ጸሎት ዘወትር አቡነ ዘበሰማያት

የሞኝ በትር ሆድ ይቀትር

የሞኝ እጁን ሁለት ጊዜ እባብ ነከሰው አንድ ጊዜ

ሳያይ ሁለተኛው ሲያሳይ

የሞኝ ዘመድ ያፍራል

የሞኝ ዘፈን ሁልጊዜ አበባዬ

የሞኝን ጠላ በለው በአንኮላ

የሞኝ ጀርባ ሲመታ ለአዋቂ ይስማማል

የሞኝን ጥርስ ብርድ ፈጀው

የሞኝ ገበሬ እርሻ በሰኔ

የረጋ ወተት ምርጫ ይደገምለታል

የረጋ ወተት ቅቤ ይወጣዋል

የራሷ ሲያርባት የሰው ታማስላለች

የራስህን አትበላ ገንዘብ የለህ የሰው አትበላ ዐመል

የለህ

የራሷ አሮባት የሰው ታማስላለች

የራስዋ እያረረባት የስው ታማስላለች

የሰማ ያውራ ያየ ይናገር

የሰካራም ግጥም ሁልጊዜ ቅዳ ቅዳ

የሰው አመሉ ዳውላ ሙሉ መቼ ያስታውቃል አብረው

ካልዋሉ

የሰው አገሩ ምግባሩ የከብት አገሩ ሳሩ

የሰው አገር ዝናብና የእንጀራ አባት አይምታህ

የሰው እንጂ የቃል ውሸት የለም

የሰው ወርቅ አያደምቅ

የሰው ፈላጊ የራሱን ያጣል

የሴት ምራቋ ወፍራም ነው

የሴትን ብልሀት የጉንዳንን ጉልበት ይስጥህ

የሴት አገር ባልዋ

የሴት አጭር ወይዘሮ የወንድ አጭር አውራ ዶሮ

የሴት ጠጭና የአህያ ፈንጪ አያድርስ ነው

የሴት ልባም ያህያ ቀንዳም

የሴት ልቧ እንጂ ሆዷ አይመርጥም

የሴት መልኳ ምንድር ነው እጅዋን ታጥባ እንኩ ስትል

ነው

የሴት መጠጥ ደፋር የወንድ አይን አፋር

የሴት ምክር ማሰሪያው አሽከቴ

የሴት ምክር የሾህ አጥር

የሴት ሞቷ በማጀቷ

የሴት ረዥም የማቅ ውዥምዥም እንብዛም

አያስጎመጅም

የሴት ስካር ያጭር ሰው ኩራት አይታይም

የሴት ብቻዋን ሂያጅ የቄስ አርፋጅ ሁለቱም ነገር

ወዳጅ

የሴት አመዳም የአህያ ሆዳም

የሴት አመዳም የአሮጌ ሆዳም

የሴት አገሩዋ ባሏ

የሴት አገሩዋ ባሏ ማደሪያዋ አመሏ

የሴት እንግዳ የመርፌ ጎዳ

የሴት ቀበጥ የበቅሎ መድን ለመሆን ገበያ

ትወጣለች

የሴት ትንሽ የለውም

የሴት ጉልበት ምላሱዋ

የሴት ጠጪ የግመል ፈንጪ

የሴት ዘበናይ የፊትዋን እንጂ የኋላዋን አታይ

የሽማግሌ ፍቅር እና የክረምት አበባ አንድ ነው

የሽሮ ድንፋታ እንጀራው እስኪመጣ ነው

የሽሮ ድንፋታ እስኪቀርብ ድረስ

የቀረ ይቀራል እንጂ ቀርቅር ብዬ አልጣራም

የቀበሮ ባህታዊ የለም

የቀበጠች አይጥ በድመት ጭራ ዘፈን ትዘፍናለች

የቀበጠች አይጥ የድመትን አፍንጫ ታሸታለች

የቀበጠ እንትን ቅቤ ቀቡኝ ይላል

የቀበጡ እለት ሞት አይገኝም

የቀን ጠማማን ሚዳቆ አትዘለውም

የቀጣፊ እንባ ባቄላ ያክላል

የቂጥ አጋሚ ፈስ ነው ወሮታው

የቃመ ተጠቀመ ያልቃመ ተለቀመ

የቃርያ እልክ አወፈረኝ

የቄስ ጠበቃ ዳዊት ይጠቅሳል

የቅርብ ጠበል የልጥ መንከሪያ ይሆናል

የቅድሙ በዛ ያሁኑ ተንዛዛ

የቆጡን አወርድ ብላ መሰላል አመጣች

የቆጡን አወርድ ብላ ቤቷን ከርቸሌ አደረገች

የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች

የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷ ጸጉር ታየ

የቆጡን አወርድ ብላ የጣራውን አወረደች

የበላ በለጠኝ የሮጠ አመለጠኝ

የበላ ባይማታም ዱላ ይችላል

የበላችው ያገሳታል በላይ በላዩ ያጎርሳታል

የበላና የተደገፈ ወድቆ አይወድቅም

የበሰበሰ ዝናብ አይፈራም

የቡና ስባቱ መፋጀቱ

የባለጌ ባለሟል ቂጥ ገልቦ ያያል

የባሪያ ደግ የቁልቋል ዘንግ የለውም

የባስ አለ ሚስትህን አትፍታ

የባሰ አለና አገርህን አትልቀቅ

የቤቴ መቃጠል ለትኌኔ በጀኝ! አለች አሉ!

የባህር ዳር ሲታረስ ጓጉንቸር ሆድ ይብሳታል

የባልቴት ወብራ የክረምት ብራ

የባል ደግነቱ ውሽሜን መርሳቱ

የባል ደግነቱ ውሽምን መርሳቱ

የባሰ አለና አገርህን አትልቀቅ

የባእድ ፍቅር የውሀ ጌጥ አንድ ነው

የቤት ቀጋ የደጅ አልጋ

የተለጎመ በሬ ከቀንበሩ ቢያመልጥ ቢላዋ

ይጠብቀዋል

የተመረረ ድሀ ይገባል ከውሀ

የተማረና ታጥቦ የተቀመጠ ብርጭቆ ፈላጊ አያጣም

የተጠማ ከፈሳሽ የተጠቃ ከነጋሽ

የተናቀ ሰፈር በአህያ ይወረራል

የተናቀ ብእር ይገነፍላል

የተናቀ እንትን ያስረግዛል

የተናቀ ያስረግዛል

የተናገሩት ከሚጠፋ የወለዱት ይጥፋ

የተናገሩት ከሚጠፋ ጽፎ ማስቀመጥ

የተናጠ ወተት ቅቤ ይወጣዋል

የተንቀለቀለች አፍሳ ለቀመች

የተንቀዠቀዠች ውሻ ላፏ ሊጥ ለወገቧ ፍልጥ

አታጣም

የተከፋ ተደፋ

የተገነዘች ነፍስ የተለጎመች ፈረስ

የትም ፍጪው ዱቄቱን አምጪው

የት ትሂጃለሽ ቢላት በታክሲ አለች

የት ትሂጃለሽ ቢሏት በታክሲ

የት አውቅሽ ብሎ አጥብቆ ሳመኝ

የቸኮለ አፍስሶ ለቀመ

የቸገረው እርጉዝ ያገባል ስትወልድበት ገደል ይገባል

የባሰበት እመጫቷን

የቸገረው ዱቄት ከንፋስ ይጠጋል

የነሀሴ ውሀ ጥሩ ነው የሚጠጣው የለም የድሀ ነገር

ፍሬ ነው የሚሰማው የለም

የነብርን ጭራ አይዙም ከያዙም አይለቁም

የነቶሎ ቶሎ ቤት ግድግዳው ሰንበሌጥ

የነቶሎ ቶሎ ቤት ግድግዳው ብሎኬት

የነቶሎ ቶሎ ቤት ግድግዳው አስቤስቶስ

የነቶሎ ቶሎ ቤት ግርግዳው ጭራሮ

የነቶሎ ቶሎ ቤት በሊዝ ተሸጠ

የነቶሎ ቶሎ ቤት ዘበኛው ቶሎሳ

የነፉክክር ቤት ሳይዘጋ ያድራል

የእናት እርግማን ወለምታ ነው

የእናት ሞትና የግር እሳት እያደር ያንገበግባል

የእናት ልጅ ቢጣላ እውነት ይመስላል ለሌላ

የእናት ልጅ የሌለው አይበላ ሽሮ የሌለው ምንቸት

አይፈላ

የናት ሆድ ዥንጉርጉር

የናት ሆድ ዥንጉርጉር ወላጅ ቀይና ጥቁር

የናት ልጅ የጎን አሳጅ

የናት ሞትና የድንጋይ መቀመጫ እያደር ይቆረቁራል

የናትን ክፋት የደመናን ውሀ ጥማት ባለቤቱ ያውቀዋል

የናት ድሀ የለውም

የንግዳ አይን አፋር ባለቤቱን ይጋብዛል

የአህያ ባል ከጅብ አያስጥልም

የአህያ "እቃው" ሆዱ ውስጥ ነው

የአሳ ግማቱ ከወደ አናቱ

የአሳ ግማቱ ከወደ ጭንቅላቱ

የ10 አለቃዬ ምክትሌ ሆይ አንተም እንደ መቶ

ትኮራለህ ወይ

የአባትህ ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍ

የአባይ ልጅ ኩሬ

የአባይን ልጅ ወዳቂ የዞማ ልጅ ሳቂ

የአባይን ልጅ ውሀ ጠማው የላጭን ልጅ ቅማል

በላው

የአንዱ ሀገር ዘፈን ለአንዱ ሀገር ለቅሶ ነው

የአንድ ቀን መዘዝ ያለ ዘጠኝ ወር አይመዘዝ

የአይጦች አድማ ምርጫ እስኪደርስ ነው

የአገሬ ሰዎች ተጠንቀቁ የሰረቁት ስጋ ያስይዛል መረቁ

የአፍ ወለምታ በቅቤ አይታሽም

የአፍ ወለምታ በፖሊስ ይታሻል

የእህል ክፉ አጃ የሳር ክፉ ሙጃ የነገር ክፉ እንጃ

የእህል ጣም በጉረሮ የነገር ጣም በዦሮ

የእብድ ገላጋይ ድንጋይ ያቀብላል

የእናት ሞትና የድንጋይ መቀመጫ እያደር ይቆረቁራል

የእንጨት ምንቸት እራሱ አይድን ሌላ አያድን

የክፉ ሰው ተዝካር ውሀ ያስወስዳል በህዳር

የክረምት ጥማትና የመከር ጊዜ ረሀብ አለባለቤቱ

የሚያውቀው የለም

የወረት ውሻ ስሟ ወለተኪሮስ

የወረቀት ላይ ነብር የተግባር ስንኩል (አንሁን)

የወንድ አልጫ የእንዶድ ሙቀጫ

የወንድ አጭር ዝንጀሮ የሴት አጭር ወይዘሮ

የወንድም ልጅ ባይወልዱትም ልጅ

የወንዶች ባል አይተህ ማር

የወንድ ልጅ ሞት ያደረገውን የዘነጋለት

የወንድ አልጫ እንዶድ ሙቀጫ

የወንድምህ ጢም ሲላጭ ጢምህን ውሀ አርስ

የወጣ ቢገባ የገባ ይወጣል

የወደቀ ዛፍ መንገዱን ዘጋ@

የወደደና የአበደ አንድ ነው

የወደዱትን ሲያጡ የጠሉትን ይቀላውጡ

የወጋ ቢረሳ የተወጋ አይረሳም

የወጋ ቢረሳ ፖሊስ ያስታውሳል

የወጌሻ ልጅ ዛፍ ላይ ያድራል

የወደቀ ዛፍ ምሳር ይበዛበታል

የዋኘ ይሻገራል የሰራ ይከብራል

የውሀ ሽታ የእባብ ፍለጋ የለውም

የውሀ ውሀ ምን አለኝ ቀሀ

የውሀ ጡር በእድፍ ያስታጥባል

የውድማ ዘንዶ ይቀጠቀጣል እንደበረዶ

የዘመድ ዘመድ ወንዝ ያሻግራል

የዘመድ ጥል የስጋ ትል

የዘሬን ብለቅ ይቆማምጠኝ አለ ቆማጣ

የዘንድሮውስ ብርድ ቆማጥ ያሳቅፋል

የዘገነ አዘነ ያልዘገነ አዘነ

የዝንጀሮ ለቅሶ መልሶ መላልሶ

የዝንጀሮ ስብሰባ በውሻ ጩኸት ይበተናል

የዝንጀሮ ንጉስ እሱ ይከምር እሱ ያፈርስ

የየጁ ቄስ አንደዜ ቅኔው ቢጎልበት ቀረርቶ ሞላበት

የየጁ ደብተራ ቅኔ ቢያልቅበት ቀረርቶ ጨመረበት

የደላው ሙቅ ያኝካል

የደላው ወርቅ ያስራል

የደመና ውሀ ጥምና የእናት በደል አይታወቅም

የደንቆሮ ለቅሶ መልሶ መልሶ

የደንቆሮ ለቅሶ መልሶ መላልሶ

የደንቆሮ ሰርግ በሽብሸባ ያልቃል

የድመት ልጅ መቧጨሯን አትረሳም

የድሮው ኮንጎዬ ካሁኑ ስቶኪንጌ ተሻለኝ

የድፍድፍ ኩራቱ ውሀ እስኪገባበት

የድፍድፍ ኩራቱ ውሀ እስኪገባ ነው

የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክሳል

የጅብ ችኩል ቶሎ ያፏጫል

የገበያ ሽብር ለሌባ ሰርጉ ነው

የገበያ ግርግር ለሌባ ይበጃል

የገንዘብን ነገር ካሰላሰሉት አባ ሀናም ሞቱ

እንደጨበጡት

የገጣጣ ሚስት ችግሩን አልቅሶ ካልነገራት

አይገባትም

የጉልበት ግማሹ አፍ ነው

የጉድ አገር ገንፎ በጣም ይጣፍጣል

የጉድ አገር ገንፎ እያደር ይፋጃል

የጉሮሮን መታነቅ ያይን መደንቆል ያስጥለዋል

የጎረምሳ መልኩ እንጂ አነጋገሩ አያምርም

የጎጃም አዝመራ ሽንብራ ነው አሉ እኛም እንዳንበላ

ተነቀለ አሉ

የጊዜ ግልባጭ እግር ሰውነት ያካል

የግመል ሽንት ይመስል ሁሌ ወደኋላ

የግፍ ግፍ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ

የጥቅምት ቀን እና የቆንጆ ሳቅ አያታልልህ

የጥንት ወዳጅክን በምን ሽኘኸው በሻሽ አዲሱ

እንዳይሽሽ

የጨለማ አፍጣጭ የእውር ገልማጭ

የጨለማ አፍጣጭ የእውር ገልማጭ አይረባም

የጨረቃ ሂያጅ የምስክር ፈራጅ

የጨረቃ ሂያጅ የምስክር ፈራጅ

የጨረቃ ንጋትና የእውር ሞት አይታወቅም

የጨርቅ ነጩ የበራ ልጩ

የጨነቀው እርጉዝ ያገባል

የጨነቀው እርጉዝ ያገባል ስትወልድበት ገደል ይገባል

የጨነቀው ይዋጋል ያልደረሰበት ያወጋል

የጨዋ ልጅ ሁሉ አርግዟል ሆዱ

የጨዋ ልጅ ሁሉ አርግዟል በሆዱ

የጨዋ ልጅ ሲያዝን አሳ በወንዝ ይመክን

የጨዋ ልጅ ሲያዝን ውሀ በወንዝ ይመክን

የጨዋ ልጅ ሲፋታ ይጋባ ይመስላል

የጨዋ ልጅ ከከተማ የድሀ ልጅ ከውድማ

የጨዋ ልጅና ቅል ተሰባሪ ነው

የጨው ገደል ሲናድ ሞኝ ይስቃል ብልህ ያለቅሳል

የጨው ገደል ሲናድ ብልህ ያለቅሳል ሞኝ ይልሳል

የጨውን ባለእዳ በጨው ቢያባብሉት ጨዌን ማለቱ

አይቀርም

የጨጌ ከብት በየወገኑ ይከተት

የጫማ ጠጠርና የእንጀራ ልጅ እያደር መቆርቆሩ

አይቀርም

የጫማ ጠጠርና የእንጀራ እናት እያደር መቆርቆሩ

አይቀርም

የፈላ ጠጅ የደረሰ ልጅ

የፈረሰኛ ማቅ ለባሽ የሴት ትምባሆ ቀማሽ

የፈረሰኛ ማቅ ለባሽ የሴት ትምባሆ ጎራሽ

የፈረሰ አልጋ የተሸበረ ዜጋ

የፈረንጅ አሽከር ነጭ ለባሽ ሳህን አመላላሽ

የፈሩት ይደርሳል የጠሉት ይወርሳል

የፈሪ ዱላ ሰላሳ ነው

የፈሪ ዱላ አያዳግምም

የፈሪ በትር አስር

የፈሪ ገዳይነት ለማታ

የፈሰሰ ውሀን ማቆር ይጠቅማል

የፈሰሰ ውሀ አይታፈስ

የፈሰሰ አይታፈስ የሞተ አይመለስ

የፈሲታ ተቆጢታ

የፈሳ የጥጋብም አይደል ሲረሳ

የፈስ ማደናገሪያው ዳባ

የፈስ ማደናገሪያው ዳቦ

የፈቷት ሴት ያጠቡት ወጪት የወጡበት ቤት አንድ

ነው

የፈቷት ሴት ያጠቡት ወጪት የወጡበት ቤት አንድ

ናቸው

የፉክክር ቤት ሳይዘጋ ያድራል

የፊተኛውን አሳረርሽ ቢሏት የኋለኛውን ጥሬ አወጣች

የፊት መሪ የኋላ ቀሪ

የፊት ምስጋና ለኋላ ሀሜት ያስቸግራል

የፊት እድፍ በመስታወት የሀጢአት እድፍ በካህናት

የፊት ከብት የእጅ ወረት

የፊት ወዳጅህን በምን ቀበርከው በሻሽ የኋለኛው

እንዳይሸሽ

የፊት የፊቱን አለ ጓያ ነቃይ

የፋቂ ልጅ ሰነፍ አንዱን ሳይፍቅ አንዱን ይዘፍቅ

የፋቂ ሰነፍ አንዱን ሳይፍቅ አንዱን ይዘፍቅ

የፋቂ ቆንጆ ቡድነቱን አይተውም

የፌጦ መስሎሽ ሰናፍጭ ትቀምሽ

የፌጦ ብቅል የብሳና ጌሾ የተልባ አሻሮ ይህን ጠምቆ

ለማ የሰው ነገር ለማይሰማ

የፍቅር ጣእሙ በመሳለሙ

የፍቅር ጣእሙ አልጋ ላይ

የፍቅር ጣእሙ ተቃቅፈው ሲተኙ

የፍቅር ደስታው ከሴት ጭን መሃል ይገኛል ፈልጉ

የፍየል ልጁን የሌባ እጁን

የፍየል ጅራት ቂጥ አይከድን ከብርድ አያድን

የፍየል ጅራት ብልት አይከድን ከብርድ አያድን

የፍየል ጅራት ከብርድ አያድን ብልት አይከድን

የፍየል ጅራት ከብርድ አያድን አፍረት አይከድን

የፍየል ጅራት ከብርድ አያድን እፍረት አይከድን

የፍየል ጭራና የሰው ሀሳብ ሁልጊዜ ወደ ላይ ነው

የፍጅት ወራት እሳት በወንፊት

የፖሊስ ዘመድና የቤንዚን አመድ

የፖሊስ ዘመድ የቤንዚን አመድ የለውም

ዪዪዪዪዪ .........አለ !አምቡላንስ (የቁጭት አባባል)

ያህያ ስጋ አልጋ ቢሉት አመድ

ያህያ ባል ቀለበት አያስርም

ያህያ ባል ከጅብ ጉቦ በላ

ያህያ ባል ከዥብ አያስጥል

ያህያ ውሀ ጠጭ ሳይታወቅ መጣጭ

ያህያ ልጅ ጥሎ ይረግጣል የፈረስ ልጅ ጥሎ

ይደነግጣል

ያህያ ስጋ ካልጋ ሲሉት ካመድ

ያህያ ካልጋ ሲሉት እምድር

ያህያ ስጋ ውርደተኛ አልጋ ላይ ቢያኖሩት እመሬት

ይተኛ

ያህያ ቀበጥ ከጅብ ጡት ይጣባል

ያህያ ባል ከጅብ አያስጥል

ያህያ እንግዳ የጅብ እራት ነው

ያህያ ደግነት ጭነት ማብዛት

ያህያ ውሀ ጠጭ ሳይታወቅ መጣጭ

ያህያ ጀላፋ መስክ ያጠፋ የሹም ዘፋፋ አገር ያጠፋ

ያህያ ፍለጋና የጥሬ እራት በግዜ ነው

ያህያ ፍሪዳ የእባብ ለማዳ የለውም

ያለባለቤቱ አይነድም እሳቱ

ያለአንድ የላት በዘነዘና ትነቀስ

ያለውን የሰጠ ንፉግ አይባልም

ያለውን የወረወረ ንፉግ አይባልም

ያለአዋቂ ተራች የራሱን አመልካች

ያለ ዝናብ ነጎዳ ያለ ብድር እዳ

ያለ ወጉ አህዮች ተዋጉ

ያለ ባለቤቱ አይነድም እሳቱ

ያለ የሚኖር ይመስላል የሞተ ያልነበረ ይመስላል

ያለ ይበዛል (አለ ወፍጮ)

ያለህ ምዘዝ የሌለህ ፍዘዝ

ያለ መሰረት ቤት ያለ ትምህርት እውቀት የለም

ያለ መከራ አይገኝም እንጀራ

ያለ መከራ ጸጋ ያለ ድካም ዋጋ አይገኝም

ያለ መጥረቢያ እንጨት ሰባሪ የቆማጣ ዘንግ ወርዋሪ

ያለ ምቀኛ አይገኝ ፍቅረኛ

ያለ ሴት ምን ያደርጋል ቤት

ያለ ሴት ቤት ያለበሬ መሬት

ያለ ስራ መብል ያለዳኛ ውል

ያለ ስራ መብል ያለዳኛ ውል አይቻልም

ያለ ስራ አይበላ እንጀራ

ያለ ስራ አይበላ እንጀራ አለባል ቆጥ አይሰራ

ያለስፍራው የተስበረ ሲጠግኑት አስቸገረ

ያለስፍራው የተስበረ ሲጠግኑት ያስቸግራል

ያለ በሬ ምን ያደርጋል ገበሬ

ያለበት ይብላላበት

ያለበት ይጉላላበት

ያለ ባለቤቱ አይነድም እሳቱ

ያላባቱ ቢዛቁን አባክኖ ያባክን

ያለአቻ ጋብቻ ቆይ ብቻ ቆይ ብቻ

ያለ እዳው መዝመት ዋ ብሎ መቅረት

ያለ እዳው ዘማች ዋ ብሎ መቅረት

ያለ ክንፍ መብረር ያለ ስራ መክበር

ያለው ሳይዋደድ ለሞተው መናደድ

ያለው ይምዘዝ የሌለው ይፍዘዝ

ያለው ይመዛል የሌለው ይፈዛል

ያለው ይበላል የሌለው ያፈጣል

ያለውን ካልሰቱ በስም አይበሉ

ያለ ዘዴ ጋሻ እንቅብ ነው

ያለ ዘመድ ነግሶ ያለ አቡን ቀስሶ

ያለ ዝናብ ነጎዳ ያለብድር እዳ

ያለ የሚኖር ይመስላል የሞተ ያልነበረ ይመስላል

ያለ ጊዜው የተወለደ ልጅ አባቱን ጥሎ አያቱን ያስረጅ

ያለ ጎረቤት ቡና ያለ ሙያ ዝና

ያለ ጎታ ደረባ ያለልብስ ካባ

ያለ ጎተራ ደረባ ያለልብስ ካባ

ያለ ጎታ ደረባ ምንድን ነው

ያለ ይበዛል አለ ወፍጮ

ያለ ጥርስ ቆሎ ያለ ጓድ አምባጓሮ

ያለ ጨው በርበሬ ያለሞፈር በሬ

ያለ ፊቱ አይቆርስ ያለባለቤቱ አይወርስ

ያለ ፍርድ ማሰር በፈጣሪ ማማረር

ያለ ፍቅር ሰላም ያለ ደመና ዝናብ

ያለ ፍቅር ጸሎት ያለ እንጨት እሳት

ያሉሽን በስማሽ ኖርዌይ ባልመጣሽ

ያሉሽን በሰማሽ ገበያ ባልወጣሽ

ያላማረ ሰርግ ጉልቻው ይሽረፋል

ያላዋቂ ሳሚ ንፍጥ ይለቀልቃል

ያላዩት አገር አይናፍቅም

ያላረፈች ምላስ ሸማ ትልስ

ያላረፈች እግር ከዘንዶ ጉድጓድ ትገባለች

ያላሰብከውን አግኝ መረገመም ምርቃን አይደል

ያላስደጉት ውሻ ቤት ዘግተው ቢመቱት ዞሮ ይናከሳል

ያላባቱ ቢዛቁን አባክኖ ያባክን

ያላዋቂ ሳሚ ምላስ ይነክሳል

ያላወቁ አለቁ

ያላዞረ ሲዞር አደረ

ያላዋቂ ቆራሽ ማእድ አበላሽ

ያላየ ልጅ ዳቦ ፍሪዳው

ያላዩት አገር አይናፍቅም

ያላዩት ነገር ክፉ አይደለም መልካምም አይደለም

ያልሰማ ጆሮ ከጎረቤት ያጣላል

ያልበላህን አትከክ

ያልበላ ዳኛ አያሟግት ያልጠጣ እንግዳ አይጫወት

ያልተመካ ግልግል ያውቃል

ያልተማረ ዋናተኛ ከዳኛ ፊት እንቢተኛ

ያልተነካ ግልግል ያውቃል

ያልተገላበጠ ያራል

ያልታደለ ቆዳ ሲላፋ ያድራል

ያልታደለ በረዶ ከድንጋይ ላይ ያርፋል

ያልታደለች ከንፈር ሳትሳም ታድራለች

ያልታደለ ከንፈር ሊፕስቲክ ያበዛል

ያልታደለ ከንፈር ሳይሳም ያረጃል

ያልነበረ ያፈርሳል ቀዳዳ ያፈሳል

ያልወለደ አጋድሞ አረደ

ያልወለድኩት ልጅ አባባ ቢለኝ ሆዴን ባርባር አለኝ

ያልወለድኩት ልጅ አባዬ ቢለኝ አፌን ዳባ ዳባ አለኝ

ያልጠረጠረ ተመነጠረ

ያልሟል ይተረጉሟል

ያልሞላ ተርፎ አይፈስም

ያልሞተና ያልተኛ ብዙ ይሰማል

ያልሰማ ጆሮ ከጎረቤት ያጣላል

ያልሰማ ጥኑ ነው ባልሽ ወዳጄ ነው

ያልሰሙት ነገር ክፉም መልካምም አይደለም

ያልሰጡት ተቀባይ ያልጠሩት አቤት ባይ

ያልሳሉት አይላጭ ያላዩት አይቆጭ

ያልቆረጠ እግብ አይደርስም

ያልበሉት እዳ ያልጠሩት እንግዳ

ያልበላ ሬሳ ያልለበሰ እንሰሳ

ያልበላ ዳኛ አያሟግት ያልጠጣ እንግዳ አያጫውት

ያልበላኝን ቢያከኝ አይገባኝ

ያልበጀው እሳት ፈጀው

ያልተማረ አይጸድቅ ያልተወቀረ አያደቅ

ያልተማረ አይምርም ያልተወቀረ አያደቅም

ያልተመታ ልጅ ሲቆጡት ያለቅሳል

ያልተማረ ዋናተኛ ከዳኛ ፊት እንቢተኛ

ያልተረታ አይረታ ያልጠገበ አይማታ

ያልተሾመ አያዝ ያልቀሰሰ አያናዝዝ

ያልተሾመ አያዝ ያልቀሰሰ አይናዝዝ

ያልተቀጣ ልጅ ቢቆጡት ያለቅሳል

ያልተቀጣ ልጅ ያልታጠበ እጅ

ያልተነካ ግልግል ያውቃል

ያልደረሰበት ግልግል ያውቃል

ያልተገላበጠ ያራል

ያልተገላበጠ ያራል ያለ ይበዛል አለ ወፍጮ

ያልተገራ ፈረስ ይጥላል በደንደስ

ያልተጠናከረ ድንገት ተሰበረ

ያልተፈተነ ወዳጅ ያልተተኮሰ ሸክላ

ያልተፈተነ ወዳጅ ያልተተኮሰ ሸክላ ነው

ያልታረመ አፍ ከዋንጫ ይሰፋል

ያልታየ እንጂ ያልተሰማ ያልተደረገ እንጂ ያልተባለ

ነገር የለም

ያልታደለ በረዶ ከድንጋይ ላይ ያርፋል

ያልታደለ ከንፈር ሳይሳም ያረጃል

ያልታደች ወፍ አይኗ በጥቅምት ይጠፋል

ያልነበረ ያፈርሳል ቀዳዳ ያፈሳል

ያልወለደ አንጀት ጨካኝ ነው

ያልወለደ አይነሳ የሽምብራ ማሳ

ያልወለደ አጋድሞ አረደ

ያልወለዱ ሁሉ ጊደሮች ይባላሉ

ያልወለደኩት ልጅ አባባ ቢለኝ አፌን ዳባ ዳባ አለኝ

ያልወለደኩት ልጅ አባ አባ ቢለኝ አፌን ዳባ ዳባ አለኝ

ያልዘሩት አይበቅልም

ያልዘራሁት በቀለብኝ ዱባ ያልኩት ቅል ሆነብኝ

ያልዘራውን የሚበላ ዝንጀሮ ነው

ያልገደለ በሽታ ምስጋና የለውም

ያልገደለ ዘማች ያልወለደ አማች

ያልጋ ሴሰኛ ሶስት ያስተኛ

ያልጠረጠረ ተመነጠረ

ያልጠሩት መካሪ ያልሾሙት ፊታውራሪ

ያልጠሩት ሰርገኛ በትረኛ

ያልጫ ድንፋታ እንጀራ እስኪቀርብ

ያልጫ ድንፋታ እንጀራ እስኪቀርብ ነው

ያልፋል እስኪያልፍ ያለፋል

ያመል ትንሽ ይጥላል በጭራሽ

ያመሰገኗት ቅል ባፏ ታፈሳለች

ያሞሌ ጥጃ በወንዙዋ ትናፋ

ያመነታ ተመታ

ያመኑት ሲከዳ ይቀላል እዳ

ያመኑት ፈረስ ጣለ በደንደስ

ያመጣሁት ውሻ ነከሰኝ ያነደድኩት እሳት ጠበሰኝ

ያመጣል አንበሴ ይበላል ኮሳሴ

ያማከሩት ዳኛ ያግዛል የመተሩበት እጅ ይወዛል

ያምላክን ነገር ምኑን አውቀሽው ወይ እኔ እበላው

አንቺ አርመሽው

ያምላክን ነገር ስንቱን አውቀሽው ወይ እኔ እበላው

አንቺ አርመሽው

ያምራል ብለው ለነብር ልጅ አይድሩም

ያምራል ብለው ከተናገሩት ይከፋል ብለው ያስቀሩት

ያምራል ብለው ከመናገር ይከፋል ብሎ መተው

ያምራል ብሎ ይሸልሟል ያውቃል ብሎ ይሾሟል

ያምሩዋል ይታደሏል

ያምና ሞኝ ዘንድሮም ደገመኝ

ያምናውን ዘንድሮ የአዋጁን በጆሮ

ያሞላቀቁት ልጅ አይሆንም ወዳጅ

ያሞሌ ጥጃ በወንዙዋ ትነፋ

ያረረበት ያማስል

ያረሮ ልጅ ጠለፋ

ያረሰ እንደ ልቡ ጎረሰ

ያረገዘች ታስታውቅ ከደረቷ ትታጠቅ

ያረጀን ሹም ገባር ይከሰዋል ያረጀን ጅብ አህያ

ይጥለዋል

ያራስ ክፉ መበለት ያደጋ ክፉ እሳት

ያራሷን በርጉዙዋ

ያራሷን ገንፎ እርጉዙዋ ውጣ ሞተች

ያርጋጅ አናጋጅ

ያርጋጅ አንጓጅ

ያሳደግሁት ውሻ ነከሰኝ ያነደድሁት እሳት ጠበሰኝ

ያስረ ይፈታል የሰጠ ይረታል

ያስለመዱት ሰው ሁልጊዜ እጅ ያያል

ያሰቡት አይገድም ጎኔን ላርገው ጋደም

ያሳደግኋት ጥጃ አለችኝ በርግጫ

ያሳደኩት ውሻ ነከሰኝ ያነደድኩት እሳት ጠበሰኝ

ያስታርቀኛል ሙተራ እያንዳንዱ እየኮራ

ያሽላል ያሉት ኩል አይን ያጠፋል

ያቀረቡልህን ጉረስ የተረፈህን መልስ

ያበረ ወገኑን አስከበረ

ያበራሽን ጠባሳ ያየ በእሳት አይጫወትም

ያ በሬ ባላገደደ ያ በሬ ገደል ባልገባ

ያ በሬ ባገደደ ያ በሬ ገደል ገባ

ያ በሬ ባገደደ ያ በሬ ገደል ገባ ያበጠው ይፈንዳ

ያበደ ለኑሮው የፈረደ ለጉሮሮው

ያበደች ጋለሞታ እናቷን ትመታ

ያበደና የወደደ አንድ ነው

ያበጠው ይፈንዳ

ያባ ሆይ መቋሚያ ላዩ ባላ ታቹ ዱላ

ያባ ጎፍናኔ ቤቱ በሪድ

ያባትህ ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍ

ያባት ወዳጅ የድንጊያ ገድጋጅ

ያባቱን ቢሰጡት ህይወቱ ያባቱን ቢነሱት ሞቱ

ያባቱን ያገኘ ህይወቱ ያባቱን ያጣ ሞቱ

ያባት ልጅ የደንደስ ስጋ

ያባት ልጅና ጆሮ አንድ ነው

ያባት ምርቃት አያስገባም ጥቃት

ያባት ልጅ የማድጋ ዶሮ ነው

ያባት ልጅ የማድጋ ዶሮ አንድ ነው

ያባት ሞቱን አይወዱ ረጃቱን አይሰዱ

ያባት ሞቱን አይወዱ ረድኤቱን አይሰዱ

ያባት ሲቀር ምሰህ ቅበር

ያባት አገር ከሞት አያስጥልም

ያባት እርግማን ሲዳሩ ማልቀስ

ያባት እዳ ለልጅ ያፍንጫ እድፍ ለእጅ የወፍጮ እዳ

ለመጅ

ያባት ወርቅ ባለዝና እህል ለቀጠና

ያባት ያምራል የባእድ ያናግራል

ያባት ያምራል የባእድ ያኖራል

ያባት ደግ ይደልላል ያባት ክፉ ለእንጀራ ልጅ ያደላል

ያባትህ ቤት ሲበዘበዝ አብረህ ዝረፍ

ያባትህና የናትህ ወገኖች ሲጣሉ ጥግህን ያዝ

ያባያ ልጅ ወዳቂ ያራኝ ልጅ አጥባቂ

ያባያ እናት አትታረድም

ያባያ ወንድሙ አይታረድም

ያባይ ምልክቱ አንደበቱ የገዳይ ምልክቱ ሽልማቱ

ያባይ እንባ አይታገድም

ያባይን እናት ውሀ ጠማት

ያባይ ውሀ ተለያየ ሲሉ ተገናኘ

ያባይን ልጅ ውሀ ጠማው የላጭን ልጅ ቅማል በላው

የአብሮ አደግ ልብ በቁና ይሰፈራል

ያብዬን እከክ ወደ እምዬ ላከከ

ያብዬን እከክ ወደ እምዬ ልክክ

ያተር ክምር የጭሰኛ ክብር

ያናጢን ልጅ ጅብ በላው የላጭን ልጅ ቅማል ፈጀው

ያንበሳ ልመና ጋማ ይዞ ነው

ያንበሳ ልመና ጋማ ይዞ የቄስ ልመና አናዞ

ያንበሳ ማላጅ ጋማ ይዞ ጅብን መውጋት አህያን

ተጎዝጉዞ

ያንበሳ ማላጅ ጋማ ይዞ ጅብን መውጋት አህያን ተገን

ይዞ

ያንበሳ አማላጅ ጋም ይዞ ጅብን መውጋት አህያን ተገን

ይዞ

ያንበሳ ኮርዲዳና የጨዋ ልጅ ሞግዚት ከመሆን

ይሰውርህ

ያንበሳ ገራም ይውላል ከላም

ያንተን የሚመስል የኔም አለኝ ቁስል

ያንቺን አትበይ ገንዘብ የለሽ የሰው አትበይ ምግባር

የለሽ

ያንካሳ ልቡ ኢየሩሳሌም

ያንዱ በሬ ሲሞት ላንዱ አጋዘኑ ፍስሀው ላንዱ ሀዘኑ

ያንዱ ቤት ሲቃጠል ላንዱ ቋያው ነው

ያንዱ ቤት ሳይጠፋ ያንዱ ቤት አይለማ

ያንዱ ቤት ካልጠፋ ያንዱ ቤት አይለማም

ያንዱ ነገር ላንዱ የእንጀራ ልጁ ነው

ያንዱ አገር መልከኛ ላንዱ አገር ገባር ነው

ያንዱ ላም ወተት ያንድ እርሻ እሸት

ያንድ ሚስቱን የሺ ከብቱን

ያንድ ሰው ፍቅር ባንድ እጅ እንደማጨብጨብ ያለ

ነው

ያንድ ሰው ነገር ሰምተህ አትፍረድ

ያንድ በሬ እሸት ያንድ ላም ወተት

ያንድ እርሻ እሸት ያንድ ላም ወተት

ያንድ ቀን ስህተት ለዘላለም እውቀት ነው

ያንድ ቀን ስህተት የዘላለም ጸጸት ነው

ያንድዋ እለት አንድዋ ባልቴት

ያንጎርጓሪ ጉልበት የተራጋጭ ወተት

ያኖሩት እንቅርት መለያ ይሆናል

ያኖሩት እንቅርት ያገለግላል

ያኩራፊ ምሳ እራት ይሆነዋል

ያኩራፊ ምሳው የነበረ እራት ይሆነዋል

ያኮረፈ ልብሱን አራገፈ

ያኮረፈ ምሳው እራቱ ነው

ያወረደ መአቱን ያመጣ ምህረቱን

ያወቀ ተጠነቀቀ የዘነጋ ተነጠቀ

ያወቀ ተጠነቀቀ የዘነጋ ተወጋ

ያወቀ ተጠነቀቀ ያላወቀ ተነጠቀ

ያወቀ ናቀ

ያወቀ ዘለቀ ያላወቀ አለቀ

ያወቁ ሲታጠቁ ያላወቁ ተሳቀቁ

ያዋቂ ሴት ቤት አለው ውበት

ያዋቂ አጥፊ የእስራኤል ጣፊ

ያዋቂ አጥፊ የጾመኛ ገዳፊ

ያዋጁን በጆሮ የእለቱን በቀጠሮ

ያውሬ ስጋ ለወሬ

ያውቃል ብሎ ያሟል ያምራል ብሎ ይሸልሟል

ያውቃል ብሎ ይሾሟል ያምራል ብሎ ይሸልሟል

ያው እንዳያችሁኝ ቅዳሜ የወጣሁ ይቆጡኛል ብዪ

አርብ ማታ መጣሁ

ያዙኝ ልቀቁኝ

ያዛዥ ቤተ ክርስቲያን ሳሚ ያጋፋሪ ራስጌ ቋሚ

ያየ ላውራ ቢል ያልሰማ አወራ

ያየ ላውራ ቢል የሰማ አወራ

ያየ ልናገር ቢል የሰማ ላውራ አለ

ያየ ቢሄድ የሰማ ይመጣል

ያየ ቢሄድ ያልሰማ ይመጣል

ያየ ይናገራል የተወለደ ይወርሳል

ያዩትን ሊሰሩ አይናቸውን ታወሩ

ያዩትን ቢያጡ ያላዩትን ይቀላውጡ

ያያን ጨንቋራ ሁሉ ያየዋል

ያይጥ ምስክሯ ድንቢጥ

ያይጥ ሞት የድመት ሰርግ

ያይጥ እርዳታ በጭራንፎ ያልቃል

ያይጥ ፉከራ ለመከራ ድመት ምን ሊበላ

ያይጦች ዝላይ ለነአቶ ውሮ ሲሳይ

ያደረገችውን ታስታውቅ ከደረቷ ትታጠቅ

ያደፈ በእንዶድ የጎለደፈ በሞረድ

ያደፈውን በእንዶድ የጎለደፈውን በሞረድ

ያዳቆነ ሰይጣን ሳያቀስ አይለቅም

ያዳቆነ ሰይጣን ሳያቀስ አይቀርም

ያዳቆነ ሰይጣን የግል ኮሌጅ ከፈተ

ያዛቆነ ሰይጣን ሳያቀስ አይቀርም

ያዳኝ ውሻ ጠጉር ባፉ ብትር ትርፉ

ያገሩን ሰርዶ ባገሩ በሬ

ያገሩን ሰርዶ ያገሩ በሬ ይወጣዋል

ያገር ልማት የገበሬ ሀብት

ያገር ልጅ በምን ይመታል በኩበት ያም እንዳይሄድ

ያም እንዳይሞት

ያገር ልጅ በምን ይማታል በኩበት ያ እንዳይሄድ ያ

እንዳይሞት

ያገር ልጅ የማር እጅ

ያገር ልጅ የማር ጠጅ

ያገር እድር ለንጉስ ያስቸግር

ያገር እድር ጦም ያሳድር

ያገርህ ልጅ ብታገባት ሚስትህ ብትፈታት እህትህ

ያገርህ ልጅ ብታገባት ሚስትህ ብትፈታት እትህ

ያገርህ ዱር ፍራትን ያስወግዳል እንጂ ከሞት

አያድንም

ያገርን ሰርዶ ያገር በሬ ያወጣዋል

ያገባሽስ ይፈታሻል ይብላኝ ለወለደሽ

ያገባሽ ይፈታሻል ይብላኝ ለወለደሽ

ያገባሽ ይፈታሻል ወዮለት ለወለደሽ

ያገኘ ከራሱ ያጣ ከዋሱ

ያጓኑት ድንጋይ ተመልሶ ራስን

ያጓኑት ድንጋይ ተመልሶ ራስን ይመታል

ያጣ ለማኝ ተሳድቦ ይሄዳል

ያጣጣመ የቆረጠመ

ያጣ ሰው ያገኝ አይመስለውም

ያጥንት ፍላጭ የስጋ ቁራጭ

ያፍ እማኝ አደረገኝ ለማኝ

ያፌን እስክውጥ እድሜ ይስጠኝ ይላል እርኩም

ያፍ ወለምታ በቅቤ አይታሽም

ያፍ ዘመድ በመንገድ አይገድ

ያፍላ ለማኝ አደረገኝ ለማኝ

ያፍላ የለው ቀርፋፋ

ያፍላ የለው ቀፋፋ

ይሄ እንግዳ ቸኮለ ሊያድር ነው መሰለኝ

ይህ ሁሉ ከርከሬሻ ባንቺ የተነሳ

ይህ ሁሉ ጠባሳ ባንቺ የተነሳ

ይህ አንበሳ ደም ደም አገሳ

ይህ እንግዳ ቸኮለ ሊያድር ነው መሰለኝ

ይህ ከርከሬሻ ዳቦዬን ለማንሻ

ይህን ብሰጥ ምን እውጥ

ይህን ብትሰጥ ምን ትውጥ

ይህንን ፈርቼ ደጄን በቀን ዘግቼ

ይህን ፈርቼ ደጄን በቀን ዘግቼ

ይህች ባቄላ ካደረች አትቆረጠምም

ይህች ተፍተፍ እኔን ለመመንተፍ

ይሆናል ብዬ ጎሽ ጠመድኩ የማይሆን ቢሆን ፈትቼ

ሰደድኩ

ይሆን ቢሆን ዝሆን ይበላ ቢሆን

ይሉሽን በሰማሽ ገበያም ባልወጣሽ

ይሉሽን ባልሰማሽ ገበያም ባልወጣሽ

ይሉሽን ባወቅሽ ገበያም ባልወጣሽ

ይሉ አይሉ የት አለ ቅሉ

ይሉሽን ብትሰሚ ጎንደር ላይ ክረሚ

ይሉኝ አይል ውሽማ ዶሮ ሲጮህ ይማለላል

ይሉኝ አይል የኋላውን አያይ

ይሉኝ አይል ጸሀፊ ከሙሴ ይገድፋል

ይሉኝታ ተፈርቶ እስከመቼ ተቆራምቶ

ይሉኝታና መጠቀም ባንድነት አይገኙም

ይሉኝታ የራስ አሊን ቤት ፈታ

ይመሰክረዋል ለነፍሱ ይፈተፍተዋል ለከርሱ

ይመስል አይመስል የጠይብ እጅ ተከሰል

ይመታሉ የሚጠሉ ይመስል ይስማሉ የሚወዱ

ይመስል

ይሙት የገደለ ይካስ የበደለ

ይማሩኝ እያልክ ከምትታማበት አትገኝ

ይማሰላል ካሉ ይዛመዳል አይገድም

ይሰጠኝ መስሎ ሊሸጠኝ

ይሰጡኛል ብሎ ከሰጠ ቆጥቦ የበላ በለጠ

ይስጡ ብሎ ከሰጠ ቆጥቦ የበላ በለጠ

ይሰጣል መስሎ ይሸጣል

ይስብረኝ ይሰንጥረኝ የሚሉ የሰውን ልብ ሊሰብሩ

ይቅር ለእግዜር ወድቆ እማይሰበር

ይቅር ለእግዜር ወድቆ አይሰበር ሞቶ አይቀበር

ይቅደም ደግነት ይከተል ቸርነት

ይበላ እንደ ቤቱ ይሰራ እንደ ጉልበቱ

ይበላ እንደ ቤቱ ይሰራ እንደ ጎረቤቱ

ይበላው ካጣ ይበላበት ያጣ

ይበጃል ያሉት መድሀኒት አይን አጠፋ

ይበጃል ያሉት ኩል አይን አጠፋ

ይብላ እንደ ቤቱ ይስራ እንደ ጎረቤቱ

ይብላኝ ለወለደሽ ያገባሽስ ይፈታሻል

ይብራና ይብራ ተጣሉ በሰው ሽንብራ

ይታደሏል እንጂ ይታገሏል

ይታደሉታል እንጂ አይታገሉትም

ይቺ ባቄላ ያደረች እንደሆን አትቆረጠምም

ይቺ ጎንበስ ጎንበስ አንድም ለመፍሳት አንድም እቃ

ለማንሳት

ይቺን ለኛ ጥሬን ለጌኛ

ይቺም ቂንጥር ሆና ቡታንታ አማራት

ይቺን በላህ ብለህ ጦሜን አታሳድረኝ አለ አሉ

ይውደደኝ የጀርባዪ ቅማል አለች አንዷ

ይገርማል አህያ ከዥብ ይከርማል

ይደንቃል ይገርማል አህያ ከዥብ ይከርማል

ይኖሩዋል በደጋ ይተኙዋል በአልጋ

ይወልደዋል ካሉ ይመሰለዋል አይገድም

ይውጋሽ ብሎ ይማርሽ

ይጥሉህ አትጥላቸው ይበድሉህ አትበድላቸው

ይጠላኝ ይመስል ይመታኛል ይወደኝ ይመስል

ይስመኛል

ይወደዋል ካሉ ይመክሩዋል ይወልደዋል ካሉ

ይመስሏል

ይውጋህ ብሎ ይማርህ

ይገርመኛል ገንፎ ከራቴ

0 Comments:

Post a Comment

Subscribe to Post Comments [Atom]

<< Home