<$ambachewmulat5.blogspot.com$> <$pub-7470502258870845$>

ቁም-ነገር

Sunday, February 28, 2021


“#From the horse’s mouth” ትሉ የለም እናንተስ
#እውነትን_በግልጥ_የማይናገር_ሰው_ሁከትን_ይፈጥራል፣
በግልጥ የሚነቅፍ ግን ሰላም እንዲገኝ ያደርጋል፡፡የደግ ሰው ንግግር የሕይወት ምንጭ ነው፣የክፉ ሰው ንግግር ግን የዐመፅ መሸፈኛ ነው፡፡ጥላቻ ሁከትን ያነሣሣል፣ፍቅር ግን በደልን ሁሉ ዐይታ በይቅርታ ታልፋለች፡፡እውነትን በምትናገርበት ጊዜ ቅን ፍርድ ታደርጋለህ፣ሀሰት ግን ፍርድ እንዲጓደል ያደርጋል፡፡ያለ ጥንቃቄ የተነገረ ቃል እንደሰይፍ ያቆስላል፣በጥበብ የተነገረ ቃል ግን ይፈውሳል፡፡የሀሰት ዕድሜ አጭር ነው፣እውነት ግን ለዘላለም ትኖራለች፡፡
#(መጽሐፈምሳሌ_ምዕ. 10 (10 – 12) – 12 (17-19)
A lie is an abomination unto the Lord and avery present help in trouble. Adlai Stevenson
(1900 – 1965)
It is always the best policy to tell the truth,unless, of course, you are an exceptionally good liar. Jerome K. Jerome (1859 – 1927)
 “#From the horse’s mouth” ትሉ የለም እናንተስ
የመጽሐፉ ዋነኛ ዓላማ ከመነሻው እስከመድረሻው የሚያጠነጥነው በተስኪያን እንደገባች ውሻ #አማራን እንዳይሸጥ እንዳይለወጥ አድርጎ በተገኘ ምናባዊመሣሪያ ሁሉ መቀጥቀጥ ነው – ፍርጃ እኮ ነው እናንተዬ፤አሁንስ ይሄ አማራ የሚባል ብሔር ባይፈጠር በተሻለው፤የጠብ ያለሽ በዳቦ ልክፍት የተጠናወተው ሁሉ አፍ ማሟሻናየጭቃ ጅራፍ ብዕር የስድብ መለማመጃ ሆኖ ይቅር እንዴ?ባይቆጭ ያንገበግብ ይባላል፡፡  በአንድ ሀገር ዜጎች መካከል እንዲህ ዓይነት አሣዛኝ ሁኔታ መፈጠሩ ለደግ አይደለምና ከአሁኑ ይልቅ የወደፊቱ እጅግ በጣም አሳሳቢ ነው፡፡ 
በዚህ አጋጣሚ መግለጽ የምፈልገው ነገር እውነትን እንዳለች እንድንመለከት እግዚአብሔር ፈጣሪያችን ሁላችንንም ልቦናና ብርታትን እንዲሰጠን ነው፡፡ እርግጥ ነው ሕንዳዊው ደራሲ ናራያና እንዳለው እውነት እንደጠራራ ፀሐይ ዐይንን ታጥበረብራለች፤ ብዙዎቻችን በቀጥታ ልናያት አይቻለንም፡፡ እውነትን ደፍሮ መጋፈጥ የሚቻለው ሰው ብርቱነው፡፡ የእውነት ጦር ከማንኛውም ሰው ሠራሽ መሣሪያየበለጠ ኅሊናን ይወጋል፡፡ ስለዚህም ነው በርካታዎቻችን ይህችን እውነት አጥብቀን ስንሸሽ የምንስተዋለው፡፡ ሁሉም ሰው የኅሊናው ባለቤት ቢሆን የምድራችን ቅርጽ ከአሁኑ እጅግ ባማረ ሁኔታ የተለዬ በሆነ ነበር፡፡ ግን ዕድሜ ለዚህ በተመሳሳይ ወቅት እየጠገበ ለሚርበው ሆድ ለጥቅም ሲባል እውነት እንደክርስቶስ አላበሳዋ እየተወገረች፣ ሀሰት ?ንግሥናንና ግርማ ሞገስን እያገኘች ዓለማችን ከምንጊዜውም በላይ በሚያስደነግጥ የጥፋት ማዕበል እየተናጠች ልትገኝ ችላለች?፡፡
እውነትን አለመናገር አንድ ነገር ነው – ዝም ማለት፡፡ እውነትን
ለመደበቅ መጣርም አንድ ነገር ነው – ማስተባበል፡፡የፈጠጠ እውነትን መካድና በፈጠራ የልቦለድ ሥራ መራር እውነትን በውሸት ቡልኮ ለመሸፈን መሞከር ግን ሰው የመሆንን ሥነ ተፈጥሮ የሚፈታተን ታላቅ ሰብኣዊና ሞራላዊ ኪሣራ ነው፡፡ የዚያን መጽሐፍ ደራሲ ያገኘሁት እንግዲህ ከሰውነት በታች ወርዶ፣ ከቀሪው የእንስሳት ዓለምም እጅግዘቅጦ በሚያሳዝን የኅልውና ደረጃ ውስጥ ወድቆ በዓሣማጋጣ የዘረኝነት አረንቋ ውስጥ ሲማስን ነው – ስንት ዓመትሊኖር? ሕወሓትንስ በዚህ ውሸቱ ጠቅሞ ስንት ዓመትሊያኖር? ከንቱነት ነው – እንደመጽሐፉ ንፋስን የመከተልያህል የከንቱ ከንቱ ነው የዚያ ሰው ልፋቱ፡፡ ወገኖቼ ናቸውየሚላቸውን ቢያድላቸው ደግሞ የኛም ወገኖች ሊሆኑይቻላቸው የነበሩ ሳይፈጠሩ ቢቀሩ የሚሻላቸው ወገኖችንወንጀልና የግፍ ቁልል ለመሸፈን የሚያደርገው ጥረት ራሱንአጋልጦ የወንጀላቸው ተባባሪ ሊሆን እንደሚችልእስክንጠራጠር ድረስ በዘረኝነት የጠባብነት ቁጢት ተተብትቦ ወያኔዎች ያልሆኑትን እንደሆኑ ለማሳመን ቆላ ደጋ መራወጡን ስናይ የምናዝነው ለኛ ለግፉኣኑ ብቻ ሳይሆን ለርሱና ለነርሱ ሳይሞቱ ለሞቱት ወገኖቻችንም ጭምር ነው፡፡ አንዳንዴ
ሟችም ለገዳይ ማዘኑ የነበረና ተገቢም ነው፡፡ የሚገድልና
የሚዋሽ ሰው ወድዶ አይደለምና እውነትም ይበልጥ ማዘን
በሀሰት ሚዛን እየመዘነ፣ በሀሰተኛ ምላስ እየፈረደ ንጹሓንን
ለሚያጠፋ ነው፡፡ ሰው በጤናው ሰውን አይገድልም፤ ሰው በጤናው አይዋሽም፤ ሰው በጤናው መጥፎ ድርጊት ውስጥ
አይገባም፡፡ አንድ ሰው የሆነ ሥነ አእምሮኣዊ ወይም ሥነ
ልቦናዊ ችግር ውስጥ ካልተዘፈቀ በስተቀር ከመሬት ተነስቶ ሰው አይዘልፍም ወይም አይገድልም፡፡ ይህ ዓይነቱ ሰው ሕክምና እንዲያገኝና ፈጣሪ ከእሥራቱ እንዲፈታው ቢጸለይለት በረከት ያስገኛል እንጂ ክፋት የለውም፡፡
ስለዚህም ዐውቀውም ይሁን ሳውቁ ለጠፉ ወንድምና
እህቶቻችን በጋራ እንጸልይላቸው፤ ልል የምችለው ቀዳሚ ነገር ይህንን ነው፡፡
‹ባልዋሽ፣ባልገድል፣ዝም ብል፣… ይህን ወይ ያን ጥቅምና ሥልጣን ላጣ እችላለሁ፡፡› ብሎ የሚያስብም የምኞቱ ባሪያ
ሆኖ ወደ ወንጀል ዓለም እየገባ ነውና ሊታዘንለትና ሊጸለይለት
ይገባል፡፡ እንጂ በመሠረቱማ የሰው ልጅ ሁሉ አንድ ነው –
ልዩነታችን ጥፋታችንና ልማታችን፡፡ በጥፋታችን እንጠፋፋለን፤
በልማታችን በሀብት እንበለጽጋለን፤በአስተሳሰብና
በአመለካከትም እናድጋለን፡፡ ይህን ዕድል የሚያሳጡንን
ታዲያን በጋራ እንታገላቸው፡፡ በዘረኝነት መታወር፣ በትምክህት
መወጠር፣በዕብሪት መጀነን፣ በዕውቀት መደኽየት፣ በራስ
ወዳድነት ልክፍት መጠፍነግ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡
ክርስቶስ “የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው” ያለው
በገንዘብና በሥልጣን ፍቅር ላበዱ ለዚያኛው ዘመን
አይሁዳውያን ወያኔዎች ብቻ አይደለም፡፡ ለተገነዘበው ለሁሉም ዘመን የሚሠራ ታላቅ አስተምህሮ አለው፡፡ የሞት ፈጣሪ በፍጡራኑ ሲሰቃይ፣ ሲገረፍ፣ ምራቅ እየተተፋበትና በእሾህ አክሊል እየተፌዘበት እስከስቅላት ደርሶ የሞትን ጽዋ ሲጎነጭ እነዚያን ወያኔዎች ቀርቶ ዓለምን ከናካቴው ሊያጠፋ የሚችል ኃይል አጥቶ አልነበረም፡፡ እንደመጽሐፉ ያ ሁሉ የሆነው ታዲያ እንዲሆን ግድ ስለነበረ ነው፡፡ ይህም ዘመን እንዲያልፍ ግድ ነውና በወያኔዎች ዐይን ያወጣ የብልግናሥራ ብዙም አንደነቅ፡፡ በቅድመ ትንበያ (predestination)ለምናምን አንዳንድ ወገኖች ይህ ሁሉ አብራቅዳብራ እንደሚከሰት – ወቅቱን በትክክል ባናውቅም – የቀደመ ግንዘቤ ነበረን፡፡ አይሆኑም የሚባሉ ነገሮች የሚሆኑበት አጋጣሚ ሞልቷል፡፡ በድምሩ ከ18ሚ. የዓለም ሕዝብ የወጡ በጣ የሚቆጠሩ ፅዮናውያን የሰባት ቢሊዮንን ሕዝብ ዕጣፋንታ፣ በድምሩ ከአምስት ሚሊዮን ሕዝብ የወጡ ‹ጥቂት›የትግሬ ገዢዎች የ110 ሚሊዮን ሕዝብ ዕጣ ፋንታ ይወስናሉብሎ በሰው ልጅ አእምሮ ማሰብ የሚቻል አይደለም ነበር ፡፡ ነገርግን ይሁን ያለው ከመሆን አይዘልምና እየተገረሙ የዓለምን አካሄድ በትዝብት ከመቃኘት በስተቀር ምንም ማድረግ አይቻለንም፡፡ በብሂልህ “ቀን የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል” ትል የለም? ወደህ ተሰደድህ? ወደህ ትራባለህ?
ወደህ ሀገር አልባ ትሆናለህ? አብዛኞቹ የዓለም ቢሌነሮች
እነማን ናቸው? የዓለምን ትልቅ ሥልጣን በእጅ አዙርና
በቀጥታ የተቆጣጠሩት እነማን ናቸው? ወዴት እየነዱህ ነው?
ወደ ጥፋ ወይንስ ወደ ልዕልና? በኢትዮጵያስ ያንን ዓለም
አቀፍ ነፀብራቅ ቁልጭ ብሎ እያየኸው አይደለምን? ዘመኑ
የጥቂቶች ነው ወዳጄ ልቤ፡፡ ሁሉን ቢያወሩት ሆድ ባዶይቀራል፡፡
እንደውነቱ ውሸት የሚናገር ሰው በሥቃይ ውስጥ ያለ ነው፡፡
እውነትን የሚናገር ሰው ግን በሥቃይ ውስጥ ላለመኖር
የቆረጠ ሰው ነው፡፡ እውነትን በመናገር ብዙ ነገር እናጣለን፡፡
ከቅርብ ጓደኛና ዘመድ ጀምሮ የምናጣው ብዙ ነገር ነው –
በዓለማዊ አስተሳሰ መብል፣መጠጥ፣ድሎት፣ሥልጣን፣ፍቅረኛንና የትዳር አጣማሪን ሳይቀር ብዙ ነገሮችን ልናጣ እንችላለን፡፡ ሀሰት
መታወቂያዋ በሆነ ዓለም ውስጥ ስንኖር እውነትን ለመናገር
ከቆረጥን እንደዕብድ ልንቆጠርና በውግዘት ከአካባቢና
ከማኅበረሰብም ጭምር ልንገለል እንችላለን – ያኔ ሃይማኖት፣ ባህል፣ ወግና ልማድ የተባለው ይበልጡን በውሸት የተቃኘው ማኅበራዊ ሥርዓት ሁሉ ይከዳህና ከሕገ ወጦቹ ጋር ሲወግንብህ መግቢያ ቀዳዳ ታጣለህ – ደግሞም
ያኔ የምትኖርባት ዓለም የሀሰት እንጂ የእውነት መገለጫ
እንዳልሆነች ትረዳና አንድም ታብዳለህ አንድም ትመንናለህ
አለዚያም በ‹ኩኑ ከማሆሙ› ሥጋዊ መርህ የቆሻሻው ዓለም
ባልደረባ ሆነህ አንተም በተራህ እንዳሻህ ትመላለስበታለህ፡፡
እከክ የሰጠ ጥፍር አይነሳምና ምርጫዎች አሉህ፡፡
ለሚያምኑበት እውነት መርዝን በድፍረት የጨለጡና የድንጋይ
ውርጅብኝ በውዱ ገላቸው ያስተናገዱ እንዲሁም በስቅላት
ያሸለቡ ሞልተዋል – ዕንቁን የላይና የታች ልጅ ክርስቶስን
ጨምሮ፡፡ በጥቃቅን የሃሳብ ልዩነት – ለምሳሌ በመሬት ቅርጽ
– ሳይቀር በሞት የተቀጡ አሉ – አሁንም ለቆሙለት እውነት
ሲሉ፡፡ ካለመስዋዕትነት ድል እንደሌለ ተገንዘበን በእውነት
መንገድ ከተጓዝን በመጨረሻው እውነት ራሷ ትክሰናለች –
አለበለዚያ ትከሰናለች፡፡
ሀሰት የሚናገር ሰው እውነት የሌለው ወይም የሚታወቅን
እውነት በመናገሩ ምክንያት አንዳች ነገር አጣለሁ ብሎ
የሚያምን ሰው ነው ማለት ይቻላል፡፡ ወያኔዎችና እበላ ባይ
ወይም የዓላማ ደጋፊ ጸሐፊያነ ትዕዛዞቻቸው የይሉኝታን ገመድ
በጣጥሰው ጥለው ነጭ ውሸቶችን በመክተብ ሥራ ላይ
የተጠመዱበት ምክንያት ካልዋሹ በስተቀር የያዙትን ቦታ
እንደሚለቁ ስለሚያውቁ ነው፡፡ የሚይዙት ካርድ ሁሉ
ያሟልጫል፡- ዴሞክራሲ ቢሉ ንዑሳን በመሆናቸውና
ከጥንትም በደምና በአጥንት ተረማምደው በመምጣታቸው
ምናልባትና በዛ ቢባል ከ6 በመቶ የሀገሪቱ ሕዝብ የበለጠ
የሚመርጣቸው እንደሌለ ያውቃሉና በዚያ ድጋፍ
በማይገኝበት የዴሞክራሲ መንገድ ሊጓዙ አያስቡትም –
ይህንንም እውነት ጃዝ ብለው ያሠማሯቸው ወገኖች
ያውቃሉ፣ በተጨባጭም አይተውታል፡፡ ጨቋኝም ሆነው
እንደቀደምቱ ነገሥታትና ወታደራዊው መንግሥት ጉልበትንና
ዘዴን ተጠቅመው እንዳይቀጥሉ ከዜጎች ብቻ ሳይሆን
ከመሬቱና ከዛፍ ቅጠሉ ተጣልተዋልና ያም አያዋጣም፡ ቀጠቀጣቸው
ብሔርን ከብሔር ፣ ቡድንን ከቡድን፣ ሰውን ከሰው፣ባልን
ከሚስት … እያናከሱ ዕድሜን መቀጠሉም ከአሁን በኋላ
የሚሠራ አይመስልም ትራፊ ወያኔዎች ፡፡ ያላቸው ብቸኛ አማራጭ በኃይል መረግጥ ነበር አልሆነም በውሸት ወሬ አደንቁሮ የተቻላቸውን ያህል ርቀት መጓዝ ነው፡፡ ስለወያኔዎች የብዙዎቻችን እውነት ይሄው ይመስለኛል፡፡
ይህ ዓለምሰገድ አሰፋ በተባለ ግለሰብ የተጻፈ ጥናታዊ
የተባለ መጽሐፍ የአማርኛ ተናጋሪውን ማኅበረሰብ አፈር ድሜ
ለማስጋጥና የሰሜኑን ሕዝብ በተለይም የኤርትራንና ትግራይን
የትግርኛ ቋንቋ ተናጋሪ ማኅበረሰብ በታሪክም በሥነ ልቦናም
በሃይማኖትም ያላቸውን ነባር ትስስር አጉልቶ በማውጣት
ከሌሎች የኢትዮጵያ ዜጎች ይልቅ እኚህ ወንድሞቻችንና
እህቶቻችን ጥንት የነበራቸውንና አሁን ሊኖራቸው የሚገባውን
የበላይነትና ሥልጣኔያዊ ገናናነት ለማሳየት ያደረገው ጥረት
ከፍተኛ ነው(በእርሱ ጥናት መሠረት ከድላቸው በኋላ ጥብቅ
የነበረው የግንኙነት ፈትል በመላላቱ ሳቢያ ትግራይ
በኢትዮጵያዊነት ስትጸና ከመረብ ማዶ ያለው ግዛት
በኤርትራነቱ እንደፀና በፀፀት መሰል ቃና ይገልጻል)፡፡ ቀጣዩን
እንይ፡-
Once in the seat of power in Addis Ababa, the
ethnic card is being aborted at a fast rate to
such an extent that even the Tigrayan features
of the regime are fading almost completely. A
new national army with no ethnic character has
been created. Except for the premiership and
foreign ministry, all cabinet posts are held by
non-Tigrayans. Even key posts such as
defense, judiciary, and police are held by non-
Tigrayans. In other words, the rational political
actors led a costly ethnic nationalist war in
Tigray without being ethnic nationalists
themselves. For the Tigrayan rational actors,
therefore, Marxism was their raison d’etre and
ethnic rationalism their means to an end. And
ethnic nationalism was a politics of power.
ተዛማጅ ትርጉም፡- [ሕወሓቶች] አዲስ አበባን ከተቆጣጠሩ
ከ1983ዓ.ም በኋላ በትግሉ ዘመን ይጠቀሙበት የነበረው
የጠባብ ብሔርተኝነት የትግል ሥልት በኅብረ ብሔራዊ
የአንዲት ሀገር ሉዓላዊ ስሜት ወዲያው በፍጥነት በመተካቱ
በመንግሥት መዋቅሩ ውስጥ ‹ለመሆኑ በዚህ መንግሥት
ውስጥ ትግሬ ሥልጣን ላይ አለ እንዴ?› እስኪባል ድረስ
የኢትዮጵያ መንግሥት ከትግሬዎች ተፅዕኖ ሙሉ በሙሉ ነጻ
ወጣ (ከ1983ዓ.ም በኋላ!)፡፡ ዘውገኝነት ያልተንፀባረቀበት
ብሔራዊ የመከላከያ ጦርም በጎሣ ተዋፅዖ ሣይሆን በብቃት
መለኪያ መሥፈርት መሠረት ተመሠረተ፡፡ ከጠቅላይ
ሚኒስትርና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቦታዎች በስተቀር
ሁሉም የካቢኔ ሚኒስትሮች ቦታዎች ትግሬ ባልሆኑ ዜጎች
ተያዙ፡፡ [Please feel free to laugh, guys!] ሌላው
ቀርቶ አሸናፊ አማፂ ማንንም አምኖ የማይሰጣቸው
የመከላከያ፣ የፍትህና የፖሊስ ዕዞች በሙሉ ትግሬ ያልሆኑ
ዜጎች እንዲይዟቸው ተደረጉ፡፡ በሌላ አባባል ሕወሓቶች
በተፈጥሯቸው የሌለባቸውን የጎሠኝነት ወይም የጠባብ
ብሔርተኝነት ባሕርይ እንደጊዜያዊ ሥልት በመጠቀም
ትግላቸውን በከፍተኛ መስዋዕትነት ከግብ ካደረሱ በኋላ
ሥልጣኑን ላልታገሉ ዜጎች አስረከቡ(ና እነሱ ባዶኣቸውን ቀሩ
– ሣቅ/ሣቂ ፤ ዛሬና አሁን ያልሣቅን መቼ ልንስቅ ጎበዝ?)፡፡
ስለዚህም ለትግራውያኑ ተጋዳላዮች ለእውነተኛ የትግላቸው
ጅማሮ ዋና አመክንዮ ማርክሲዝም ሆኖ እንደመታገያ ሥልት
ግን ጠባብ ብሔርተኝነትን ወይም ዘውገኝነትን ተጠቀሙበት
(እንጂ እነሱማ ኧረ ንሽ እቴ! ዘውገኛነት በሉት ጎጠኝነት
አሊያም ነፍጠኝነት ሲያልፉ አይነኳቸውም፡፡) እናም ሕወሓቶች
ጠባብ ብሔርተኝነትን ለሕዝባዊ ዴሞክራሲያዊ የሥልጣን
ማረጋገጫነት ተገለገሉበት እንጂ በተፈጥሯዊ ባሕርያቸው
ዴሞክራቶች ናቸው፡፡
መንግሥቱ ኃ/ማርያምን በሁለት ውሸቶቹ ዘወትር
አስታውሰዋለሁ – “እውን አሁን ደርግ አለ?” አንድ በሉ፤ “እኔ
እንኳንስ ሰው ትንኝ አልገደልኩም!” ሁለት በሉ ( በነገራችን
ላይ ከደቂቃዎች በፊት ‘Talk to Aljazeera’ ላይ
በእንግድነት የቀረበ ኑር ሚሷሪ የተባለ አንድ ፊሊፒናዊ
የቀድሞ አማፂ ቡድን መሪ ጋዜጠኛዋ ‹ራስህ ሰው ገድለህ
ታውቃለህ ወይ?› ብላ ስትጠይቀው ‹እንኳን ሰው ጉንዳንም
ገድዬ አላውቅ› ብሎ ሲመልስላት መንግሥቱ ፊቴ ላይ ድቅን
አለብኝ – ሰውዬው ውሸታም ነው ለማለት ፈልጌ ግን
አይደለም – ስለማላውቀው፡፡) መንግሥቱንና ወያኔን መሰል
አምባገነኖች በአደባባይ የሚያደርጉትን ሁሉ ‹ዐይኔን ግምባር
ያ’ርገው› ብለው ሽምጥጥ ማድረግ የባህርይ ስጦታቸው
ነው፡፡ ኢትዮጵያ ባላት የተመናመነ ኢኮኖሚ ያስተማረችው፣
በእናቱ የጭንቅ ቀንም በፈለገችው ጊዜ የደረሰላት ይህ
‹ምሁር› የሚለውን እንቶ ፈንቶ ‹እውነት ነው፤ ውሸት ነው›
ብሎ መከራከር ጉንጭን ማልፋትና በጊዜም መቀለድ ነው፡፡
ጽሑፉ ራሱ ብዙ ይናገራልና፡፡ እዚህ ላይ ከመጽሐፉ ብዙ
መጥቀስ በተቻለ፤ ግን ይብስ ሆድ ማስባስ ነው፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ ‹በሀሰት አትመስክር፤ የባልንጀራህን
የጎረቤትህንም ገንዘብና ሚስቱንም አትመኝ፤
አትስረቅ፣ጓደኛህን እንደራስህ ውደድ፣ … › ይላል፡፡
የዓለምሰገድ ሃይማኖት ክርስትና ነው ብዬ ለማመን
እቸገራለሁ፡፡ በእስልምናም ‹ዋሽ› የሚል ቁርኣናዊ ጥቅስ
ይኖራል ብዬ ስለማልገምት ሙስሊም አይሆንም ባይ ነኝ፡፡
በአይሁድ ሃይማኖትም እንዲሁ ውሸትን የሚያበረታታ
የታልሙድም ይሁን የታናክ ወይም የቶራ ጥቅስ ይኖራል
የሚል ሃሳብ የለኝም፡፡ የዚህ ሰውዬ እምነት እንግዲህ –
እርሱ ተቀበለውም አልተቀበለውም – ምናልባት በማንኛውም
መንገድ በ‹የትም ፍጪው ዱቄቱን አምጪው›ም በሉት
በ‹The end justifies the means.› የሥጋ
ፍላጎቶቻቸውን ለማርካት ምንም ነገር ከማድረግ ወደኋላ
ከማይሉት የቤተ ሣጥናኤል (Church of Satan)
አምላኪዎች ጋር የሚመሳሰል ወይም የሚነባበር መሆን
አለበት – ሊያውም ከነሱም መካከል የ‹አትድረሱብን
አንደርስባችሁም› ዓይነት የመከባበር መርህ የሚከተሉ
‹ጨዋዎች› አሉ፡፡ አንድ ኢአማኒ(ኤቲይስት) ጓደኛ አለኝ –
እንዲያውም ከአንድ በላይ፡፡ በሞራሉና በማኅበራዊ ግንኙነቱ
በጣም ጨዋና ሰውን በቸገረው የሚረዳ ደግ ነው –
altruist፡፡ ሃይማኖት የለኝም ብሎ አይዋሽም አይቀጥፍም፡፡
ጽድቅና ኩነኔ የሉም ብሎ ማመኑ ልክ እንደዚህ ሰውዬ
ቆርጠህ ቀጥል የሆነ ውሸታም እንዲሆን አላደረገውም፡፡
የዚህ ሰውዬ ውሸት ግን የተለዬ ነው፡፡ ፍላጎቱ ግልጽ ነው –
ልክ እንደ‹ፕሮፌሰር› ክንፈ አብርሃም የትግራዩ ገዢ መደብ
በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ያሳረፈውንና እያሣረፈ ያለውን
የማይፋቅ ጠባሳ በዓይጥ ምሥክር ድንቢጥ የሀሰት
ምሥክርነት ጽድቅና ለማሰጠት ነው፡፡ እውነቱን ከፈጣሪ
ቀጥሎ ዓለምና የኢትዮጵያ ሕዝብ እያወቀው ለመዋሸት
ይህን ያህል ርቀት መጓዝ ከትዝብት ሌላ እንደማይኖር እነዚህ
ሀሰተኛ የዲያብሎስ አሽከሮች ሊረዱት በተገባቸው ነበር፡፡ ግን
ያሳዝናል ኅሊናቸው በዘረኝነት ልክፍት የታወረ በመሆኑ
እውነት ታጥበረብራቸዋለችና የሚሠሩት ህፀፅ ሊታያቸው
አልቻለም፡፡ ዛሬ የነጻነት ጎሕ ሲቀድ ልጆቻቸውና የልጅ
ልጆቻው ሲያፍሩበት በአሳቻ ቦታ ተጥሎ ውሻና እሪያ
የሚሸናት አፅማቸው እንደሚታዘባቸው መገንዘብ ነበረባቸው፡፡
እዘህ ላይ ማለት የምፈልገው ነገር የቀድሞ መንግሥታት
በነዓለምሰገድ ሥሌት ምንም ይባሉ ምን፣ ምንም ይሁኑ ምን
የሠሩት ስህተት አሁን ለሚሠራው ሌላ ስህተት መሠረትና
ድጋፍ ሊሆን እንደማይችል ማወቅ የሚገባን መሆኑን ነው፡፡
ዱሮ ዘመኑ የዕውቀት አልነበረም እንበልና የዱሮውን ስህተት
አምነን እንቀበል፡፡ “Every argument has two sides.”
ከሚለው ማለፊያ ነጥብ አኳያ የታሪክ አጻጻፍ ግነትም
ግድፈትም ሊኖረው መቻሉን በታሳቢነት ይዘን ዓለምሰገድም
ሆነ መሰል ፀረ – አማራና በተያያዥነትም ፀረ-ኢትዮጵያ ጥናት
አጥኚዎች በአማራው ‹ገዢ መደብ› ላይ የሚደፈድፉት
ኃጢያት እውነት እንደሆነ በሙሉ ልብ እንቀበልላቸው፡፡
እንዲያም አመንንላቸውና አማራ ትግሬን ጨቁኗል፤ ትግራይንና
ኤርትራን ዘርፎ ጎንደርንና ሸዋን፣ ጎጃምንና ወሎን ፋብሪካ
በፋብሪካ፣ ትምህርት ቤት በትምህርት ቤት፣ ዩኒቨርስቲ
በዩኒቨርስቲ፣ አስፋልት በአስፋልት፣… አድርጓል – ይሁን ብለን
እንመን – ማመን አይገድም፡፡ በሌላም በኩል በማወቅ
ወይም ባለማወቅ ብዙ የጭካኔና የአረመኔ ተግባር የፈጸሙ
አማሮች ነበሩ፣ አሁንም በአስተሳሰባቸው ከሞቱት በላይ
ከቆሙት በታች የሆኑ ከወያኔዎች የማይሻሉ ከንቱ አማሮች
ሊኖሩ እንደሚችሉ እንመን፤ እናምናለንም፡፡ የሀገር ግንባታና
ልማዳዊ የግዛት አስተዳደር ጉዳይ ሂደታዊ ነውና በተለይ
በዱሮ ዘመን ጥፋት አይኖርም ብሎ ማሰብ ሞኝነት ነው –
እነጋሪባልዲም 38 ብጥስጣሽ የጣሊያን ግዛቶችን
አስተባብረው ነው ታላቅ ሀገር የፈጠሩት፡፡ ይህ ክስተት
ለኢትዮጵያ ሲሆን ነውር ለወያኔና ለሌላው ሲሆን ጽድቅ ሊሆን
አይገባም፤ አይችልምም፡፡ ደርግ የወደቀው በአበባ በታኝ
የሠርግ አጃቢዎች ሣይሆን በሬሣ ላይ እየተረማመዱ
በመጡ፣ በትግርኛ ፕሮግራማቸው ‹ዘራፍ! አማራ ገዳይ! አህያ
ገዳይ! አማራ ፈሪ ነው – እንዳትለቀው› እያሉ በወሎና ሸዋ
የዋህ አማሮች መንገድ አመላካችነት በተመሙ ማይማን
የሀሽሽ ሰለባ ጦረኞችና በሕዝብ ኩርፊያ መሆኑን ልብ
ይሏል፡፡ ሌሎች ተጓዳኝ ሻጥሮችና ዓለም አቀፍ ሤራዎች …
ሳይዘነጉ፡፡ እውነት እንደፀሐይ ስለምታጥበረብር የምለው
ነገር የሚጎመዝዘው ቢኖር ልረዳው አልችልም – (አማርኛ
ተናጋሪ የሆናችሁ – በአማራነት የተፈረጃችሁ ወይም
ራሳችሁን የፈረጃችሁ ወገኖች በምንም መንገድ አትናደዱ –
በቀል የፈጣሪ እንጂ የሰው አይደለችምና ኅሊናችሁን ንጹሕ
አድርጋችሁ ወደላይ ጩኹ፤ ክፉ ብታስቡ ያ ክፋት ወደራሳችሁ
ይዞራልና እንዲያውም ክፉን ለሚያደርጉባችሁ ፍቅራችሁን
አሳዩዋቸው – አደራ)፡፡ እውነትን መናገር ሀሰትን ከመናገር
ቢከብድም ምንም ማድረግ አልችልም፡፡ በበኩሌ አህያ ጥሩ
አገልጋይ ስለሆነች ይህ ስም ሲበዛብኝ እንጂ አያንሰኝም፤
አይከፋኝምም፡፡ ስለዚህ ዕድሜ ለወያኔዎቹና – የጠቤን
ምህዳር ላስፋው ይሆን? አይ፣ ይቅርብኝ – ለማንኛውም ጥሩ
የዳቦ ስም አለኝ፡፡ ‹አንድ ጣትህን ወደሰው ስትቀስር ሦስቱ
ወዳንተ መዞራቸውን አስተውል› ይባላል፡፡ የኛንም ‹ቁስል›
ማሳየቱ ነውር አይደለም ከሚል የዋህነት ነው አለወትሮየ
እንዲህ የምል – በዚያ ላይ ዓለምሰገድ ብቻውን ‹ስለኛ›
መናገር አይገባውም – እኔም ‹ስለነሱ› ላግዘው፡፡ እርግጥ
ነው – ሁሉም እንደምንጭ ውኃ ኩልል ብሎ የሚጠራበት
ጊዜ ይመጣል – የእስከያኔውና የእስከዛሬው ድፍርስ ነበር፡፡
ከአሁን በኋላ ግን ሁኔታዎች እየከረሩ የሚሄዱበት ወቅት ላይ
የደረስን ይመስለኛል፡፡ ይህችን ሀገር እግዚአብሔር
ባይጠብቃት ኖሮ ይሄኔ ከሦርያም ብሰን ነበር፡፡ ፈጣሪ ጓዙን
ጠቅልሎ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳለ ማመን አለብን፡፡
ያልተላለቅነውና ውለን የምንገባው በኪነ ጥበቡ እንጂ
በወያኔ ቸርነትና ጥበቃ አይደለም፡፡ ለነገሩ ሰው በስንቱ
ሊበደል ይችላል?
ለማንኛውም ጥቂት ከፍ ሲል በጀመርነው ተጠየቅ መሠረት
በቀድሞ ዘመን የተሠራው መጥፎ ነገር ሁሉ የታሪክ ስህተት
ነውና ቀጣዩ የታሪክ ተረካቢ ነባሩን ስህተት አስተካክሎ
በፍትህ ይገዛል ብለን በጉጉት እንጠብቅ፡፡ ከ17 ዓመታት
የደርግ የግፍ አገዛዝ በኋላ በቆዬ የቦካ ቂም ክራሩን በአዲስ
የበቀል አንቺሆዬ ቃኝቶ ለሌላ የተነጣጠረ ዕልቂት ያላለመ
መንግሥት ጠበቅን እንበል፡፡ አልቀረም መጣ‹ልን›፡፡
ግንቦት 20 ቀን 1983ዓ.ም፡፡
ቀጣዩ የታሪክ ባቡር በትግሬዎች እጅ ወደቀ፡፡ ምን ተፈጸመ?
የ‹አማሮች› ስህተት ተደገመ ወይንስ ተስተካክሎ ዕንባ ታበሰ፣
የሚፈስ ደምስ ደረቀ? ‹አማራው› ያስለቀሳቸው ወገኖች
ጭቁኑን አማራ ጨምሮ አለፈላቸው? የታወጀላቸው ራስን
በራስ የማስተዳደር ዴሞክራሲያዊ ባህል ሠፈነላቸው? የዚያ
ሁሉ መስዋዕትነት ዋጋ ምን አመጣ? ለሌላ አዙሪት የሚዳርግ
ስህተት እየተሠራ ነው ወይንስ ፍትህ ሰፍኖ ሁሉንም ያማከለ
ልማት ተዘረጋ? ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ ተጀመረ
ወይንስ ተሠሩ የተባሉ ስህተቶች ታርመው ፍትህና ርትዕ
ነገሡ? ጥያቄውም መልሱም ከማንም የተሠወረ አይደለም፡፡
‹ተቀልዷል፣ ተቀልዷል፣ተቀልዷል› በሚል አዝማች አንዲት
ዘፋኝ ያቀነቀነችው ሥልት ትዝ አለኝ፡፡…
የሚመለከታችሁ ወገኖች በአስቸኳይ ከአማራ ራስ ውረዱ!!
‹አማራ› አጥፍቷል፤ እውነት ነው፡፡ አጠፉ የተባሉት አማሮች
ግን ብቻቸውን አልነበሩም፤ ዘመኑም እጅግ ሩቅ ነው፡፡
የመንግሥት ሥልጣን ይዛችኋል – ሌላው ወገናችሁ ብዙ
ጊዜ እናንተንና ፈጣሪን አንጋጥጦ ጠበቀ፡፡ በስቃይ እየኖረ
እንደክርስቶስ ኤሎሄ እያለ ነው፡፡ የጸሎቱ ዳፋ ግን ለማንም
ምሕረት የማይኖረው እንደሚሆን እንረዳ፡፡ እውነትን
እንነጋገር፡- የዘረኝነትን አጥር በአመዛዛኝ የዕውቀት ቁልፋቸው
ከፍተው ለጋራ ሕይወት ከሚታገሉ በጥቂት ሺዎች የሚገመቱ
የትግራይ ተወላጆች ውጪ አብዛኛው ትግራዋይ ለወያኔ
የማይራራ ልብ አለው ማለት ስለሚከብድ የሕዝቡ መራቆት
ይሰማንና ነገን ሳንጠብቅ የሚመርም ቢሆን መድሓኒት ገዝተን
ዛሬውኑ እንዋጥና ‹በኛ ይብቃ!› እንበል፤ ለልጆቻችን
መርገምት አናስተላልፍ፡፡ የማስተካከል ወርቃማ ዕድል
በበራችሁ ተኝታ ስትማጸናችሁ እናንተ ሳታስተውሏት ይሄውና
22 ዓመታት ላይመለሱ ነጎዱ፡፡ አታሞ እርግጥ ነው በሰው
እጅ ታምራለች – የማደናገር ዕዳው ሲይዟት ነው፡፡
በኢትዮጵያ ከሞላ ጎደል ሁሉም የሥልጣን ቦታዎች ላይ
አለችሎታቸውና አለዕውቀታቸው – በዘውጋዊ ታማኝነታቸው
ብቻ የተቀመጡ ሌሎችን ግን የሚያባርሩና አልፎ ተርፎም
በአሸባሪነት እየከሰሱ ወህኒ የሚያወርዱ የገዢው መደብ
አባላት ወደየኅሊናቸው በአፋጣኝ ይመለሱ፡፡ ጊዜ የለም፡፡
ፅዋው ሞልቷል፡፡ ከአሁን በኋላ ምርጫው ሁለት ነው፤ አንዱ
አካሄድን ማስተካከልና ልክ እንደደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ ዕርቅ
ማውረድ፡፡ ሁለተኛው የእናቴ መቀነት አሰናከለኝን መተውና
ወያኔዎች በድንቁርናቸውና በዕብሪታቸው ያበላሹት – ዐፈር
ላይ ጥለው አለመላው ያርመጠመጡት ዋልጌያዊ
የመንግሥት ሥልጣን አያያዝ የሚያመጣውን የማይቀር ዕዳ
ለመቀበል መዘጋጀት፡፡ ከዚያ በተረፈ “በምኒልክ የደነቆረ፣
‹ምኒልክ ይሙት› እያለ ሲምል ይኖራል” እንደሚባለው
የአማራን ስም እንደውዳሤ ማርያም ቀን ከሌት እየደገሙ
አበሳን ማብዛት የራሷን ምስል በመስትዋት ውስጥ ተመልክታ
‹አምላኬ ሆይ፣ እንኳንስ እንደዚህች ዓይነት አስጠሊታ ፍጡር
አላደረግኸኝ!› ብላ እንደጸለየችው ዝንጀሮ መሆን ነው፡፡ ጀሮ
ያለው ይስማ፤ልብ ያለው ልብ ይበል፡፡ ፀጉር ስንጠቃ
አርማጌዴዖንን አያስቀርም፡፡ ጉራና ትዕቢትም ወንዝ ቀርቶ
የደረቀ ፈፋን አያሻግርም – ሲያመጣው፡፡
ይህን የምለው አንዱ ጻዲቅ ሌላው ኃጥዕ ሆኖ አይደለም፡፡
ነገር ግን የእግዚአብሔር ሚዛን እንደሰው ሚዛን
ስለማይቀላምድ በሆነው ነገርና እየሆነ ባለው ነገር መካከል
ያለውን ልዩነት ተመልክተን የመጪውን ጊዜ ይዞታ ስንገምት
በአማራ ላይ የደረሰው ቅጣት ከወይራ ጥብጣብ ወይም
ከለበቅ የሚወዳደር እንጂ በአሁኖቹ ቀብራራ ገዢዎች ሊደርስ
ካለው ጋር በምንም መንገድ እንደማይቀራረብ ለመጠቆም
ነው – የነብርንና የሚዳቋን የ‹አሁን ብበላህ ምን እሆናለሁ?›
ምሣሌያዊ ብሂል አስታውሱ፤ ሁልጊዜ ጌትነትም የለም፤
በፋሲካ የገባች ገረድ ፍልሰታ እንደምትመጣ ካላወቀች ገልቱ
ናት – እርግጥ ነው ፋሲካና ፍልሰታ ርቀት አላቸው –
ቢሆንም … ፡፡ በበኩሌ ሁለት ነገር አስባለሁ – አንድም ያንን
የፍርድ ቀን ፈጣሪየ ባያሳየኝ፣ አንድም ያንን የፍርድ ቀን
ፈጣሪዬ አድርሶ ቢያሳየኝ፡፡ ምርጫው የርሱ ይሁንልኝ፡፡
ከአያያዝ ይቀደዳል፤ ከአነጋገር ይፈረዳል – ቀኑን እዩት ፤ ቀኑ
ደርሷል! የዘመኑን መቅረብ ለመረዳት ደግሞ በግድ ቆዳ
ታጥቆ አንበጣ እየበላ በበረሃ የሚሰብክ ሰው መጠበቅ
አይገባንም፡፡
የዘሩት መብቀሉ፣ የበቀለ መታጨዱና ተወቅቶ ጎተራ መግባቱ
አይቀርም፡፡ ሼክስፒር ‹ትልቅ ደግ ነገር ለመሥራት ትንሽ
መጥፎ ነገር መሥራት ምንም አይደለም› ይል ነበር አሉ፡፡
በኢትዮጵያ ያለው ተጨባጭ ሁኔታ ግን የስሙኒ ዶሮ
የሚሊዮን ብሩን የወርቅ ገመድ ይዛ እየጠፋች ተቸግረናል፡፡
የአንዲት ክፍለ ሀገር ጥቂት መኳንንትን ሁለንተናዊ ርሀብ
ለማስታገስና የጥቂት ሚሊዮን ዜጎችን ሥነ ልቦናዊ የገዢነት
እርካታ እውን ለማድረግ የተከፈለው መስዋዕትነትና
የወደመው ሀብትና ንብረት አሥራ አራቱንም የቀድሞ
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ግዛቶች ሕዝብ ቁጭ አድርጎ ለአሠርት
ዓመታት ይቀልብ ነበር፡፡ ነገር ግን የፊተኞቹም ሞኞች፣
የአሁኖቹም ለከት ያጡ ብልጦች ሆኑና በመካከሉ ሀገርና
ሕዝብ ለማያባራ የሲዖል እሳት ተዳርገው መቅኖ አጥተው
ቀሩ፡፡ ደግነቱ ግን ይህም ያልፋል፡፡
በዚያ ላይ ትልቁ ችግር የሆነብን ኅሊናን የሚሠቀጥጥ ውሸት
እየተለቀቀብን ፈረንጆቹ በ‹MC› (Mind Control)
በሳተላይት የተደገፉ ሥውር የአእምሮ መቆጣጠሪያ
ፕሮጄክቶቻቸው ዜጎቻቸውን በኤሌክትሮኒክስ ጨረሮች
እንደሚያነሆልሏቸው ሁሉ የኛ የገዢው መደብ ምሁራን
ተብዬዎችም እንዳቅሚቱ ያቺን የMC/PR የምትመስል
የሕዝብ ግንኙነት ሥራ መሥራታቸው ነው፡፡ ቂሎች ናቸው፡፡
በእንደዚህ ዓይነት የሞኝነት ሥራ ገብተው ሊዋረዱ
አይገባቸውም ነበር – የውርደትን ምንነት ቢያውቁ፡፡ ዝምታ
ማንን ገደለ? ምንም ሳይናገሩ የታሪክ ባቡር ወስዶ አንዱ
ሥርቻውስጥ እስኪቀረቅራቸው ድረስ ዕድል የሰጠቻቸውን
ሲሳይ ድምጻቸውን አጥፍተው እንደለመዱት እዬዘረፉ
ቢከፋፈሉ ማን ምን ያደርጋቸዋል? ልፉ ብሏቸው እንጂ ዋሹ
አልዋሹ፣ የፈጠራ ድርሰት ጻፉ አልጻፉ ያላሰቧት ዕድል
እንደሆነች በደጃቸው ከትማለችና የመጥፎ ሥራቸው የዞረ
ድምር መቅሰፍቱን እስኪያዘንብባቸው ድረስ አርፈው
መቀመጥ ይችላሉ፡፡ መንቀዥቀዥ ሳያስፈልጋቸው አሁን
እያደረጉ ያሉትን ሁሉ እያደረጉ መኖር ‹ጉልበታቸው›
የሰጣቸው መብታቸው ነው፡፡ ናፖሊዮንንና ሂትለርን የመሰሉ
አባ ጉልቤዎችም ብለዋል:- “Mighty is right”.
አስተዋይ ሰው ከቆመው ብቻ ሣይሆን ከወደቀውና
ከተቀመጠውም ብዙ ይማራል፡፡ ስህተትን በስህተት ቢደግም
ራሱም ቀኑን ጠብቆ እንደሚወድቅ ይገነዘባል፡፡ ትናንትን ከዛሬ፣
ዛሬንም ከነገ በማገናዘብ ለአለውና ለመጪው ትውልድ
መልካም ነገሮችን ቀይሶ ያልፋል፡፡ እናም ወያኔዎች ወድቋል፤
ተቀብሯል ያሉት አማራ እንግዲያውስ ለምን ወደቀ? ብለው
አዙረው ማየት ነበረባቸው እንጂ በ‹ብጥለው ገለበጠኝ›
የመሠሪነት ባሕርይ ታሪክ አፍ አውጥቶ እስኪታዘባቸው ድረስ
እንዲህ ባልተጃጃሉ ነበር፡፡ ሌላውን ሁሉ ትተን ጣልነው
ያሉትን የጣሉት በኢፍትሃዊነት ተፈጥሮው ስለተጓዘ እንደሆነ
አምነው ሳይሆን ለሀብትና ለሥልጣን በነበራቸው ጉጉት
ያስመስልባቸዋል፡፡ ይሄ ሁሉ የስም ማጥፋት ዘመቻም
ስለፍትህ በመጨነቅ ሳይሆን ለግላዊ ጥቅምና ለሥልጣን
ጥም እርካታ መሆኑን ያሳብቅባቸዋል፡፡
ኢፍትሃዊነት እነሱን ወልዶና አሳድጎ ራሱን ኢፍትሃዊነትን
ካጠፋ የነሱ ኢፍትሃዊነት ሌላ አካል ወልዶና አሳድጎ የነሱን
መረን የለቀቀ ኢፍትሃዊ አገዛዝ ሊያጠፋ እንደሚችል እንዴት
ሊገነዘቡ አይችሉም? ምን ዓይነት ተፈጥሯዊ ‹intrinsically
in-built› ድንቁርና ይሆን እነዚህን ወንድሞቻችንን
የተጣባቸው? አፄ ኃ/ሥላሴ ለምን ወደቁ? ደርግ ለምን
ወደቀ? ሂትለር ለምን ተዋርዶ ሞተ? ጋዳፊ ከ42 ዓመታት
በኋላ ከነባረያ ፈንጋይ ሥርዓቱ ለምን ተገረሠሠ? የደቡብ
አፍሪካ የጥቂቶች የአፓርታይድ አገዛዝ ብዙ ጥፋትና ውድመት
ካደረሰ በኋላም ቢሆን ለምን ወደቀ? (ነጮቹ ከጠቅላላው
ሕዝብ 6 በመቶ እንደሆኑ ይነገራል) ሆስኒ ሙባረክ ለምን
ተዋረደ? ጨቋኙ አላዊት ባሽር አላሳድ ለምን ሰሞኑን
ይወድቃል? … እነዚህ የትግሬ ገዢዎች ከዚህ ሁሉ ዓለም
አቀፍ የአሁንና የጥንት ኹነቶች ትምህርት ሊቀስሙ
ያልቻሉበትና በመዥገራዊ የዘረኝነት አባዜ እንደተለከፉ
የማርጀታቸው ምክንያት ምን ሊሆን እንደሚችል ሲታሰብ
በእጅጉ ይገርማል፡፡ ለመሆኑ ‹የክፋት ዕድሜ እስከ ስንት
ሊሆን ይችላል? የዱባ ጥጋብስ ዕድሜው ስንት ነው – ምን
ያህል ዳገቶችንስ ያስወጣል? …› ብለው ጥቂት ማሰላሰል
እንዴት አቃታቸው? ታሞ የተነሣ ፈጣሪን ረሳ ማለት እንግዲህ
እዚህ ላይ ነው፡፡ ይወቁት – አማራ በቡድንና በማኅበረሰብ
ደረጃ የማንም ጠላት አልነበረም፤አይደለም፤አይሆንምም፡፡
ግን ግን በስሙ የነገዱ ሆዳምና ራስ ወዳድ አማሮችና ሌሎች
ዘውጎችም ነበሩ፡፡ ሴትዮዋ “ዕድሌ ሆኖ ፈሴ ይሸታል”
እንዳለችው ባለቤት የታጣላቸው ታሪካዊ ስህተቶች ሳይቀሩ
በአማራው እየተላከኩ ይህን ምሥኪን ሕዝብ በኢትዮጵያና
በ‹ዓለማቀፉ ማኅበረሰብ› ዘንድ እንዲጠላ ሙከራ ይደረጋል
እንጂ አሁን ቆም ብለን ወደኋላ ብናይ አማራ ሠራው የተባለው
ነውር የአሁኑ የብዔልዘቡል መንግሥት ከሠራውና እየሠራው
ካለው ነውር ጋር ሲወዳደር ልዩነቱ በአንድ ኩሬና ከአሥር
በላይ በሚገመቱ ውቅያኖሦች የሚመሰል ነው፡፡ ለአፍ አቀበት
ስለሌለው ግን ጆሮ አይሰማው የለምና የእምዬን ወደአብዬ
ሲያላክኩ አፋችንን በሀፍረት እየተመተምን መስማትን
ቀጥለናል – እስከ አንድ ቀን ድረስ፡፡

“#From the horse’s mouth” ትሉ የለም እናንተስ


“#From the horse’s mouth” ትሉ የለም እናንተስ
#እውነትን_በግልጥ_የማይናገር_ሰው_ሁከትን_ይፈጥራል፣
በግልጥ የሚነቅፍ ግን ሰላም እንዲገኝ ያደርጋል፡፡የደግ ሰው ንግግር የሕይወት ምንጭ ነው፣የክፉ ሰው ንግግር ግን የዐመፅ መሸፈኛ ነው፡፡ጥላቻ ሁከትን ያነሣሣል፣ፍቅር ግን በደልን ሁሉ ዐይታ በይቅርታ ታልፋለች፡፡እውነትን በምትናገርበት ጊዜ ቅን ፍርድ ታደርጋለህ፣ሀሰት ግን ፍርድ እንዲጓደል ያደርጋል፡፡ያለ ጥንቃቄ የተነገረ ቃል እንደሰይፍ ያቆስላል፣በጥበብ የተነገረ ቃል ግን ይፈውሳል፡፡የሀሰት ዕድሜ አጭር ነው፣እውነት ግን ለዘላለም ትኖራለች፡፡
#(መጽሐፈምሳሌ_ምዕ. 10 (10 – 12) – 12 (17-19)
A lie is an abomination unto the Lord and avery present help in trouble. Adlai Stevenson
(1900 – 1965)
It is always the best policy to tell the truth,unless, of course, you are an exceptionally good liar. Jerome K. Jerome (1859 – 1927)
 “#From the horse’s mouth” ትሉ የለም እናንተስ
የመጽሐፉ ዋነኛ ዓላማ ከመነሻው እስከመድረሻው የሚያጠነጥነው በተስኪያን እንደገባች ውሻ #አማራን እንዳይሸጥ እንዳይለወጥ አድርጎ በተገኘ ምናባዊመሣሪያ ሁሉ መቀጥቀጥ ነው – ፍርጃ እኮ ነው እናንተዬ፤አሁንስ ይሄ አማራ የሚባል ብሔር ባይፈጠር በተሻለው፤የጠብ ያለሽ በዳቦ ልክፍት የተጠናወተው ሁሉ አፍ ማሟሻናየጭቃ ጅራፍ ብዕር የስድብ መለማመጃ ሆኖ ይቅር እንዴ?ባይቆጭ ያንገበግብ ይባላል፡፡  በአንድ ሀገር ዜጎች መካከል እንዲህ ዓይነት አሣዛኝ ሁኔታ መፈጠሩ ለደግ አይደለምና ከአሁኑ ይልቅ የወደፊቱ እጅግ በጣም አሳሳቢ ነው፡፡ 
በዚህ አጋጣሚ መግለጽ የምፈልገው ነገር እውነትን እንዳለች እንድንመለከት እግዚአብሔር ፈጣሪያችን ሁላችንንም ልቦናና ብርታትን እንዲሰጠን ነው፡፡ እርግጥ ነው ሕንዳዊው ደራሲ ናራያና እንዳለው እውነት እንደጠራራ ፀሐይ ዐይንን ታጥበረብራለች፤ ብዙዎቻችን በቀጥታ ልናያት አይቻለንም፡፡ እውነትን ደፍሮ መጋፈጥ የሚቻለው ሰው ብርቱነው፡፡ የእውነት ጦር ከማንኛውም ሰው ሠራሽ መሣሪያየበለጠ ኅሊናን ይወጋል፡፡ ስለዚህም ነው በርካታዎቻችን ይህችን እውነት አጥብቀን ስንሸሽ የምንስተዋለው፡፡ ሁሉም ሰው የኅሊናው ባለቤት ቢሆን የምድራችን ቅርጽ ከአሁኑ እጅግ ባማረ ሁኔታ የተለዬ በሆነ ነበር፡፡ ግን ዕድሜ ለዚህ በተመሳሳይ ወቅት እየጠገበ ለሚርበው ሆድ ለጥቅም ሲባል እውነት እንደክርስቶስ አላበሳዋ እየተወገረች፣ ሀሰት ?ንግሥናንና ግርማ ሞገስን እያገኘች ዓለማችን ከምንጊዜውም በላይ በሚያስደነግጥ የጥፋት ማዕበል እየተናጠች ልትገኝ ችላለች?፡፡
እውነትን አለመናገር አንድ ነገር ነው – ዝም ማለት፡፡ እውነትን
ለመደበቅ መጣርም አንድ ነገር ነው – ማስተባበል፡፡የፈጠጠ እውነትን መካድና በፈጠራ የልቦለድ ሥራ መራር እውነትን በውሸት ቡልኮ ለመሸፈን መሞከር ግን ሰው የመሆንን ሥነ ተፈጥሮ የሚፈታተን ታላቅ ሰብኣዊና ሞራላዊ ኪሣራ ነው፡፡ የዚያን መጽሐፍ ደራሲ ያገኘሁት እንግዲህ ከሰውነት በታች ወርዶ፣ ከቀሪው የእንስሳት ዓለምም እጅግዘቅጦ በሚያሳዝን የኅልውና ደረጃ ውስጥ ወድቆ በዓሣማጋጣ የዘረኝነት አረንቋ ውስጥ ሲማስን ነው – ስንት ዓመትሊኖር? ሕወሓትንስ በዚህ ውሸቱ ጠቅሞ ስንት ዓመትሊያኖር? ከንቱነት ነው – እንደመጽሐፉ ንፋስን የመከተልያህል የከንቱ ከንቱ ነው የዚያ ሰው ልፋቱ፡፡ ወገኖቼ ናቸውየሚላቸውን ቢያድላቸው ደግሞ የኛም ወገኖች ሊሆኑይቻላቸው የነበሩ ሳይፈጠሩ ቢቀሩ የሚሻላቸው ወገኖችንወንጀልና የግፍ ቁልል ለመሸፈን የሚያደርገው ጥረት ራሱንአጋልጦ የወንጀላቸው ተባባሪ ሊሆን እንደሚችልእስክንጠራጠር ድረስ በዘረኝነት የጠባብነት ቁጢት ተተብትቦ ወያኔዎች ያልሆኑትን እንደሆኑ ለማሳመን ቆላ ደጋ መራወጡን ስናይ የምናዝነው ለኛ ለግፉኣኑ ብቻ ሳይሆን ለርሱና ለነርሱ ሳይሞቱ ለሞቱት ወገኖቻችንም ጭምር ነው፡፡ አንዳንዴ
ሟችም ለገዳይ ማዘኑ የነበረና ተገቢም ነው፡፡ የሚገድልና
የሚዋሽ ሰው ወድዶ አይደለምና እውነትም ይበልጥ ማዘን
በሀሰት ሚዛን እየመዘነ፣ በሀሰተኛ ምላስ እየፈረደ ንጹሓንን
ለሚያጠፋ ነው፡፡ ሰው በጤናው ሰውን አይገድልም፤ ሰው በጤናው አይዋሽም፤ ሰው በጤናው መጥፎ ድርጊት ውስጥ
አይገባም፡፡ አንድ ሰው የሆነ ሥነ አእምሮኣዊ ወይም ሥነ
ልቦናዊ ችግር ውስጥ ካልተዘፈቀ በስተቀር ከመሬት ተነስቶ ሰው አይዘልፍም ወይም አይገድልም፡፡ ይህ ዓይነቱ ሰው ሕክምና እንዲያገኝና ፈጣሪ ከእሥራቱ እንዲፈታው ቢጸለይለት በረከት ያስገኛል እንጂ ክፋት የለውም፡፡
ስለዚህም ዐውቀውም ይሁን ሳውቁ ለጠፉ ወንድምና
እህቶቻችን በጋራ እንጸልይላቸው፤ ልል የምችለው ቀዳሚ ነገር ይህንን ነው፡፡
‹ባልዋሽ፣ባልገድል፣ዝም ብል፣… ይህን ወይ ያን ጥቅምና ሥልጣን ላጣ እችላለሁ፡፡› ብሎ የሚያስብም የምኞቱ ባሪያ
ሆኖ ወደ ወንጀል ዓለም እየገባ ነውና ሊታዘንለትና ሊጸለይለት
ይገባል፡፡ እንጂ በመሠረቱማ የሰው ልጅ ሁሉ አንድ ነው –
ልዩነታችን ጥፋታችንና ልማታችን፡፡ በጥፋታችን እንጠፋፋለን፤
በልማታችን በሀብት እንበለጽጋለን፤በአስተሳሰብና
በአመለካከትም እናድጋለን፡፡ ይህን ዕድል የሚያሳጡንን
ታዲያን በጋራ እንታገላቸው፡፡ በዘረኝነት መታወር፣ በትምክህት
መወጠር፣በዕብሪት መጀነን፣ በዕውቀት መደኽየት፣ በራስ
ወዳድነት ልክፍት መጠፍነግ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡
ክርስቶስ “የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው” ያለው
በገንዘብና በሥልጣን ፍቅር ላበዱ ለዚያኛው ዘመን
አይሁዳውያን ወያኔዎች ብቻ አይደለም፡፡ ለተገነዘበው ለሁሉም ዘመን የሚሠራ ታላቅ አስተምህሮ አለው፡፡ የሞት ፈጣሪ በፍጡራኑ ሲሰቃይ፣ ሲገረፍ፣ ምራቅ እየተተፋበትና በእሾህ አክሊል እየተፌዘበት እስከስቅላት ደርሶ የሞትን ጽዋ ሲጎነጭ እነዚያን ወያኔዎች ቀርቶ ዓለምን ከናካቴው ሊያጠፋ የሚችል ኃይል አጥቶ አልነበረም፡፡ እንደመጽሐፉ ያ ሁሉ የሆነው ታዲያ እንዲሆን ግድ ስለነበረ ነው፡፡ ይህም ዘመን እንዲያልፍ ግድ ነውና በወያኔዎች ዐይን ያወጣ የብልግናሥራ ብዙም አንደነቅ፡፡ በቅድመ ትንበያ (predestination)ለምናምን አንዳንድ ወገኖች ይህ ሁሉ አብራቅዳብራ እንደሚከሰት – ወቅቱን በትክክል ባናውቅም – የቀደመ ግንዘቤ ነበረን፡፡ አይሆኑም የሚባሉ ነገሮች የሚሆኑበት አጋጣሚ ሞልቷል፡፡ በድምሩ ከ18ሚ. የዓለም ሕዝብ የወጡ በጣ የሚቆጠሩ ፅዮናውያን የሰባት ቢሊዮንን ሕዝብ ዕጣፋንታ፣ በድምሩ ከአምስት ሚሊዮን ሕዝብ የወጡ ‹ጥቂት›የትግሬ ገዢዎች የ110 ሚሊዮን ሕዝብ ዕጣ ፋንታ ይወስናሉብሎ በሰው ልጅ አእምሮ ማሰብ የሚቻል አይደለም ነበር ፡፡ ነገርግን ይሁን ያለው ከመሆን አይዘልምና እየተገረሙ የዓለምን አካሄድ በትዝብት ከመቃኘት በስተቀር ምንም ማድረግ አይቻለንም፡፡ በብሂልህ “ቀን የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል” ትል የለም? ወደህ ተሰደድህ? ወደህ ትራባለህ?
ወደህ ሀገር አልባ ትሆናለህ? አብዛኞቹ የዓለም ቢሌነሮች
እነማን ናቸው? የዓለምን ትልቅ ሥልጣን በእጅ አዙርና
በቀጥታ የተቆጣጠሩት እነማን ናቸው? ወዴት እየነዱህ ነው?
ወደ ጥፋ ወይንስ ወደ ልዕልና? በኢትዮጵያስ ያንን ዓለም
አቀፍ ነፀብራቅ ቁልጭ ብሎ እያየኸው አይደለምን? ዘመኑ
የጥቂቶች ነው ወዳጄ ልቤ፡፡ ሁሉን ቢያወሩት ሆድ ባዶይቀራል፡፡
እንደውነቱ ውሸት የሚናገር ሰው በሥቃይ ውስጥ ያለ ነው፡፡
እውነትን የሚናገር ሰው ግን በሥቃይ ውስጥ ላለመኖር
የቆረጠ ሰው ነው፡፡ እውነትን በመናገር ብዙ ነገር እናጣለን፡፡
ከቅርብ ጓደኛና ዘመድ ጀምሮ የምናጣው ብዙ ነገር ነው –
በዓለማዊ አስተሳሰ መብል፣መጠጥ፣ድሎት፣ሥልጣን፣ፍቅረኛንና የትዳር አጣማሪን ሳይቀር ብዙ ነገሮችን ልናጣ እንችላለን፡፡ ሀሰት
መታወቂያዋ በሆነ ዓለም ውስጥ ስንኖር እውነትን ለመናገር
ከቆረጥን እንደዕብድ ልንቆጠርና በውግዘት ከአካባቢና
ከማኅበረሰብም ጭምር ልንገለል እንችላለን – ያኔ ሃይማኖት፣ ባህል፣ ወግና ልማድ የተባለው ይበልጡን በውሸት የተቃኘው ማኅበራዊ ሥርዓት ሁሉ ይከዳህና ከሕገ ወጦቹ ጋር ሲወግንብህ መግቢያ ቀዳዳ ታጣለህ – ደግሞም
ያኔ የምትኖርባት ዓለም የሀሰት እንጂ የእውነት መገለጫ
እንዳልሆነች ትረዳና አንድም ታብዳለህ አንድም ትመንናለህ
አለዚያም በ‹ኩኑ ከማሆሙ› ሥጋዊ መርህ የቆሻሻው ዓለም
ባልደረባ ሆነህ አንተም በተራህ እንዳሻህ ትመላለስበታለህ፡፡
እከክ የሰጠ ጥፍር አይነሳምና ምርጫዎች አሉህ፡፡
ለሚያምኑበት እውነት መርዝን በድፍረት የጨለጡና የድንጋይ
ውርጅብኝ በውዱ ገላቸው ያስተናገዱ እንዲሁም በስቅላት
ያሸለቡ ሞልተዋል – ዕንቁን የላይና የታች ልጅ ክርስቶስን
ጨምሮ፡፡ በጥቃቅን የሃሳብ ልዩነት – ለምሳሌ በመሬት ቅርጽ
– ሳይቀር በሞት የተቀጡ አሉ – አሁንም ለቆሙለት እውነት
ሲሉ፡፡ ካለመስዋዕትነት ድል እንደሌለ ተገንዘበን በእውነት
መንገድ ከተጓዝን በመጨረሻው እውነት ራሷ ትክሰናለች –
አለበለዚያ ትከሰናለች፡፡
ሀሰት የሚናገር ሰው እውነት የሌለው ወይም የሚታወቅን
እውነት በመናገሩ ምክንያት አንዳች ነገር አጣለሁ ብሎ
የሚያምን ሰው ነው ማለት ይቻላል፡፡ ወያኔዎችና እበላ ባይ
ወይም የዓላማ ደጋፊ ጸሐፊያነ ትዕዛዞቻቸው የይሉኝታን ገመድ
በጣጥሰው ጥለው ነጭ ውሸቶችን በመክተብ ሥራ ላይ
የተጠመዱበት ምክንያት ካልዋሹ በስተቀር የያዙትን ቦታ
እንደሚለቁ ስለሚያውቁ ነው፡፡ የሚይዙት ካርድ ሁሉ
ያሟልጫል፡- ዴሞክራሲ ቢሉ ንዑሳን በመሆናቸውና
ከጥንትም በደምና በአጥንት ተረማምደው በመምጣታቸው
ምናልባትና በዛ ቢባል ከ6 በመቶ የሀገሪቱ ሕዝብ የበለጠ
የሚመርጣቸው እንደሌለ ያውቃሉና በዚያ ድጋፍ
በማይገኝበት የዴሞክራሲ መንገድ ሊጓዙ አያስቡትም –
ይህንንም እውነት ጃዝ ብለው ያሠማሯቸው ወገኖች
ያውቃሉ፣ በተጨባጭም አይተውታል፡፡ ጨቋኝም ሆነው
እንደቀደምቱ ነገሥታትና ወታደራዊው መንግሥት ጉልበትንና
ዘዴን ተጠቅመው እንዳይቀጥሉ ከዜጎች ብቻ ሳይሆን
ከመሬቱና ከዛፍ ቅጠሉ ተጣልተዋልና ያም አያዋጣም፡ ቀጠቀጣቸው
ብሔርን ከብሔር ፣ ቡድንን ከቡድን፣ ሰውን ከሰው፣ባልን
ከሚስት … እያናከሱ ዕድሜን መቀጠሉም ከአሁን በኋላ
የሚሠራ አይመስልም ትራፊ ወያኔዎች ፡፡ ያላቸው ብቸኛ አማራጭ በኃይል መረግጥ ነበር አልሆነም በውሸት ወሬ አደንቁሮ የተቻላቸውን ያህል ርቀት መጓዝ ነው፡፡ ስለወያኔዎች የብዙዎቻችን እውነት ይሄው ይመስለኛል፡፡
ይህ ዓለምሰገድ አሰፋ በተባለ ግለሰብ የተጻፈ ጥናታዊ
የተባለ መጽሐፍ የአማርኛ ተናጋሪውን ማኅበረሰብ አፈር ድሜ
ለማስጋጥና የሰሜኑን ሕዝብ በተለይም የኤርትራንና ትግራይን
የትግርኛ ቋንቋ ተናጋሪ ማኅበረሰብ በታሪክም በሥነ ልቦናም
በሃይማኖትም ያላቸውን ነባር ትስስር አጉልቶ በማውጣት
ከሌሎች የኢትዮጵያ ዜጎች ይልቅ እኚህ ወንድሞቻችንና
እህቶቻችን ጥንት የነበራቸውንና አሁን ሊኖራቸው የሚገባውን
የበላይነትና ሥልጣኔያዊ ገናናነት ለማሳየት ያደረገው ጥረት
ከፍተኛ ነው(በእርሱ ጥናት መሠረት ከድላቸው በኋላ ጥብቅ
የነበረው የግንኙነት ፈትል በመላላቱ ሳቢያ ትግራይ
በኢትዮጵያዊነት ስትጸና ከመረብ ማዶ ያለው ግዛት
በኤርትራነቱ እንደፀና በፀፀት መሰል ቃና ይገልጻል)፡፡ ቀጣዩን
እንይ፡-
Once in the seat of power in Addis Ababa, the
ethnic card is being aborted at a fast rate to
such an extent that even the Tigrayan features
of the regime are fading almost completely. A
new national army with no ethnic character has
been created. Except for the premiership and
foreign ministry, all cabinet posts are held by
non-Tigrayans. Even key posts such as
defense, judiciary, and police are held by non-
Tigrayans. In other words, the rational political
actors led a costly ethnic nationalist war in
Tigray without being ethnic nationalists
themselves. For the Tigrayan rational actors,
therefore, Marxism was their raison d’etre and
ethnic rationalism their means to an end. And
ethnic nationalism was a politics of power.
ተዛማጅ ትርጉም፡- [ሕወሓቶች] አዲስ አበባን ከተቆጣጠሩ
ከ1983ዓ.ም በኋላ በትግሉ ዘመን ይጠቀሙበት የነበረው
የጠባብ ብሔርተኝነት የትግል ሥልት በኅብረ ብሔራዊ
የአንዲት ሀገር ሉዓላዊ ስሜት ወዲያው በፍጥነት በመተካቱ
በመንግሥት መዋቅሩ ውስጥ ‹ለመሆኑ በዚህ መንግሥት
ውስጥ ትግሬ ሥልጣን ላይ አለ እንዴ?› እስኪባል ድረስ
የኢትዮጵያ መንግሥት ከትግሬዎች ተፅዕኖ ሙሉ በሙሉ ነጻ
ወጣ (ከ1983ዓ.ም በኋላ!)፡፡ ዘውገኝነት ያልተንፀባረቀበት
ብሔራዊ የመከላከያ ጦርም በጎሣ ተዋፅዖ ሣይሆን በብቃት
መለኪያ መሥፈርት መሠረት ተመሠረተ፡፡ ከጠቅላይ
ሚኒስትርና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቦታዎች በስተቀር
ሁሉም የካቢኔ ሚኒስትሮች ቦታዎች ትግሬ ባልሆኑ ዜጎች
ተያዙ፡፡ [Please feel free to laugh, guys!] ሌላው
ቀርቶ አሸናፊ አማፂ ማንንም አምኖ የማይሰጣቸው
የመከላከያ፣ የፍትህና የፖሊስ ዕዞች በሙሉ ትግሬ ያልሆኑ
ዜጎች እንዲይዟቸው ተደረጉ፡፡ በሌላ አባባል ሕወሓቶች
በተፈጥሯቸው የሌለባቸውን የጎሠኝነት ወይም የጠባብ
ብሔርተኝነት ባሕርይ እንደጊዜያዊ ሥልት በመጠቀም
ትግላቸውን በከፍተኛ መስዋዕትነት ከግብ ካደረሱ በኋላ
ሥልጣኑን ላልታገሉ ዜጎች አስረከቡ(ና እነሱ ባዶኣቸውን ቀሩ
– ሣቅ/ሣቂ ፤ ዛሬና አሁን ያልሣቅን መቼ ልንስቅ ጎበዝ?)፡፡
ስለዚህም ለትግራውያኑ ተጋዳላዮች ለእውነተኛ የትግላቸው
ጅማሮ ዋና አመክንዮ ማርክሲዝም ሆኖ እንደመታገያ ሥልት
ግን ጠባብ ብሔርተኝነትን ወይም ዘውገኝነትን ተጠቀሙበት
(እንጂ እነሱማ ኧረ ንሽ እቴ! ዘውገኛነት በሉት ጎጠኝነት
አሊያም ነፍጠኝነት ሲያልፉ አይነኳቸውም፡፡) እናም ሕወሓቶች
ጠባብ ብሔርተኝነትን ለሕዝባዊ ዴሞክራሲያዊ የሥልጣን
ማረጋገጫነት ተገለገሉበት እንጂ በተፈጥሯዊ ባሕርያቸው
ዴሞክራቶች ናቸው፡፡
መንግሥቱ ኃ/ማርያምን በሁለት ውሸቶቹ ዘወትር
አስታውሰዋለሁ – “እውን አሁን ደርግ አለ?” አንድ በሉ፤ “እኔ
እንኳንስ ሰው ትንኝ አልገደልኩም!” ሁለት በሉ ( በነገራችን
ላይ ከደቂቃዎች በፊት ‘Talk to Aljazeera’ ላይ
በእንግድነት የቀረበ ኑር ሚሷሪ የተባለ አንድ ፊሊፒናዊ
የቀድሞ አማፂ ቡድን መሪ ጋዜጠኛዋ ‹ራስህ ሰው ገድለህ
ታውቃለህ ወይ?› ብላ ስትጠይቀው ‹እንኳን ሰው ጉንዳንም
ገድዬ አላውቅ› ብሎ ሲመልስላት መንግሥቱ ፊቴ ላይ ድቅን
አለብኝ – ሰውዬው ውሸታም ነው ለማለት ፈልጌ ግን
አይደለም – ስለማላውቀው፡፡) መንግሥቱንና ወያኔን መሰል
አምባገነኖች በአደባባይ የሚያደርጉትን ሁሉ ‹ዐይኔን ግምባር
ያ’ርገው› ብለው ሽምጥጥ ማድረግ የባህርይ ስጦታቸው
ነው፡፡ ኢትዮጵያ ባላት የተመናመነ ኢኮኖሚ ያስተማረችው፣
በእናቱ የጭንቅ ቀንም በፈለገችው ጊዜ የደረሰላት ይህ
‹ምሁር› የሚለውን እንቶ ፈንቶ ‹እውነት ነው፤ ውሸት ነው›
ብሎ መከራከር ጉንጭን ማልፋትና በጊዜም መቀለድ ነው፡፡
ጽሑፉ ራሱ ብዙ ይናገራልና፡፡ እዚህ ላይ ከመጽሐፉ ብዙ
መጥቀስ በተቻለ፤ ግን ይብስ ሆድ ማስባስ ነው፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ ‹በሀሰት አትመስክር፤ የባልንጀራህን
የጎረቤትህንም ገንዘብና ሚስቱንም አትመኝ፤
አትስረቅ፣ጓደኛህን እንደራስህ ውደድ፣ … › ይላል፡፡
የዓለምሰገድ ሃይማኖት ክርስትና ነው ብዬ ለማመን
እቸገራለሁ፡፡ በእስልምናም ‹ዋሽ› የሚል ቁርኣናዊ ጥቅስ
ይኖራል ብዬ ስለማልገምት ሙስሊም አይሆንም ባይ ነኝ፡፡
በአይሁድ ሃይማኖትም እንዲሁ ውሸትን የሚያበረታታ
የታልሙድም ይሁን የታናክ ወይም የቶራ ጥቅስ ይኖራል
የሚል ሃሳብ የለኝም፡፡ የዚህ ሰውዬ እምነት እንግዲህ –
እርሱ ተቀበለውም አልተቀበለውም – ምናልባት በማንኛውም
መንገድ በ‹የትም ፍጪው ዱቄቱን አምጪው›ም በሉት
በ‹The end justifies the means.› የሥጋ
ፍላጎቶቻቸውን ለማርካት ምንም ነገር ከማድረግ ወደኋላ
ከማይሉት የቤተ ሣጥናኤል (Church of Satan)
አምላኪዎች ጋር የሚመሳሰል ወይም የሚነባበር መሆን
አለበት – ሊያውም ከነሱም መካከል የ‹አትድረሱብን
አንደርስባችሁም› ዓይነት የመከባበር መርህ የሚከተሉ
‹ጨዋዎች› አሉ፡፡ አንድ ኢአማኒ(ኤቲይስት) ጓደኛ አለኝ –
እንዲያውም ከአንድ በላይ፡፡ በሞራሉና በማኅበራዊ ግንኙነቱ
በጣም ጨዋና ሰውን በቸገረው የሚረዳ ደግ ነው –
altruist፡፡ ሃይማኖት የለኝም ብሎ አይዋሽም አይቀጥፍም፡፡
ጽድቅና ኩነኔ የሉም ብሎ ማመኑ ልክ እንደዚህ ሰውዬ
ቆርጠህ ቀጥል የሆነ ውሸታም እንዲሆን አላደረገውም፡፡
የዚህ ሰውዬ ውሸት ግን የተለዬ ነው፡፡ ፍላጎቱ ግልጽ ነው –
ልክ እንደ‹ፕሮፌሰር› ክንፈ አብርሃም የትግራዩ ገዢ መደብ
በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ያሳረፈውንና እያሣረፈ ያለውን
የማይፋቅ ጠባሳ በዓይጥ ምሥክር ድንቢጥ የሀሰት
ምሥክርነት ጽድቅና ለማሰጠት ነው፡፡ እውነቱን ከፈጣሪ
ቀጥሎ ዓለምና የኢትዮጵያ ሕዝብ እያወቀው ለመዋሸት
ይህን ያህል ርቀት መጓዝ ከትዝብት ሌላ እንደማይኖር እነዚህ
ሀሰተኛ የዲያብሎስ አሽከሮች ሊረዱት በተገባቸው ነበር፡፡ ግን
ያሳዝናል ኅሊናቸው በዘረኝነት ልክፍት የታወረ በመሆኑ
እውነት ታጥበረብራቸዋለችና የሚሠሩት ህፀፅ ሊታያቸው
አልቻለም፡፡ ዛሬ የነጻነት ጎሕ ሲቀድ ልጆቻቸውና የልጅ
ልጆቻው ሲያፍሩበት በአሳቻ ቦታ ተጥሎ ውሻና እሪያ
የሚሸናት አፅማቸው እንደሚታዘባቸው መገንዘብ ነበረባቸው፡፡
እዘህ ላይ ማለት የምፈልገው ነገር የቀድሞ መንግሥታት
በነዓለምሰገድ ሥሌት ምንም ይባሉ ምን፣ ምንም ይሁኑ ምን
የሠሩት ስህተት አሁን ለሚሠራው ሌላ ስህተት መሠረትና
ድጋፍ ሊሆን እንደማይችል ማወቅ የሚገባን መሆኑን ነው፡፡
ዱሮ ዘመኑ የዕውቀት አልነበረም እንበልና የዱሮውን ስህተት
አምነን እንቀበል፡፡ “Every argument has two sides.”
ከሚለው ማለፊያ ነጥብ አኳያ የታሪክ አጻጻፍ ግነትም
ግድፈትም ሊኖረው መቻሉን በታሳቢነት ይዘን ዓለምሰገድም
ሆነ መሰል ፀረ – አማራና በተያያዥነትም ፀረ-ኢትዮጵያ ጥናት
አጥኚዎች በአማራው ‹ገዢ መደብ› ላይ የሚደፈድፉት
ኃጢያት እውነት እንደሆነ በሙሉ ልብ እንቀበልላቸው፡፡
እንዲያም አመንንላቸውና አማራ ትግሬን ጨቁኗል፤ ትግራይንና
ኤርትራን ዘርፎ ጎንደርንና ሸዋን፣ ጎጃምንና ወሎን ፋብሪካ
በፋብሪካ፣ ትምህርት ቤት በትምህርት ቤት፣ ዩኒቨርስቲ
በዩኒቨርስቲ፣ አስፋልት በአስፋልት፣… አድርጓል – ይሁን ብለን
እንመን – ማመን አይገድም፡፡ በሌላም በኩል በማወቅ
ወይም ባለማወቅ ብዙ የጭካኔና የአረመኔ ተግባር የፈጸሙ
አማሮች ነበሩ፣ አሁንም በአስተሳሰባቸው ከሞቱት በላይ
ከቆሙት በታች የሆኑ ከወያኔዎች የማይሻሉ ከንቱ አማሮች
ሊኖሩ እንደሚችሉ እንመን፤ እናምናለንም፡፡ የሀገር ግንባታና
ልማዳዊ የግዛት አስተዳደር ጉዳይ ሂደታዊ ነውና በተለይ
በዱሮ ዘመን ጥፋት አይኖርም ብሎ ማሰብ ሞኝነት ነው –
እነጋሪባልዲም 38 ብጥስጣሽ የጣሊያን ግዛቶችን
አስተባብረው ነው ታላቅ ሀገር የፈጠሩት፡፡ ይህ ክስተት
ለኢትዮጵያ ሲሆን ነውር ለወያኔና ለሌላው ሲሆን ጽድቅ ሊሆን
አይገባም፤ አይችልምም፡፡ ደርግ የወደቀው በአበባ በታኝ
የሠርግ አጃቢዎች ሣይሆን በሬሣ ላይ እየተረማመዱ
በመጡ፣ በትግርኛ ፕሮግራማቸው ‹ዘራፍ! አማራ ገዳይ! አህያ
ገዳይ! አማራ ፈሪ ነው – እንዳትለቀው› እያሉ በወሎና ሸዋ
የዋህ አማሮች መንገድ አመላካችነት በተመሙ ማይማን
የሀሽሽ ሰለባ ጦረኞችና በሕዝብ ኩርፊያ መሆኑን ልብ
ይሏል፡፡ ሌሎች ተጓዳኝ ሻጥሮችና ዓለም አቀፍ ሤራዎች …
ሳይዘነጉ፡፡ እውነት እንደፀሐይ ስለምታጥበረብር የምለው
ነገር የሚጎመዝዘው ቢኖር ልረዳው አልችልም – (አማርኛ
ተናጋሪ የሆናችሁ – በአማራነት የተፈረጃችሁ ወይም
ራሳችሁን የፈረጃችሁ ወገኖች በምንም መንገድ አትናደዱ –
በቀል የፈጣሪ እንጂ የሰው አይደለችምና ኅሊናችሁን ንጹሕ
አድርጋችሁ ወደላይ ጩኹ፤ ክፉ ብታስቡ ያ ክፋት ወደራሳችሁ
ይዞራልና እንዲያውም ክፉን ለሚያደርጉባችሁ ፍቅራችሁን
አሳዩዋቸው – አደራ)፡፡ እውነትን መናገር ሀሰትን ከመናገር
ቢከብድም ምንም ማድረግ አልችልም፡፡ በበኩሌ አህያ ጥሩ
አገልጋይ ስለሆነች ይህ ስም ሲበዛብኝ እንጂ አያንሰኝም፤
አይከፋኝምም፡፡ ስለዚህ ዕድሜ ለወያኔዎቹና – የጠቤን
ምህዳር ላስፋው ይሆን? አይ፣ ይቅርብኝ – ለማንኛውም ጥሩ
የዳቦ ስም አለኝ፡፡ ‹አንድ ጣትህን ወደሰው ስትቀስር ሦስቱ
ወዳንተ መዞራቸውን አስተውል› ይባላል፡፡ የኛንም ‹ቁስል›
ማሳየቱ ነውር አይደለም ከሚል የዋህነት ነው አለወትሮየ
እንዲህ የምል – በዚያ ላይ ዓለምሰገድ ብቻውን ‹ስለኛ›
መናገር አይገባውም – እኔም ‹ስለነሱ› ላግዘው፡፡ እርግጥ
ነው – ሁሉም እንደምንጭ ውኃ ኩልል ብሎ የሚጠራበት
ጊዜ ይመጣል – የእስከያኔውና የእስከዛሬው ድፍርስ ነበር፡፡
ከአሁን በኋላ ግን ሁኔታዎች እየከረሩ የሚሄዱበት ወቅት ላይ
የደረስን ይመስለኛል፡፡ ይህችን ሀገር እግዚአብሔር
ባይጠብቃት ኖሮ ይሄኔ ከሦርያም ብሰን ነበር፡፡ ፈጣሪ ጓዙን
ጠቅልሎ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳለ ማመን አለብን፡፡
ያልተላለቅነውና ውለን የምንገባው በኪነ ጥበቡ እንጂ
በወያኔ ቸርነትና ጥበቃ አይደለም፡፡ ለነገሩ ሰው በስንቱ
ሊበደል ይችላል?
ለማንኛውም ጥቂት ከፍ ሲል በጀመርነው ተጠየቅ መሠረት
በቀድሞ ዘመን የተሠራው መጥፎ ነገር ሁሉ የታሪክ ስህተት
ነውና ቀጣዩ የታሪክ ተረካቢ ነባሩን ስህተት አስተካክሎ
በፍትህ ይገዛል ብለን በጉጉት እንጠብቅ፡፡ ከ17 ዓመታት
የደርግ የግፍ አገዛዝ በኋላ በቆዬ የቦካ ቂም ክራሩን በአዲስ
የበቀል አንቺሆዬ ቃኝቶ ለሌላ የተነጣጠረ ዕልቂት ያላለመ
መንግሥት ጠበቅን እንበል፡፡ አልቀረም መጣ‹ልን›፡፡
ግንቦት 20 ቀን 1983ዓ.ም፡፡
ቀጣዩ የታሪክ ባቡር በትግሬዎች እጅ ወደቀ፡፡ ምን ተፈጸመ?
የ‹አማሮች› ስህተት ተደገመ ወይንስ ተስተካክሎ ዕንባ ታበሰ፣
የሚፈስ ደምስ ደረቀ? ‹አማራው› ያስለቀሳቸው ወገኖች
ጭቁኑን አማራ ጨምሮ አለፈላቸው? የታወጀላቸው ራስን
በራስ የማስተዳደር ዴሞክራሲያዊ ባህል ሠፈነላቸው? የዚያ
ሁሉ መስዋዕትነት ዋጋ ምን አመጣ? ለሌላ አዙሪት የሚዳርግ
ስህተት እየተሠራ ነው ወይንስ ፍትህ ሰፍኖ ሁሉንም ያማከለ
ልማት ተዘረጋ? ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ ተጀመረ
ወይንስ ተሠሩ የተባሉ ስህተቶች ታርመው ፍትህና ርትዕ
ነገሡ? ጥያቄውም መልሱም ከማንም የተሠወረ አይደለም፡፡
‹ተቀልዷል፣ ተቀልዷል፣ተቀልዷል› በሚል አዝማች አንዲት
ዘፋኝ ያቀነቀነችው ሥልት ትዝ አለኝ፡፡…
የሚመለከታችሁ ወገኖች በአስቸኳይ ከአማራ ራስ ውረዱ!!
‹አማራ› አጥፍቷል፤ እውነት ነው፡፡ አጠፉ የተባሉት አማሮች
ግን ብቻቸውን አልነበሩም፤ ዘመኑም እጅግ ሩቅ ነው፡፡
የመንግሥት ሥልጣን ይዛችኋል – ሌላው ወገናችሁ ብዙ
ጊዜ እናንተንና ፈጣሪን አንጋጥጦ ጠበቀ፡፡ በስቃይ እየኖረ
እንደክርስቶስ ኤሎሄ እያለ ነው፡፡ የጸሎቱ ዳፋ ግን ለማንም
ምሕረት የማይኖረው እንደሚሆን እንረዳ፡፡ እውነትን
እንነጋገር፡- የዘረኝነትን አጥር በአመዛዛኝ የዕውቀት ቁልፋቸው
ከፍተው ለጋራ ሕይወት ከሚታገሉ በጥቂት ሺዎች የሚገመቱ
የትግራይ ተወላጆች ውጪ አብዛኛው ትግራዋይ ለወያኔ
የማይራራ ልብ አለው ማለት ስለሚከብድ የሕዝቡ መራቆት
ይሰማንና ነገን ሳንጠብቅ የሚመርም ቢሆን መድሓኒት ገዝተን
ዛሬውኑ እንዋጥና ‹በኛ ይብቃ!› እንበል፤ ለልጆቻችን
መርገምት አናስተላልፍ፡፡ የማስተካከል ወርቃማ ዕድል
በበራችሁ ተኝታ ስትማጸናችሁ እናንተ ሳታስተውሏት ይሄውና
22 ዓመታት ላይመለሱ ነጎዱ፡፡ አታሞ እርግጥ ነው በሰው
እጅ ታምራለች – የማደናገር ዕዳው ሲይዟት ነው፡፡
በኢትዮጵያ ከሞላ ጎደል ሁሉም የሥልጣን ቦታዎች ላይ
አለችሎታቸውና አለዕውቀታቸው – በዘውጋዊ ታማኝነታቸው
ብቻ የተቀመጡ ሌሎችን ግን የሚያባርሩና አልፎ ተርፎም
በአሸባሪነት እየከሰሱ ወህኒ የሚያወርዱ የገዢው መደብ
አባላት ወደየኅሊናቸው በአፋጣኝ ይመለሱ፡፡ ጊዜ የለም፡፡
ፅዋው ሞልቷል፡፡ ከአሁን በኋላ ምርጫው ሁለት ነው፤ አንዱ
አካሄድን ማስተካከልና ልክ እንደደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ ዕርቅ
ማውረድ፡፡ ሁለተኛው የእናቴ መቀነት አሰናከለኝን መተውና
ወያኔዎች በድንቁርናቸውና በዕብሪታቸው ያበላሹት – ዐፈር
ላይ ጥለው አለመላው ያርመጠመጡት ዋልጌያዊ
የመንግሥት ሥልጣን አያያዝ የሚያመጣውን የማይቀር ዕዳ
ለመቀበል መዘጋጀት፡፡ ከዚያ በተረፈ “በምኒልክ የደነቆረ፣
‹ምኒልክ ይሙት› እያለ ሲምል ይኖራል” እንደሚባለው
የአማራን ስም እንደውዳሤ ማርያም ቀን ከሌት እየደገሙ
አበሳን ማብዛት የራሷን ምስል በመስትዋት ውስጥ ተመልክታ
‹አምላኬ ሆይ፣ እንኳንስ እንደዚህች ዓይነት አስጠሊታ ፍጡር
አላደረግኸኝ!› ብላ እንደጸለየችው ዝንጀሮ መሆን ነው፡፡ ጀሮ
ያለው ይስማ፤ልብ ያለው ልብ ይበል፡፡ ፀጉር ስንጠቃ
አርማጌዴዖንን አያስቀርም፡፡ ጉራና ትዕቢትም ወንዝ ቀርቶ
የደረቀ ፈፋን አያሻግርም – ሲያመጣው፡፡
ይህን የምለው አንዱ ጻዲቅ ሌላው ኃጥዕ ሆኖ አይደለም፡፡
ነገር ግን የእግዚአብሔር ሚዛን እንደሰው ሚዛን
ስለማይቀላምድ በሆነው ነገርና እየሆነ ባለው ነገር መካከል
ያለውን ልዩነት ተመልክተን የመጪውን ጊዜ ይዞታ ስንገምት
በአማራ ላይ የደረሰው ቅጣት ከወይራ ጥብጣብ ወይም
ከለበቅ የሚወዳደር እንጂ በአሁኖቹ ቀብራራ ገዢዎች ሊደርስ
ካለው ጋር በምንም መንገድ እንደማይቀራረብ ለመጠቆም
ነው – የነብርንና የሚዳቋን የ‹አሁን ብበላህ ምን እሆናለሁ?›
ምሣሌያዊ ብሂል አስታውሱ፤ ሁልጊዜ ጌትነትም የለም፤
በፋሲካ የገባች ገረድ ፍልሰታ እንደምትመጣ ካላወቀች ገልቱ
ናት – እርግጥ ነው ፋሲካና ፍልሰታ ርቀት አላቸው –
ቢሆንም … ፡፡ በበኩሌ ሁለት ነገር አስባለሁ – አንድም ያንን
የፍርድ ቀን ፈጣሪየ ባያሳየኝ፣ አንድም ያንን የፍርድ ቀን
ፈጣሪዬ አድርሶ ቢያሳየኝ፡፡ ምርጫው የርሱ ይሁንልኝ፡፡
ከአያያዝ ይቀደዳል፤ ከአነጋገር ይፈረዳል – ቀኑን እዩት ፤ ቀኑ
ደርሷል! የዘመኑን መቅረብ ለመረዳት ደግሞ በግድ ቆዳ
ታጥቆ አንበጣ እየበላ በበረሃ የሚሰብክ ሰው መጠበቅ
አይገባንም፡፡
የዘሩት መብቀሉ፣ የበቀለ መታጨዱና ተወቅቶ ጎተራ መግባቱ
አይቀርም፡፡ ሼክስፒር ‹ትልቅ ደግ ነገር ለመሥራት ትንሽ
መጥፎ ነገር መሥራት ምንም አይደለም› ይል ነበር አሉ፡፡
በኢትዮጵያ ያለው ተጨባጭ ሁኔታ ግን የስሙኒ ዶሮ
የሚሊዮን ብሩን የወርቅ ገመድ ይዛ እየጠፋች ተቸግረናል፡፡
የአንዲት ክፍለ ሀገር ጥቂት መኳንንትን ሁለንተናዊ ርሀብ
ለማስታገስና የጥቂት ሚሊዮን ዜጎችን ሥነ ልቦናዊ የገዢነት
እርካታ እውን ለማድረግ የተከፈለው መስዋዕትነትና
የወደመው ሀብትና ንብረት አሥራ አራቱንም የቀድሞ
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ግዛቶች ሕዝብ ቁጭ አድርጎ ለአሠርት
ዓመታት ይቀልብ ነበር፡፡ ነገር ግን የፊተኞቹም ሞኞች፣
የአሁኖቹም ለከት ያጡ ብልጦች ሆኑና በመካከሉ ሀገርና
ሕዝብ ለማያባራ የሲዖል እሳት ተዳርገው መቅኖ አጥተው
ቀሩ፡፡ ደግነቱ ግን ይህም ያልፋል፡፡
በዚያ ላይ ትልቁ ችግር የሆነብን ኅሊናን የሚሠቀጥጥ ውሸት
እየተለቀቀብን ፈረንጆቹ በ‹MC› (Mind Control)
በሳተላይት የተደገፉ ሥውር የአእምሮ መቆጣጠሪያ
ፕሮጄክቶቻቸው ዜጎቻቸውን በኤሌክትሮኒክስ ጨረሮች
እንደሚያነሆልሏቸው ሁሉ የኛ የገዢው መደብ ምሁራን
ተብዬዎችም እንዳቅሚቱ ያቺን የMC/PR የምትመስል
የሕዝብ ግንኙነት ሥራ መሥራታቸው ነው፡፡ ቂሎች ናቸው፡፡
በእንደዚህ ዓይነት የሞኝነት ሥራ ገብተው ሊዋረዱ
አይገባቸውም ነበር – የውርደትን ምንነት ቢያውቁ፡፡ ዝምታ
ማንን ገደለ? ምንም ሳይናገሩ የታሪክ ባቡር ወስዶ አንዱ
ሥርቻውስጥ እስኪቀረቅራቸው ድረስ ዕድል የሰጠቻቸውን
ሲሳይ ድምጻቸውን አጥፍተው እንደለመዱት እዬዘረፉ
ቢከፋፈሉ ማን ምን ያደርጋቸዋል? ልፉ ብሏቸው እንጂ ዋሹ
አልዋሹ፣ የፈጠራ ድርሰት ጻፉ አልጻፉ ያላሰቧት ዕድል
እንደሆነች በደጃቸው ከትማለችና የመጥፎ ሥራቸው የዞረ
ድምር መቅሰፍቱን እስኪያዘንብባቸው ድረስ አርፈው
መቀመጥ ይችላሉ፡፡ መንቀዥቀዥ ሳያስፈልጋቸው አሁን
እያደረጉ ያሉትን ሁሉ እያደረጉ መኖር ‹ጉልበታቸው›
የሰጣቸው መብታቸው ነው፡፡ ናፖሊዮንንና ሂትለርን የመሰሉ
አባ ጉልቤዎችም ብለዋል:- “Mighty is right”.
አስተዋይ ሰው ከቆመው ብቻ ሣይሆን ከወደቀውና
ከተቀመጠውም ብዙ ይማራል፡፡ ስህተትን በስህተት ቢደግም
ራሱም ቀኑን ጠብቆ እንደሚወድቅ ይገነዘባል፡፡ ትናንትን ከዛሬ፣
ዛሬንም ከነገ በማገናዘብ ለአለውና ለመጪው ትውልድ
መልካም ነገሮችን ቀይሶ ያልፋል፡፡ እናም ወያኔዎች ወድቋል፤
ተቀብሯል ያሉት አማራ እንግዲያውስ ለምን ወደቀ? ብለው
አዙረው ማየት ነበረባቸው እንጂ በ‹ብጥለው ገለበጠኝ›
የመሠሪነት ባሕርይ ታሪክ አፍ አውጥቶ እስኪታዘባቸው ድረስ
እንዲህ ባልተጃጃሉ ነበር፡፡ ሌላውን ሁሉ ትተን ጣልነው
ያሉትን የጣሉት በኢፍትሃዊነት ተፈጥሮው ስለተጓዘ እንደሆነ
አምነው ሳይሆን ለሀብትና ለሥልጣን በነበራቸው ጉጉት
ያስመስልባቸዋል፡፡ ይሄ ሁሉ የስም ማጥፋት ዘመቻም
ስለፍትህ በመጨነቅ ሳይሆን ለግላዊ ጥቅምና ለሥልጣን
ጥም እርካታ መሆኑን ያሳብቅባቸዋል፡፡
ኢፍትሃዊነት እነሱን ወልዶና አሳድጎ ራሱን ኢፍትሃዊነትን
ካጠፋ የነሱ ኢፍትሃዊነት ሌላ አካል ወልዶና አሳድጎ የነሱን
መረን የለቀቀ ኢፍትሃዊ አገዛዝ ሊያጠፋ እንደሚችል እንዴት
ሊገነዘቡ አይችሉም? ምን ዓይነት ተፈጥሯዊ ‹intrinsically
in-built› ድንቁርና ይሆን እነዚህን ወንድሞቻችንን
የተጣባቸው? አፄ ኃ/ሥላሴ ለምን ወደቁ? ደርግ ለምን
ወደቀ? ሂትለር ለምን ተዋርዶ ሞተ? ጋዳፊ ከ42 ዓመታት
በኋላ ከነባረያ ፈንጋይ ሥርዓቱ ለምን ተገረሠሠ? የደቡብ
አፍሪካ የጥቂቶች የአፓርታይድ አገዛዝ ብዙ ጥፋትና ውድመት
ካደረሰ በኋላም ቢሆን ለምን ወደቀ? (ነጮቹ ከጠቅላላው
ሕዝብ 6 በመቶ እንደሆኑ ይነገራል) ሆስኒ ሙባረክ ለምን
ተዋረደ? ጨቋኙ አላዊት ባሽር አላሳድ ለምን ሰሞኑን
ይወድቃል? … እነዚህ የትግሬ ገዢዎች ከዚህ ሁሉ ዓለም
አቀፍ የአሁንና የጥንት ኹነቶች ትምህርት ሊቀስሙ
ያልቻሉበትና በመዥገራዊ የዘረኝነት አባዜ እንደተለከፉ
የማርጀታቸው ምክንያት ምን ሊሆን እንደሚችል ሲታሰብ
በእጅጉ ይገርማል፡፡ ለመሆኑ ‹የክፋት ዕድሜ እስከ ስንት
ሊሆን ይችላል? የዱባ ጥጋብስ ዕድሜው ስንት ነው – ምን
ያህል ዳገቶችንስ ያስወጣል? …› ብለው ጥቂት ማሰላሰል
እንዴት አቃታቸው? ታሞ የተነሣ ፈጣሪን ረሳ ማለት እንግዲህ
እዚህ ላይ ነው፡፡ ይወቁት – አማራ በቡድንና በማኅበረሰብ
ደረጃ የማንም ጠላት አልነበረም፤አይደለም፤አይሆንምም፡፡
ግን ግን በስሙ የነገዱ ሆዳምና ራስ ወዳድ አማሮችና ሌሎች
ዘውጎችም ነበሩ፡፡ ሴትዮዋ “ዕድሌ ሆኖ ፈሴ ይሸታል”
እንዳለችው ባለቤት የታጣላቸው ታሪካዊ ስህተቶች ሳይቀሩ
በአማራው እየተላከኩ ይህን ምሥኪን ሕዝብ በኢትዮጵያና
በ‹ዓለማቀፉ ማኅበረሰብ› ዘንድ እንዲጠላ ሙከራ ይደረጋል
እንጂ አሁን ቆም ብለን ወደኋላ ብናይ አማራ ሠራው የተባለው
ነውር የአሁኑ የብዔልዘቡል መንግሥት ከሠራውና እየሠራው
ካለው ነውር ጋር ሲወዳደር ልዩነቱ በአንድ ኩሬና ከአሥር
በላይ በሚገመቱ ውቅያኖሦች የሚመሰል ነው፡፡ ለአፍ አቀበት
ስለሌለው ግን ጆሮ አይሰማው የለምና የእምዬን ወደአብዬ
ሲያላክኩ አፋችንን በሀፍረት እየተመተምን መስማትን
ቀጥለናል – እስከ አንድ ቀን ድረስ፡፡

Tuesday, February 23, 2021

100 ways to say “I love you

100 ways to say “I love you”

1. You are beautiful.
2. I love your smile.
3. Here, let me get that for you.
4. I love seeing you wake up in the
morning.
5. You are amazing.
6. I love (this) about you
7. Stay safe. Text me when you
get there
8. I love when you do (this)
9. I think you’re beautiful when
10. You’re too good for me.
11. I don’t deserve you.
12. I care about you.
13. Don’t put yourself down like
that.
14. I adore you.
15. I can’t stop thinking about
you.
16. Seeing you makes me smile.
17. I need you by my side.
18. I’m thankful for you.
19. You make me a better person.
20. You complete me.
21. Have a good day at work
22. You’re the light of my life.
23. Seeing you makes my day.
24. I get butterflies every time we
talk.
25. I’m so lucky to have you; I
don’t know how I got so lucky.
26. You set my heart on fire.
27. I’ll walk you home.
28. I love to make you happy.
29. You’re my soulmate.
30. You’re my best friend.
31. I can’t wait to see you
(again).
32. You mean the world to me.
33. You’re my rock.
34. I value you.
35. I want to spend the rest of my
life with you.
36. I love being around you.
37. Pull over and let me drive
some.
38. Take my jacket, it’s cold
outside.
39. I want you.
40. You complete me.
41. You’re my happiness.
42. Do you need anything?
43. I want to hold your hand and
never let go.
44. You’re the only one for me.
45. You are my heaven on earth.
46. Every time I look at you I fall
in love all over again.
47. Drive safe.
48. I don’t know what I’d do
without you.
49. Forever isn’t too long, because
I know I’ll be with you.
50. I’d rather argue with you than
kiss someone else.
51. You look great today.
52. I love that ___ on you.
53. You look cute when you put
your glasses.
54. I’ll always be here; I’m here for
you.
55. My heart hurts when you’re
not around.
56. I can’t think of what my life
would be like without you.
57. We’re perfect for each other.
58. I cherish you; you’re more
important than anything else in my
life.
59. I will love you until I die, and
even after.
60. You’re mine.
61. I support you.
62. I’m addicted to you.
63. You’re perfect in my eyes.
64. Take this; it’ll help you feel
better.
65. I can’t wait to see you.
66. You’re the only one for me.
67. I’m crazy about you.
68. I had an amazing time with
you.
69. I feel so lucky to have you.
70. I’ll never let you go; I’ll never
want to.
71. I hope this moment never
ends.
72. You leave me breathless.
73. I’d do anything for you.
74. Seeing you happy makes me
happy.
75. I’m sorry for hurting your
feelings.
76. You always find a way to
make me smile.
77. I can’t put what I feel for you
into words; it’s too great.
78. I still get jealous even though I
know you’re mine.
79. I’m listening to you.
80. I made this for you, I know it’s
your favorite.
81. I’m excited and nervous for
tonight with you.
82. I got you your favorite candy.
83. I’ll always care about you.
84. I made you breakfast.
85. I can never stay mad at you.
86. I love your eyes; they’re
gorgeous.
87. I love that outfit on you.
88. You look so cute.
89. You’re the highlight of my day.
90. How’d you sleep?
91. Your smile makes my heart go
crazy.
92. I hate seeing you cry.
93. It’s my job to make you
happy.
94. I want to spend more time
with you.
95. I’ll fix it.
96. I hate when we argue.
97. You’re the only person I want
to live my life with.
98. You drive me crazy (in a good
way).
99. I’m proud of you.
100. I trust you, I always will.

Wednesday, February 17, 2021

Grade 8  Chemistry Final Exam
 1.Which one of the following is    basic oxide 
 A.CaO B. MgO C. BaO D. FeO
2. Acids change color of indicator of blue lithmus into
  A. Colorless B. blue C. red D.all
3. One of the following is not hydrocarbone
A.methane B.ethanol C.Hexane D. All
4. Which compound is express about ampoteric oxide 
A.ZnO B.HCl C.HBr D.HI
5. Acids are dissolve by water to rise.....
A. H B. OH  C. N D. Fe
6. The main ore of alumunium is 
A. Corundum B.Alumunium oxide D. none 
7.The chemical formula of table salt is...
 A. NaOH  B. NaCl C.NaH D.all
8. Which one of the following is alkali metal?
 A.Ca B. Na C.Mg D.Ba
9.Which substance manufacture plastics?
 A.buthene B.ethene C.methane D.hexane
10. .......is the only alkaline gas
  A.nitrate B.ammonia C.formaline D.none
11. The commom name of calcium carbonat is.......
 A.gypsum B. limestone C. dolmite .D. none
12.the chemucal formula of hexene is......
A.CH4  B.C6H12  C. C6H10 D. C6H14
13. AN alkane that contain 6 carbon atom is called..
 A. Hexyne B. Hexane C. Hexene D.Heptane
14. Na + Cl ------->---------
 A. NaC  B. NaCl  C. NalC D.all
15. Which acid found in carbatrries?
 A.HCl  B. H2SO4  C. HBr D. all
       
     Chemistry

አፄ ቴዎድሮስ

አፄ ቴዎድሮስ
(ከታሪክ ማኅደር)
፨፨፨
ከ201 ዓመት በፊት ጥር 6 ቀን 1811 ዓ/ም በጎንደር-ቋራ
ተወለዱ ፡፡ በፈረስ ስማቸው አባ ታጠቅ ፤ በትውልድ
ስማቸው ካሳ ሀይሉ ፤ በውትድርና ስማቸው ደግሞ
መይሳው ካሳ ሲባሉ የዙፋን ስማቸው ደግሞ ዳግማዊ
ቴዎድሮስ ይባላል ፡፡
በትውፊት እንደሚነገረው በ15 ኛው መቶ ክፍለዘመን
ቀዳማዊ ቴዎድሮስ የተባለ ተወዳጅ ኢትዮጵያዊ ንጉስ ነበር
ይባላል፡፡ ይህ ንጉስ በ19 ኛው መቶ ክፍለዘመን ዳግም
ይመጣል ተብሎ በተነገረው ትንቢት መሠረት ካሳ ሀይሉ
ራሳቸውን ዳግማዊ ቴዎድሮስ ንጉሰ ነገስት ዘ ኢትዮጵያ
ብለው የካቲት 11/1847 ዘውድ ደፉ፡፡ ቴዎድሮስ የሚለው
ስያሜ "ጣዎስ ድሮስ" ከሚል የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን
ትርጉሙም የአምላክ ስጦታ ማለት ነው፡፡
አጼ ቴዎድሮስ፣ ይህ "የአገሪቱን የታሪክ አቅጣጫ
የሚቀይር" የሚመጣው ንጉስ ነኝ ብለው ያምኑ እንደነበር
ለማመን አይከብድም ። በስርዓተ ንግሳቸው ላይ ባደርጉት
ንግግር አገሪቷን አንድ ለማድረግና እንደገና ለመገንባት
ያላቸውን ከፍተኛ ፍላጎት ገልጸዋል። የቴወድሮስን የህይወት
ታሪክ የጻፈው ስቬን ሩቤንሰን አፄ ቴወድሮስ ስልጣን ላይ
ሲወጡ በአይምሮአቸው ውስጥ የነበረውን ዕቅድ እንዲህ
ሲል ይዘግባል ።
"የቴዎድሮስ ስሜት እንደቀደሙት ነገስታት ሳይሆን የተለየ
ነበር ፤ ለእርሱ የባላባቶች ትርምስ ፣ የግብረገብ መላሸቅ ፣
የቴክኖሎጂ ኋላቀርነት የአገሪቱን መኖር ጥያቄ ውስጥ
የጣሉ ጉዳዮች ነበሩ። ያወጃቸው ለውጦች፣ የተከተላቸውና
ሊተገብራቸው የፈለጋቸው ፖሊሲወች፣ እያንዳንዱን ችግር
ለመፍታት ያሳየው እልከኝነት ፣ የሚያሳዩት የንጉሱ አላማ
ብሔራዊ ተሃድሶና አገሪቱን ወደ ዘመናዊ አገር ማሻገር
እንደነበር ነው" ይላል ።

አፄ ቴዎድሮስ የንግስና ጊዜያቸው የባሪያ ንግድን ፣
ጎጠኝነትን ፣ ከወገብ በላይ ተራቁቶ በብዛት ባህልን. ..
ወዘተ አስቀርተዋል ፡፡ ዘመናዊ ኢትዮጵያን ለመፍጠር ጥረት
ያደረጉት ቴዎድሮስ የወቅቱን ዘመናዊ ጦር ፣ ዘመናዊ
የመከላከያ ምሽግ እና ዘመናዊ ሙዚየም አቋቁመዋል፡፡
ከውትድርናው ውጪ መፅሀፍ ቅዱስን በአማርኛ በብዛት
እንዲተረጎም ከማድረግ ባለፈ ስነፁሁፍ እና ፍልስፍና
እንዲያድግ የቻሉትን ያህል ጥረዋል ፡፡ የመንገድ ዝርጋታ
በማስጀመርም ሆነ ብሔራዊ ፍቅርን በመስበክ ለዘመናዊ
የኢትዮጵያ ታሪክ የአንድነት መነሻ ሆነዋል (ፓውል
ሄንዝ ) .።
አፄ ቴዎድሮስ የዘመናዊ ስልጣኔን በር ከፋች ሲሆኑ
"እንደገና አንድ የሆነችና ጠንካራ ኢትዮጵያም" ምልክት
ናቸው ። የአገሪቱን ፖለቲካዊና ሃይማኖታዊ አንድነት
ለመመለስ ታላቁ ምኞታቸው ነበር ፣ ያገሪቱን ጥንታዊ
ድንበርም ለማስመለስ እንዲሁ ። የቴዎድሮስ መነሳት
የዘመናዊ ኢትዮጵያ ታሪክ መጀመሪያ ነው ። ለዚህም
ምክንያቱ ደግሞ የፈጸሟቸው ለውጦች ናቸው ።

አጼ ቴዎድሮስ ብዙ የጓጉለትን ለውጥ ማምጣት ሳይችሉ
ከውስጥና ከውጭ በተቀሰቀሰባቸው ተቃውሞ ምክኒያት
የእንግሊዝ ወራሪ ጦርን ተፋልመው በሚያዝያ ወር 1860
ዓ.ም መቅደላ አምባ ላይ ለሀገራቸው መስዋዕት የሆኑ
ታላቅ ንጉስ ነበሩ ፡፡
በፈረስ ስማቸው ከተገጠመላቸው ግጥሞች፦
ታጠቅ ብሎ ፈረስ ካሣ ብሎ ስም ፤
ዓርብ ዓርብ ይሸበራል ኢየሩሳሌም ።
አባ ታጠቅ ካሳ ነገር ሲያሰላስል ፤
ባህሩን ያስባል መረብ ጣይ ይመስል ።
ትልቅ ነበርን ትልቅም እንሆናለን
፨ ዛሬ የጀግናው 201ኛ ዓመት ነው...እንኳን ተወለዱልን
ጊዜውን የቀደሙ እንቁ መሪ ነበሩና

ያድራል በየቦታው ለነብሱም አይሳሳ
ብለው ይሻለኛል አንድ አርጋቸው ካሳ
አንድ ቀን ሳይደላው ሁሌ እንደዋተተ
ለአገሩ ተፈጥሮ ለአገሩ የሞተ
(ትዕግስት አፈወርቅ_አልረሳ አለኝ...ከሚለው ሙዚቃ)
ዋቢ መጽሐፍት ፦
1. ጳውሎስ ኞኞ (አፄ ቴዎድሮስ)
2. ባህሩ ዘውዴ

Monday, February 15, 2021

ዴርቶጋዳ

ዴርቶጋዳ

ዳን ብራውንን ስሙን ያልሰማ ወይም ከመፃህፍቱያልተቋደሰ
ይኖር ይሆን? ብራውን “የዳቪንቺ ኮድ” ደራሲነው። ይህ ቅኝት
በተፃፈበት ሰሞን ካሳተመው “ዘ ሎስትሲምበል” ጋር አምስት
መፃህፍትን አቅርቦልናል። ብራውንየደራሲ ሮበርት ሉድለም ደቀ
መዝሙር ነው። ሉድለምበአርባ አመቱ ወደ ድርሰት ዓለም ከገባ
በሁዋላ በህይወትበኖረባቸው ዘመኑ ስፍር ቁጥር የሌላቸው
ውስብስብ፤እጅግ ፈጣን የድርጊት ታሪክና የደም ዝውውወርን
የማቆምሃይል ያላቸው የሚመስሉ ልብ አንጠልጣይ የስለላና
የሴራመፃህፍትን አበርክቶልናል።
ደቀመዝሙሩን ከመምህሩ (ብራውንን ከሉድለም) የሚለየው
ጉልህ የድርሰት ባህሪ አለው። አንባቢየብራውንን መፃህፍት
አንብቦ ሲጨርስ ነፍሱ እፎይታንአታገኝም። ሠላም አይኖራትም፤
ዕውቀት ትጠማለችና። ይህየብራውን ልዩ የድርሰት ችሎታው
ነው። ይህ የዳን ብራውንየድርሰት አደራረስ ልቤን ምርኮኛው
አድርጎት ኖሯል።
ለምሳሌ በብራውን መፃህፍት ሳቢያ – በቫቲካን
ቁልፍልፍኮሪደሮችና በከርሰ ምድሩም የምሥጢር ጓዳ
ጉድጓዶች፤በፓሪስ ጥልፍልፍ መንገዶችና ሙዚየሞች፤
በስፔንካቴድራሎችና በስዊስ የባንክ ጎተራዎች፤
በኒውዮርክጉራንጉሮችና በዋሽንግተን ድብቅ
ዋሻዎች….የሊዮናርዶዳቪንቺን ሥዕላዊ ምሥጢራት፤ የኒውተንን
ድብቅ ቀመር፤የገጣሚያንን ስውር ቅኔ፤ የመንግሥታት መሪዎችን
ስውርተልዕኮ…የባህታውያንን፤ የቴምፕለሮችን፤
የማሶናውያንንምሥጢራዊ ድርጅቶችና ዓላማዎችቻቸውን…
ብራውንንተከትዬ ሳሳድድና አብሬያቸው ስሳደድ ኖሬያለሁ።…
ከእንግዲህስ ነፃነቴን አውጃለሁ አቶ ዳን ብራውን!
ፀሐይ በጠዋት ማልዳ አዲስ ቀን መውጣቱን ለአዳም
ዘርለማብሰር አድማስን ታካ ከወደ ምሥራቅ አምራና
ደምቃፍንትው እንደምትል፤ እንዲሁ ደግሞ ከወደ ምሥራቅአፍሪቃ
ከምድረ ኢትዮጵያ በዓለም የሥነ ፅሁፍ ማማ ላይየወጣ
ዴርቶጋዳ ርችቱን ተኩሷል። ተኳሹም ብላቴናይስማዕከ ወርቁ
ይባላል።
 ዴርቶጋዳ – በሴራው ውቅረት የረቀቀ፤ በቋንቋው
ውበትየመጠቀ፤ በገፀ ባህሪያቱ የገዘፈ፤ በምናብ ህዋን
የዳሰሰ፤ተስፋና ራዕይ ያነገበ፤ ትላንት ዛሬንና ነገን ያቆራኘ፤
የዚህወጣት ትውልድ ታላቅ የሥነ ፅሁፍና የፈጠራ ስራ
ውጤትነው፤ የብላቴናው ይስማዕከ ወርቁ በረከት።
እነሆ በፓሪስ ኤፍል ታወር ላይ ቆሜ፤ በኒው ዮርክ ስታቹ
ኦፍሊበርቲ ሠገነት ላይ ወጥቼ፤ በሲድኒ ሀርበር ብሪጅ
ላይተንጎራድጄ፤ አዲስአባ በምኒልክ አደባባይ ነጋሪት ጎስሜ –
ዴርቶጋዳን ለዓለም አውጃለሁ…እኛም አለን ዳን ብራውን!!
ማሔር ሻላል ሐሽ ባዝ
በታላቁ መፅሐፍ ላይ ኢትዮጵያ ስሟ ተደጋግሞ
ተነስቷል።ከሁሉም በላይ ግን ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ አያሌ
የዓለምማህበረሰብንም አመራማሪው “ኢትዮጵያ እጆቿን
ወደፈጣሪ ዘርግታለች” የሚለው ነው።
ይህ ከተፃፈ ምዕተ ዓመታት ተቆጥረዋል። ዛሬም
ኢትዮጵያእጆቿን ወደ ፈጣሪዋ እንደዘረጋች ናት።
ፀሎቷንናልመናዋን አላቋረጠችም። ‘አንኳኩ ይከፈትላችዃል፤
እሹታገኙማላችሁ” ይላል የጌታ ቃል። ኢትዮጵያ
እስከዛሬባላቋረጠችው ፀሎቷ የምትሻውን አላገኘችም።
በሩምአልተከፈተላትም።
 ለመሆኑ ስለምን ይሆን ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ ፈጣሪዋዘርግታ
የምትፀልየው? ፀሎቷስ ስለነማን ነው? ፈጣሪዋስየሚሰማት
መቼ ይሆን?…እንጠይቃለን እኛ።
እነሆ አንድዬ ፀሎቷን መስማቱንና የዛሉት ክንዶቿምይጠነክሩ፤
የጠወለገው ገላዋም ይፋፋ፤ ግርማ ሞገሷምይመለስ ዘንድ፤
ራዕይ አስይዞ መልዕክተኛውን ልኮላታል – ዴርቶጋዳን።
እንደ መልዕክተኛው ጳውሎስም፤ ራዕይ የታየው
ብላቴናውመልዕክተኛ ይስማዕከ ሲፅፍም፤ “ከላይኛው ደራሲ
ዘንድየተላከ ታላቅ መልዐክ በሬን በርግዶ ገብቶ
ከእንቅልፌአባነነኝ።…ከወርቃማ ክንፉ ላይ አንድ ላባ ነቅሎ
ብዕርቀርፆ ሰጠኝ። በታላቅ ሰሌዳ ላይም “ማሔር ሻላል ሐሽባዝ”
ብለህ ፃፍ አለኝ።…” ይላል። ምን ማለት ይሆን? ይህየስላሴ
ቋንቋ ነውን? ራዕይ የታያቸው ብቻየሚገለጥላቸው?
በላይኛው መልዐክ ቋንቋ “ማሔር ሻላል ሐሽ ባዝ”ማለትም
“ምርኮ ፈጠነ ብዝበዛ ቸኮለ” ማለት ነው ይለናል– ምሥጢሩን
የፈታልን ይስማዕከ።
ተማራኪው ማን ነው? ተበዝባዡስ? ብዝበዛውስ
መፍጠኑስለምንድን ነው? – እንላለን እኛ ደግሞ፤
ምሥጢራዊውቋንቋ ይበልጥ በአእምሯችን እየተወሳሰበ።
“ኦርያ ኢትዮጵያ…ማሔር ሻላል ሐሽ ባዝ” ይላልደራሲው ደግሞ
– በውድቅት ሌሊት የተነገረውን መልዕክትሲያስተላልፍልን። ምን
ማለት ነው? እንጠይቃለን እኛደግሞ። “ኦርያ!…ማሔል ሻላል
ሐሽ ባዝ” ማለትም“የኢትዮጵያ ተባዮች ከላይዋ ላይ ተነሱ…
ምርኮፈጥኗል…ብዝበዛ ቸኩሏል” ማለት መሆኑንተርጉሞልናል
ደራሲው።
 ያንተ ያለህ! እንላለን እኛ፤ መልዕክቱ እንደ ድንገተኛነጎድጓዳዊ
መብረቅ በህሊኛችን ውስጠ ውስጥ ብርሃኑሲያስገመግም
እየታየን። “ዓይን አላቸው አያዩም፤ ጆሮአላቸው አይሰሙም”
የሚለው የመለኮት ቃልከነጎድጓዳዊው ብርሃን ጋር በአእምሯችን
እያስተጋባ።
 ዕውነት ነው እንላለን፤ የጋረደን ጉም እየተገለጠልን፤ዕውነታው
እየታየን። ኢትዮጵያ በተባዮች ተወራለች።ኢትዮጵያ ተማርካለች።
እጆቿንም ወደ ፈጣሪ እንደዘረጋችያለችው ዛሬም መማረኳን
ስታሳየው ነው፤ አቅም ማጣቷን፤ከምርኮዋ ነፃ የሚያወጣት
አለማግኘቷን።
 “ኦርያ ኢትዮጵያ!”
ዕርግጥ ነው አይተናል። ዕውነት ነው ሰምተናል።
ብዝበዛውፈጥኗል። የኢትዮጵያን ሆድዕቃ ቦትርፈው
አንጀቷንየሚዘለዝሉ ጅቦች በዝተዋል። እነሆ እንደ
መስቀልቅርጫም እየተቀራመቷት ናቸውና። ለዘመናት
አይተንእንዳላየ – ሰምተንም እንዳልሰማ ኖረናል።
ሀጢያታችንበዝቷል። ወንጀላችንም በርክቷል። እንደ
ጲላጦስእጆቻችንን ታጥበን – በኢትዮጵያ ምርኮ
የለንበትም፤ብዝበዛውንም አናውቅም – ለማለት አንችልም።
የፍርድቀን ቀርቧልና!
ማሔር ሻላል ሐሽ ባዝ – “እግዚአብሄርም ታላቅ ሰሌዳወስደህ
ምርኮ ፈጠነ ብዝበዛ ቸኮለ ብለህ በሰው ፊደልፃፍበት።
የታመኑትን ሰዎች ካህኑን ኦርዮንና የበራኪዩንልጅ ዘካርያስን
ምስክሮች አድርግልኝ አለኝ” ይላል የኢሳያስመፅሀፍ። ይህ
እንግዲህ የናሳው ሳይንቲስት ኢንጂነር ሻጊዝእጅጉ በዴርቶጋዳ
ላይ ለትንሳኤ ኢትዮጵያ ያዘጋጀው ዶ/ርሚራዥ በቀይ ድንጋይ ላይ
ተቀርፆ የደረሰው መልዕክትመፅሐፍ ቅዱሳዊ ትርጉም ነው።
“አዎን” አለ ሚራዥ ቀዩን ድንጋይ እንደያዘ፤ “ምርኮፈጥኗል
ብዝበዛም ቸኩሏል። ሀገሪቱ በቅጥረኞችናበአድርባዮች
እየተበዘበዘች ነው። ህዝቦቿ የበይተመልካች ሆነዋል። ተስፋ
በቆረጠ ትውልድተሞልታለች። ወጣቶቿ እንጀራ ፍለጋ በባዕዳን
ሀገርሲሰደዱ በጋንጃቸው እየታረዱ ነው። ሴት ልጆቿ
የአረብገረዶች እየሆኑ ነው። ማምለጫ ያጡትም
በጥቁርአልማዛቸው ላይ ተኝተው እየለመኑ ነው። አዎ
ጥቂቶችእየበዘበዙ ነው። ኢትዮጵያን የተሰበረ መንፈስወጥሯታል።
ምርኮ ፈጥኗል ። ብዝበዛም ቸኩሏል።”
ያንተ ያለህ! እንላለን እኛ ይህንን ስናነብ ከሚያስጨንቅህልም
ውስጥ ድንገት እንደ ባነንን ሁሉ። ምርኮውመፍጠኑ ብዝበዛውም
መቻኮሉ ስለምን ይሆን? እንላለንበአንክሮ። ምን ይሻላል? ምን
ይበጃል? አርባ ማዕልት አርባሌሊት ብንፆም ብንፀልይና ብንሰግድ
ፈጣሪያችን ይታረቀንይሆን? – እንጠይቃለን እኛ።
የለም! ይለናል ዴርቶጋዳ። ፆም ፀሎት ለነፍሳችሁ
ነው፤ለሥጋችሁ። እና ምን ይሻለናል? እንጠይቃለን ደግመን።
“አንድ ነገር ያስፈልጋል። ለለውጥ ራስን መስጠት።አሁንም…
ኢትዮጵያ አንድ አብዮት ያስፈልጋታል።ልጆቿን የማይበላ አብዮት!
ራሱን የማይውጥ አብዮት! ሳይንቲፊክ ሪቮሉሽን። በሳይንስና
ቴክኒዮሎጂ የታገዘአብዮት።…ለውጥን የሚጠላ ኢትዮጵያዊ
የለም። ለውጡሆዳቸውን ከሚያጎልባቸው ጥቂቶች በቀር።
ችግሩ ግንየለውጡ አካል መሆን የሚፈልግ የለም። በሌሎች
ሞትናደም ለመጠርቃትና ኑሯቸውን ለማደላደል የሚመኙብዙዎች
ናቸው።” – ከዓለማችን ዝነኛ ሳይንቲስቶች አንዱሻጊዝ እጁጉ
ነው የሚመልስልን – በዴርቶጋዳ።
ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል? ግራ በመጋባት
እንጠይቃለን።ከሎሬት ፀጋዬ ገብረ መድህን ‘ሰቆቃው ጴጥሮስ”
ምሥጢራዊ ሥነ ግጥም ውስጥ መልሱን ታገኙታላችሁ –
ይለናል ዴርቶጋዳ።
በ1961 ዓ/ም አባ ዲዲሞስ የተባሉ ሰው ለባለ ራዕዩ
ወጣትገጣሚ ፀጋዬ ገብረ መድህን በአቁማዳቸው ውስጥ
ከያዙትብራና አርባ ስምንት ቃላትን አውጥተው አንድ መቶአምስት
(105) ስንኞች ባሉት “ሰቆቃው ጴጥሮስ” ሥነግጥሙ ውስጥ
ወጣቱ ባለቅኔ እንዲዘራቸው ያደርጉታል።አርባ ስምንቱን የአባ
ዲዲሞስ ምሥጢራዊ ቃላት ጨምሮ‘ሰቆቃው ጴጥሮስ” አራት
መቶ ዘጠና ሰባት (497) ቃላትአሉት። እነሆ እኒህ አርባ ስምንት
ቃላት ታላቅ ምሥጢርያለውንና በቁጥሮች የተነቀሰውን በ “ቶ”
ፊደል ቅርፅየተሰራውን “ዴርቶጋዳ” የተሰኘውን መስቀል
እንቆቅልሽየሚፈቱ ቁልፎች ናቸው – ይለናል ይስማዕከ ወርቁ።
ታምርአያልቅም፤ በዴርቶጋዳ! ለመሆኑ አባ ዲዲሞስ ማን ናቸው?
እንጠይቃለን እኛ።
አባ ዲዲሞስ የአባ ፊንሀስና የአባ ዠንበሩ ጓደኛ የነበሩ…
የማፊያው የአባ ዲዎላ አባት…በሳይንቲስት ሻጊዝ እና በዶ/ር
ሚራዥ ጀርባ ላይ የሚገኙትን የመስቀል ንቅሳቶችየሳሉ…አቡነ
ጵጥሮስ ሀውልት ላይ ሽንታቸውንእያንፎለፎሉ አቡኑን ሲሳደቡ…
ከወጣቱ ባለቅኔ ፀጋዬ ጋርግብግብ የገጠሙ ናቸው፤ አባ
ዲዲሞስ ማለት።
ስለምንድን ነው አባ ዲዲሞስ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት
ላይመሽናታቸው? የከረመ ብስጭት አለባቸው – አባ
ዲዲሞስ።አቡነ ጴጥሮስ አልሰማ ብሎኝ ነው የሞተው – ይላሉ
አባዲዲሞስ። “…ክፉ ነገርን ማለፊያ ጥበብ
አልነገርኩህምነበር?…አንተ ድንጋይ!…ክፉ ቀንን በጥበብ ከማለፍ
በላይጥበብ የለም…ይህንንም ነግሬህ ነበር። ይህቺ ደም
መላስየለመደች ሀገር የምትለወጥ መስሎሃል! …ስንት
ጀግኖችሞቱላት…አልተለወጠችም። ጴጥሮስ አልነገርኩህም…
አንተብትኖር ኖሮ ይሄኔ አቡነ ዲዲሞስ እባል ነበር። የዚህች
አገርእጣ ፈንታ በእጃችን ይወድቅ ነበር። እንለውጣት ነበር።
ግንሞትክ…ጵጵስና ሳትሾመኝ ሞትክ” ይህን እያሉ ነበር
አባዲዲሞስ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ላይ ሽንታቸውንያንፎለፎሉት
– በ1961 ዓ/ም።
ይህንን ስናነብ አእምሯችን ይወጠራል። አቡነ ጴጥሮስና
አባዲዲሞስ ይተዋወቁ ነበርን? ምሥጢርም ነበራቸው
ማለትነው? ኢትዮጵያን የመለወጥ ምሥጢር? ለመሆኑ
አቡኑናአባው ኢትዮጵያን የመለወጥ ራዕያቸው ምን ነበር?
ሃይማኖትና ፖለቲካ፤ ጉድ ነው! እንላለን በመሃይምአንደበታችን፤
እንቆቅልሹ ሲበዛብን።
“ይኸው እኒህኛው ጳጳስ የዳጋ እስጢፋኖስ ገዳም አበምኔትእንኳ
ያድርጉኝ ብላቸው ከለከሉኝ። አባ ዠንበሩን ሾሙት።አንተ ብትኖር
ግን ወንበዴዎች ጳጳስ ሆነው አይሾሙምነበር። እኔና አንተ
የምናውቀው የዚህች ሀገር ምሥጢርበወንበዴዎች እጅ አይገባም
ነበር።…ለምን ስልጣንሳትሰጠኝ ሞትክ? ለዚህች ሀገር ታላቅ
ስራ ልንሰራተስማምተን ከዳኸኝ አንተ ድንጋይ…” ማርያም
ድንግላዊትሆይ! እባክሽ አማልጂን! እንላለን ስድስት ጊዜ
አማትበንበአባ ዲዲሞስ ንግግር ተጨንቀን።
ጵጵስናውንም ወንበዴዎች ተሹመውበታል እንዴ?እግዚኦ!! ይህ
ሁሉ ሲሆን ኢትዮጵያውያን የት ነበርን? ለመሆኑ አባ ዲዲሞስና
አቡነ ጴጥሮስ ይጋሩት የነበረውየዚህች ሀገር ምሥጢርስ ምንድን
ነበር? እንጠይቃለንራሳችንን ደጋግመን።
ታዲያ አባ ዲዲሞስ ሀውልቱ ላይ መሽናታቸውና አቡነጴጥሮስን
መሳደባቸው ሆን ብለው ነበር፤ ወጣቱን ባለቅኔናገጣሚ ፀጋዬ
ገብረመድህንን አበሳጭተው ለማጥመድ።
“ድንጋይ አይደለም” ይላቸዋል ወጣቱ ገጣሚ በደም ፍላት፤አባ
ዲዲሞስ ላይ አፍጥጦ። “ድንጋይ ነው” ይሉታልእሳቸውም
መልስው እያፈጠጡበት። ይቃመሳሉ በቡጢ – ዲዲሞስና
ፀጋዬ።…ያን ሌሊት ፀጋዬ ቤቱ ሲገባ “ሰቆቃውጴጥሮስ”ን
ይፅፋል። ያንኑ ሌሊት አባ ዲዲሞስም ፀጋዬ ቤትዘው ብለው
ይገባሉ። እናም ያንኑ ሌሊት አቁማዳቸውንፈትተው ከብራናቸው
ላይ አርባ ስምንት ቃላት ለወጣቱገጣሚ ሰጥተውት በ”ሰቆቃው
ጴጥሮስ” ውስጥ አራምባናቆቦ አድርጎ እንዲዘራቸው አዘዙት።
የቃላቱን ምሥጢርፀጋዬ አያውቅም። አውቆም ከነበረ
አልነገረንም። ግን“ዝም እንበል” ብሎ ፅፏል፤ “አብረን ዝም
እንበል”። ሌላቅኔ፤ ሌላ ቁልፍ፤ ሌላ ምሥጢር ይሆን?
አናውቅም።…ከእንግዲህ “እሳት ወይ አበባ” የሥነ ግጥም
መድብልመሆኑ አከተመ፤ የምሥጢራት ጎተራ እንጂ!
እድሜለዴርቶጋዳ፤ እድሜ ለብላቴናው ይስማዕከ!
“እሳት ወይ አበባ” የሚለው የፀጋዬ የሥነ ግጥም
መድብልለህትመት ‘ብርሃንና ሰላም’ ሲገባ አባ ዲዲሞስ
“አክሳፎስ” የሚል ርዕስ ያለው የመፅሀፍ ረቂቅ ይዘው ገብተው
ነበር – “ሰቆቃው ጴጥሮስ” በመድብሉ ውስጥ መካተቱንና
አርባስምንቱም ምሥጢራዊ ቃላት በግጥሙ ውስጥተሰራጭተው
መኖራቸውን ለማረጋገጥ። አባ ዲዲሞስ“አክሳፎስ”ን
አላሳተሙም። ለመሆኑ ‘አክሳፎስ’ ምን ማለትይሆን? ማለታችን
ግን አልቀረም። ማን ያውቃል? አንድ ቀን‘አክሳፎስ’ ታትሞ
ምሥጢሩንም እናውቅ ይሆናል።እስከዛው ግን በ’ዴርቶጋዳ’
ምሥጢር እንመራመር…
አባ ዠንበሩ ራዕይ ናቸው
አባ ዠንበሩ፤ አባ ዲዲሞስ፤ አባ ፊንሐስ። ሶስት
አባዎች፤የዴርቶጋዳ ምሥጢር መዘውሮች። ሶስት
አርበኞች።በፋሽስት ጣሊያን ወረራ ዘመን የነፃነት
ፋኖዎች።በምሥጢራት የተሞሉ አባዎች፤ አርበኞች።
ከነፃነትበዃላስ?…
 “…ዋሻውን መቆፈር ስንጀምር (አባ ዠንበሩ፤ አባዲዲሞስ፤ አባ
ፊንሐስ) አላማችን ለራሳችን መደበቂያነትለመጠቀም ነበር።
በዃላ የሀገሪቱ ውድ ሀብቶችና የብራናመፃህፎች ከጥፋት
መከላከያ ሆኖ አገለገለ። እኔም በዚህወቅት በገዳሙ ውስጥ
በማነባቸው መፃህፍት እየተቀየርኩመጣሁ። ራዕዬን ከግለሰብነት
ወደ ሀገራዊነትቀየርኩት…” አባ ዠንበሩ ናቸው ለዶ/ር
ሚራዥየሚነግሩት።
 አባ ዠንበሩ የዴርቶጋዳ ራዕይ ናቸው፤ እርሾ። የጣና
ገዳማትጥንተ ጥንታዊ መፃህፍት ናቸው አባ ዠንበሩን
ዳግምየፈጠሯቸው – ራዕይ የሰጧቸው። እንቀጥል
የአባዠንበሩን ትረካ፤
“…ይህንን ዋሻ ወደ ትልቅ ህቡዕ የምርምርና
መንግሥታትሲለዋወጡ የማይለዋወጥ ለሀገሪቱ ፅኑ መሰረት
የሚሆንምሥጢራዊ ድርጅት የማድረግ ራዕይ
በውስጤተጠነሰሰ…ኢትዮጵያን ለኢትዮጵያውያን
ማድረግየሚቻለው ትክክለኛው የቴክኒዮሎጂ
ዕውቀትናትክክለኛው የቴክኒዮሎጂ መሳሪያ በራሷ ልጆች እጅ
ሲገባመሆኑን ተረዳሁ።…ይህንን ራዕይ የተጋራኝ ሰው
አለቃአያሌው ብቻ ነበር። አያሌው…አባ ዲዲሞስ ይባል ነበር።
አባዲዲሞስ ብዙ ለውጦች ለማምጣት ሥልጣን
ይፈልግነበር።…ከአቡነ ጴጥሮስ ጋር ቅርርቦሽ ነበረው።…
አቡነጴጥሮስ በባንዶች የጣሊያን አሽከሮች በጥይትተደብድበው
ሞቱ። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ባህሪውተለወጠብኝ።…” ይላሉ አባ
ዠንበሩ ለዶ/ር ሚራዥሲያስረዱ። አባ ፊንሐስስ?… “…አባ ፊንሐስ
ስለ ሀገርማሰብ አይፈልግም። ኢትዮጵያ የሚለው
ቃልያንገሸግሸው ነበር” – ይላሉ አባ ዠንበሩ። አስገራሚታሪክ…
ሶስት አባ–ዎች…ሶስት መንገዶች።
አባ ዲዲሞስ፤ አርበኛ፤ ፈላስፋ፤ ንቅሳት (ንድፍ) ነዳፊ፤ለውጥ
አላሚ፤ ሥልጣን ፈላጊ።
አባ ፊንሐስ፤ ከራስ በላይ ንፋስ ያሉ፤ የኢትዮጵያን እንባመጥረግ
እማይፈልጉ፤ ከዋሻው ውስጥ ከሚገኙት ቅርሶችየንጉሥ ዘውድ
ሰርቀው የሸጡ፤ ወንጀለኛ አባ።
አባ ዠንበሩስ? አባ ዠንበሩማ ራዕይ ናቸው ብለናል፤የኢትዮጵያ
ራዕይ…
 እንቀጥል…
“…በዚህ ዋሻ ውስጥ ብዙ ለውጦች ታይተዋል…ይህምየሆነው
እንደ ኢንጂነር ሻጊዝ ያሉ ኢትዮጵያውያንሳይንቲስቶች በገንዘብም
በእውቀትም አብረውን መስራትከጀመሩ በሁዋላ ነው።…” ይላሉ
አበ ዠንበሩ ለዶ/ርሚራዥ ሲያብራሩ። አባ ዠንበሩ ምንድን ነው
እሚነግሩን? ኢንጂነር ሻጊዝ እጅጉ፤ የናሳው ምርጥ ሳይንቲስት
ከአባዠንበሩ ጋር? እንጠይቃለን በታላቅ መደመም፤
የዴርቶጋዳተአምር መቼም በዋዛ አያልቅም።
“ከእኔ የሚጠበቀው ምንድን ነው?” ዶ/ር ሚራዥ ነበር
አባዠንበሩን የጠየቃቸው።
“ሁለት ነገር ይጠበቅብሃል። አንዱ ቀሪ ህይወትህን በዚህድርጅት
ውስጥ በማገልገል ሀገርህን ከጥፋት ማዳንነው። በዚህ ሰዓት
ዓለም ዐቀፍ ማፍያዎችከማይጠረቁት የመንግሥት
ባለሥልጣናት ጋር በመሻረክሀገርህን እየበዘበዙዋት ነው።…
“ማሔር ሻላል ሐሽ ባዝ…ምርኮ ፈጠነ ብዝበዛ ቸኮለ።ኢትዮጵያ
ተስፋ በቆረጡ ወጣቶችና ህዝቦችተሞልታለች። የብዙ
ኢትዮጵያውያን መንፈስተሰብሯል። የድህነቱ ምንጭ ምን እንደሆነ
ሁላችንእናውቀው ይሆናል። እሱን ለመድፈን ግን አንድ
ልብየለንም። መንፈሳችን ተሰብሯል። ስለዚህም በአሰቃቂሁኔታ
እየተበዘበዝን ነው። ራሳችንን ለብዝበዛያጋለጥነው እኛው ራሳችን
ነን። የጋራ ራዕይ ሊኖረንይገባል።”
አባ ዠንበሩ የሚነግሩት ለማን ነው? እንላለን። እያንዳንዱቃል
በህሊናችን እየተሰነቀረ የሀገራችንን እውን ሰቆቃለዳተኛው
ልባችን እየነገረ ማንነታችንን ሲፈትነንእየታወቀን። አዎ ዕውነት
ነው፤ መንፈሳችን ተሰብሯል፤በዘመናችን የህወሃት ፕሮፓጋንዳና
ተግባር ማንነታችንተሽመድምዷል፤ ወኔያችን ተሰልቧል፤
መሰረታችንተናግቷል…ምን ይሻላል? እንመለስ ወደ አባ ዠንበሩ፤
“… ሌላው ከእኔ የሚጠበቀው ነገር ምንድን ነው?” ጠየቃቸው
ዶ/ር ሚራዥ።
“የሰጠመውን መርከብ የምናወጣበትን ቁልፍ ስጠኝ”
“ምን?”
“በ’ቶ’ ቅርፅ የተሰራውን ግማደ መስቀል መልስልኝ።”
“እሱ መስቀል ቁልፍ ነበር እንዴ?”
ሰአሊነነ ቅድስት! ጉድ መጣ!! አባ ዠንበሩ ሰጠመ ያሉትመርከብ
ምንድን ነው? እንላለን ልባችን እንደ ማዕበልእየተነሳና እየፈረጠ።
ማንስ ለምን አሰጠመው? መቼስ ነበርየሰጠመው? በውስጡስ
ምን ይዟል? መርከቡና አባዎቹስግንኙነታቸው ምን ይሆን? ግማደ
መስቀሉስ እንደምንየሰጠመው መርከብ መክፈቻ ቁልፍ ሊሆን
ይችላል? ለዶ/ርሚራዥስ ቁልፉን ማን ሰጠው? እግዚኦ!
እንላላንየጥያቄዎች አይነትና ብዛት በአእምሯችን ሲተራመስብን…
እናም ምሥጢራቱ ላይ ለመድረስ፤ ውስብስቡን
ለመፍታት፤ዴርቶጋዳን ገፅ በገፅ እያጣፋን እንነጉዳለን…
ሣይንቲስት ሻጊዝ እጅጉ ህያው ነው
ከዴርቶጋዳ ረቂቅና አስገራሚ ገፀ ባህሪያት አንዱሣይንቲስት
ኢንጂነር ዶ/ር ሻጊዝ እጅጉ ነው። ይህ ሰውአሜሪካንን የህዋው
ልዕለ ሃያል ካደረጓት ሳይንቲስቶችአንዱ ነው። ሻጊዝ የኢትዮጵያ
ልጅ ነው።…እነሆ ሳይንቲስቱፊቱን ወደ እናት ሀገሩ መልሷል –
ይለናል ዴርቶጋዳ። መላእውቀቱን፤ ንብረቱንና እሱነቱን ለሀገሩ
መስጠት ከጀመረዓመታት ተቆጥረዋል…ሳይንቲስቱ ፊቱን ወደ
ድሃ ሀገሩመመለሱ ደግሞ የተለያዩ መንግሥታትን ከፍተኛ
ሽብርውስጥ ጥሏቸዋል። ሻጊዝ ከአሜሪካን መዳፍ
እንዳይወጣየአሜሪካን መንግሥት ለሲ አይ ኤ ጥብቅ
ትዕዛዝአስተላልፏል…
ሳይንቲስት ሻጊዝ እጅጉ የዓለማችንን ራዳሮች
ሳተላይቶችናየመገናኛ አውታሮች በፈለገው ጊዜ መዝጋት
የሚችልአእምሮ ያለው ነው።…እና ይህ ሰው ድሃ ሀገሩን
ለማንሳትበመነሳቱ አሜሪካንና እስራኤል ተረብሸዋል።
በአረብሀገራት የስለላ መዋቅራት ታፍኖ ሊወሰድ
ይችላልስለሚሉም ርምጃ መውሰድ አለባቸው። የእስራኤሉ
ሞሳድበእጁ ሊያስገባው መረቡን ዘርግቷል። የሩሲያው ኬ ጂ
ቢምየሻጊዝን ማንነት የሚያውቅ በመሆኑ
እንቅስቃሴውንእየተከታተለ ከነህይወቱ አፍኖ ሊወስደው
መሰናዶውንአጠናቋል። ከሁሉም በላይ የሚገርመው ደግሞ
የኢትዮጵያመንግሥት የስለላ ድርጅት ወኪሎች የሳይንቲስቱን
ህይወትየሚቀጥፉበትን አመቺ ጊዜና ሰአት
እየተጠባበቁመሆናቸው ነው። ”…ይህ ሰው እንኳንስ
ጭንቅላቱናሊቅነቱ አስከሬኑ እንኳን ኢትዮጵያን አይረግጣትም” –
ሲሉዝተዋል፤ የኢትዮጵያ መንግሥት የላካቸው ገዳይ
ሰላዮች።ለምን? ማለታችን ግድ ነው ይህንን ሲነግረን ዴርቶጋዳ።
በዘረኝነት ላይ የተገነባውና ዘረኝነት የተጠናወተውየህወሃት/
ኢህአዴግ አገዛዝ በኢትዮጵያዊነት የማያምንበመሆኑ ሀገሪቱን
በማፈራረስ ላይ ይገኛል፤ ኢትዮጵያበጥፋት ዘመን ውስጥ
ትገኛለች፤ ከዚህ ጥፋትየሚያወጣት ‘የኖህ መርከብ’
ያስፈልጋታል። ሳይንቲስትሻጊዝ እጅጉ ሀገሩን ከፍፁማዊ ጥፋት
ለማዳን ‘የኖህመርከብ’ን ከሚገነቡላት አንዱ ነው። እና ህወሃት
‘የኖህመርከብ’ ከመታነፁና ከማለቁ በፊት አናፂውን
ሳይንቲስትሻጊዝን እና ባልደረቦቹን ማጥፋት አለበት…
ኢንጂነርሳይንቲስት ሻጊዝ እጅጉ ተከቧል፤ በማንኛውም
ሰዓትከከባቢዎች በአንዱ ህይወቱ ልትጠፋ ትችላለች…
ሻጊዝእጅጉ ግን ራዕይ አለው፤ ለሀገሩ ብርሃን
የሚፈነጥቅከድህነትና ከአምባገነኖች የሚያላቅቅ ራዕይ አለው…
መንገደኛ ነው ሻጊዝ፤ ሩቅ አላሚ…ሩቅ ተጓዥ…እንቀንጭብ
ከዴርቶጋዳ፤
“…ኢትዮጵያ መጪው ትውልድ ከፍሎ የማይጨርሰውብድር
ተበድራለች። እያንዳንዱ ወጣት እያንዳንዱ ታዳጊየሚወርሰው
ሌላ ነገር የለም።…የገንዘብ ዕዳ፤ የሞራልዕዳ፤ የደም ዕዳ…
ኢትዮጵያውያን ነዳጃቸው ላይ ቆመውእየለመኑ ነው።
ኢትዮጵያውያን ዩራኒየማቸው ላይ ቆመውነዳጅ አጥሯቸዋል።…
የኢትዮጵያ ጥቋቁር አልማዞች ጥቁርአልማዛቸው ላይ ቆመው
እየተመፀወቱ ነው…ወንድሜሚራዥ…እኔና አንተስ እስከመቼ
ዝምእንላለን?..እስከመቼ ድረስ ዳር እንቆማለን?”
ሳይንቲስትሻጊዝ እጅጉ ለዶ/ር ሚራዥ የተናገረው ያገጠጠ
ሀቅሰውነታችንን እንደ ኤሌክትሪክ ንዝረት ሲወረውይሰማናል።
ጥያቄው ለኛም መሆኑ ይከሰትልናልና።
ሻጊዝ የሚናገረው የእያንዳንዳችንን ዐይነ ውሃ
እየተመለከተእንደሆነ ሁሉ ይሰማንና – ሀገራችን ኢትዮጵያ
በዘመነህወሃት ምዝበራዋና ፍዳዋ፤ ሰቆቃዋና የደም ዕዳዋ
ገዝፎበጣዕር ድምፅ ስትጠራንና ዓይኖቿ የመከራ ዘመን
ልጆቿንመድህንንት ለማግኘት ሲንከራተቱ ይታየንና…
በእስከዛሬው‘የምንቸገረኝ’ ምግባራችን ሀፍረቱ ያሸማቅቀናል።
ስለምንእኛ ልንወጣው የሚገባንን ዕዳ ለመጪው
ትውልድለልጆቻችን እናስተላልፍላቸዋለን? ስለምን ያለዕዳቸው
ዕዳእንሰጣቸዋለን? ዝምታችን የሚያበቃውስ መች ይሆን?
እስከመቼ በዚህ እንዘልቃለን?…እንላለን ለራሳችን፤ህሊናችን
ሲወቅረን እየታወቀን…
እንመለስ ወደ ዴርቶጋዳ ትረካ፤
“እስከመቼ!” አለ ሚራዥ ውስጡ ተቃጥሎ። “እኔ በበኩሌከአሁኗ
ደቂቃ ጀምሮ ማንኛውንም ተግባር ለመፈፀምዝግጁ ነኝ። ግን
ምን ማድረግ እችላለሁ? የችግሩ ሰንሰለትተቆርጦ የማያልቅ
ነው። የሰው ሀይልና በቂ ገንዘብያስፈልጋል።” ይህ የሚራዥ
ጭንቀት ቀልባችንንይስበዋል። ዕውነቱን ነው ሚራዥ እንላለን
“ምን ማድረግእንችላለን?” – እናስተጋባለን እኛም የሚራዥን
ጥያቄ።
“ዕውነት አይደለም” ይላል ሳይንቲስት ሻጊዝ –
ለሚራዥምለኛም። “በቂ ገንዘብ ብቻ አይደለም የሚፈልገው።
ብዙህዝብም አይደለም የሚፈልገው። ልብ ለልብ
ከተገናኘንናአብረን ከሰራን እንኳንስ አንዲት ሀገር ዓለምን
መለወጥየሚያስችል ዕውቀትና አቅም አለን…”
ዕቅጩንይነግረናል ሻጊዝ፤ ለዶ/ር ሚራዥ ብቻ ሳይሆን በቀጥታ
ለኛየሚመልስልን እስኪመስለን…
“…ይልቅ እኔም አንተም ሞት ሳይቀድመን ወገኖቻችንንከሞት
የምንታደግበት ወቅት ላይ ነን።…ኢትዮጵያ ተስፋበቆረጡ
ወጣቶች ተሞልታለች። ራዕይ ያጡ ህዝቦችጎተራ ሆናለች።
ራዕይ የሌለው ህዝብ ደግሞ ይጠፋል።የተስፋው መስኮት
መከፈት አለበት። ኢትዮጵያን ሌላሰው መጥቶ አይለውጥልህም።
አንተን ለመለወጥ ሌላሰው አይመጣም። ይህን ሀቅ እወቅ።
ኢትዮጵያ ውስጥሿ ብትን የሚሉት ቻይናዎችና አረቦች ሁሉ
ለአንተብልፅግና ግድ የላቸውም። ሀገርህን
ከቅጥረኞችናከወሮበሎች የምታድንበት ጊዜው አሁን ነው።”
“አንድ ጥያቄ እንድጠይቅህ ፍቀድልኝ” አለው ሚራዥ
“ጠይቀኝ…”
“ወደ ጦር ሜዳ እየላከኝ ነው?”
* * *
ይህ የሻጊዝና የሚራዥ ምልልስ አንዳች ልዩ ስሜትንበውስጣችን
ሲያቀጣጥል ይሰማናል። ተስፋ ይታየናል። ያምተስፋ
የሚጀምረው ከራሳችን እንደሆን ስንገነዘብም በራስየመተማመን
ስሜታችን ከውስጣችን ሲንር ሲንተገተግ፤ችቦው ሲለኮስ
ይታወቀናል። ዕውነት ነው እንላለን፤ ራዕይየሌለው ትውልድ
ተስፋ የለውም፤ ተስፋ ከሌለውበመንፈስም በምግባርም
የጠወለገ ትውልድ ይሆናል፤የጠወለገ ትውልድ ደግሞ እያዘገመ
ይሞታል። እና ጊዜውአሁን ነው እንላለን። ሀገራችን ማጥ ውስጥ
የገባችውናእንዲህ ያለው አሳዛኝና አደገኛ ደረጃ ላይ የደረሰችው
በኛውትውልድ ነው። ተስፋ በቆረጠና ራዕይ በራቀው
ወጣትትውልድ ለመሞላቷ አንዱ ምክንያት እኛ
በእድሜየሰነበትነው (በ1966 ዓ/ም አብዮት ፍንዳታና ማግስት
ወስጥየተሳተፍነው/ባንሳተፍም የኖርነው) ትውልድ አካላት
ነን፤አንድም በዝምታችን አንድም በጥፋት ተባባሪነታችን።
አዎ እውነት ነው! ኢትዮጵያን ሌላ ስው መጥቶአይለውጥልንም።
ኢትዮጵያ በሀራጅ እየተሸጠች ነው፤ለቻይናው ለህንዱ ለአረቡ።
ኢትዮጵያውያን በገዛ ሀገራቸውባይተዋርና ባርያ፤ በምርታቸው
የበይ ተመልካች ሆነዋል።የደደቢቱ ህወሃት ክፉ አገዛዝ
የኢትዮጵያን ለም መሬትየሚቸበችብላቸው ባዕዳን ሌት ተቀን
የኢትዮጵያን አንጡራሀብት የሚጭኑት ወደ ሀገሮቻቸው እንጂ
ለኢትዮጵያውያንዕድገትና ብልፅግና በሚውልበት መንገድና
ስምሪትበኢትዮጵያ ምድር አይደለም። ዘርፎ ለዘራፊ በሯን
በርግዶበከፈተው ወንጀለኛና ወሮበላ የህወሃትና
ህወሃታውያንአገዛዝ አዝማችነት ዓለም አቀፍ የምዝበራ
ቡድናትኢትዮጵያን በያቅጣጫው እየተቀራመቷት ናቸው።
ማንከእኛ በቀር ሊያድናት ይችላል?…ከእኛስ በቀር ማን
ህይወቱንገብሮ ኢትዮጵያን ሊታደጋት ይችላል?
እንቀጥል ቅኝታችንን፤
የሻጊዝ ራዕይ ወዴት ያመራ ይሆን? የሚራዥስተልዕኮ?…ዴርቶጋዳ
ሴራውና ታሪኩ እንደ ሸረሪት ድርእየተወሳሰበና እየሰፋ፤ ከድርጊት
ወደ ድርጊት ከምሥጢርወደ ላቀ ምሥጢር ሲወነጨፍ፤
ልባችንም አብሮእየተወነጨፈ ይነጉዳል…
እንቀንጭብ ከትርክቱ ሂደት፤
እነሆ በጃንዋሪ 13፤ 2006 ከኦስቲን ቴክሳስ ታላቅ የሀዘን
ዜናበዓለማችን ህዋ ላይ ተናኘ፤ የሳይንቲስት ሻጊዝ እጅጉ ሞት።
ሳይንቲስቱ ፊቱን ወደ ድሃ ሀገሩ በመለሰና ሀገሩን
ከጥፋትለመታደግ የፖለቲካ መዋቅር ባቆመ በሁለት ዓመት
ውስጥ፤‘ኢትዮጵያዊው የህዋ ሳይንቲስት ሻጊዝ እጅጉ በተወለደ
58 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል’ – አሉን
አሜሪካኖቹ።እልል አለ የህወሃት/አህአዴግ አገዛዝ፤ እፎይ ብሎ
ተነፈሰ፤ሻጊዝን አድነው እንዲያጠፉለት የላካቸው ነፍሰ
ገዳዮችበእጃቸው የሳይንቲስቱን እስትንፋስ እንዳቆሙለት
ሁሉእየተሰማው። ይህ እውነት ነው፤ ሻጊዝ ሞቷል።…
ግናሳይንቲስት ሻጊዝ እጅጉ ዕውን የሞተው ተፈጥሯዊ
ሞትነውን?! ዴርቶጋዳ ስለሻጊዝ ሞትና ከሞት ወዲያ
ባለውህያው ህይወቱ ቀልባችንን ሰድሮ፤ ሀዘናችንን አስውጦ…
ውስብስቡን ታሪክ እያፍታታ…ያልተገለጠልንንእየገላለጠልን
ትረካው ይንቆረቆራል…ምሥጢሩምይበራያል…
* * *
ሳይንቲስት ኢንጂነር ዶ/ር ሻጊዝ እጅጉ አልሞተም፤በዴርቶጋዳ፤
በዴር 33፤ በዳጋ እስጢፋኖስ ገዳም ከርሰምድር፤ በምድረ
ኢትዮጵያ፤ ዘላለማዊ ህያውነትንተቀዳጅቷል። እንዴት? ለእኒህና
ለሌሎችም የዴርቶጋዳምሥጢራት…ዴርቶጋዳን ማንበብ ብቻ
ይሆናልመፍትሄው። ቁንፅል ስዕላዊ ቅኝታችን ግና ይቀጥላል፤
አባ ዠንበሩ በሳይንቲስት ሻጊዝ እጅጉ ውስጥ ህያውሆነዋል።
ለኢትዮጵያ ክብር፤ ልዕልና እና ብልፅግና ህልምየነበራቸው።
ነፃነቷን፤ ታሪኳንና ቅርሷን ጠብቀው ያቆዩንአባቶቻችን ተምሳሌ
ናቸው አባ ዠንበሩ። እና ሳይንቲስትሻጊዝ የአባ ዠንበሩን ህልም
ዕውን አደረገና ሞተ። …አባዠንበሩም ሞቱ፤ ህልማቸውና
ራዕያቸው ግን አልሞተም።
አዎ ሳይንቲስት ሻጊዝ ሞቷል፤ ዓርማው ግን አልወደቀም።በዶ/ር
ሚራዥ፤ በሞሳዷ ሲራጳ፤ በአሜሪካ አየር ሀይልውስጥ ዝነኛ
አብራሪ በነበረው ጌራ፤ በቁጥር ሁለትየዴርቶጋዳ ኢትዮጵያውያን
ሳይንቲስቶችና ምሁራን፤ በዴር33 ራዕዩ ዛሬም አለ። እኒህ ሁሉና
በዚህ ቅኝት ያላነሳናቸው የዴርቶጋዳ ገፀ ባህርያት በታሪኩ
ውስጥ ባላቸው ሚና እናሰብዕና ዕውቀትና ተልዕኮ አንባቢን
በስሜት ማዕበልእያናጡ፤ በታሪኩ መርከብ እያንሳፈፉ፤ ከምዕራፍ
ምዕራፍእሚያስፈነጠሩ ናቸው…
ዴር 33 በሳይንቲስት ሻጊዝ የተነደፈች በዴርቶጋዳጥበበኞች
ህልውና ያገኘች፤ እንደ መኪና በየብስ እንደአሞራ በሰማይ
የምትበር የተራቀቀች የዴርቶጋዳ ውጤትናት። ዴር 33 የዴርቶጋዳ
አባላት ራዕይ ተምሳሌ ናት። ዴር 33 የሳይንስ ልቦለድ ናት
አትበሉ። ሻጊዝ እጅጉ ዛሬ ዓለምየሚገለገልበትን ጂ ፒ ኤስ
(አቅጣጫ አመልካች) አልፈለሰፈምን? ታዲያ ዴር 33 እንደምን
የሳይንስ ልቦለድብቻ ልትሆን ትችላለች? ዴር 33 ራዕያችን ናት፤
የአባዠንበሩ ራዕይ፤ የሻጊዝ ራይዕ፤ የኢትዮጵያ ወጣትትውልድ
ራዕይ…
ይልቅስ ለዚህች ልዩ የዚህ ትውልድ ራዕይ 33 ቁጥር
ለምንመታወቂያዋ ሆነ? አዎ! ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን
ልጅከዘመናት የዲያቢሎስ ባርነት ነፃ ሊያወጣ
ከሀጢያቱምሊያነፃው ራሱን አሳልፎ በመስቀል ተቸንክሮ የሞተው
በ33 ዓመቱ ነበር።…እና የዴር 33 ተምሳሌነት ይህ
ወጣትትውልድ የሀገሩ መድህን፤ የሀገሩ ትንሳኤ፤ የሀገሩ
ራዕይሆኖ ሀገሩን ይታደጋት ወገኑኑም ከናዚስት ህወሃትባርነት ነፃ
ያወጣ ዘንዳ…አመልካች ትሆን? ማለታችንግን አልቀረም።
ልጅ በአባቱ ሀጢያት አይኖርም
አባ ፊንሐስ ወንጀለኛ ናቸው። አባ ፊንሐስ ከሀገራቸውብሶትና
ሰቆቃ ይልቅ ግላዊ ህይወታቸው
የሚደላደልበትንናየሚከብሩበትን ህልም ሲያልሙ – ለዚህም
ደፋ ቀና ሲሉየኖሩ አባት ናቸው። አባ ፊንሐስ መንፈሳዊ
አባትነታቸውለአለማዊ ህይወታቸው ካባ ሆኖ የሸፈነላቸው
አባትናቸው።…እንዲህ ያሉ አባ ፊንሐሶች በየትውልዱ
ሁሉተፈጥረዋል፤ ነበሩም። ዛሬም ናዚስት ህወሃትን
አገልጋዮችብዙ አባ ፊንሐሶች ሞልተዋል…የዴርቶጋዳው አባ
ፊንሐስለኒህ ሁሉ ተምሳሌያዊ ገፀ ባህሪ ናቸው።
አባ ዲዲሞስ ሩቅ ተጓዥ ራዕይ የነበራቸው አባት ነበሩ።አባ
ዲዲሞስ አዋቂ ናቸው፤ የተማሩ። የአባ ዲዲሞስራዕይና
ዕውቀት ግና በሥልጣን አባዜ ተሸበበ፤ ታወረ።አቡነ ጵጥሮስን
የተቃወሙትም ለዚሁ ነበር – ሥልጣንንበእሳቸው በኩል
ማግኘት ከመቻላቸው በፊት ስለሞቱ። እናአባ ዲዲሞስ
ዕውቀታቸውንና ሩቅ ተጓዥ ራዕያቸውንለሥልጣን አባዜ የሸጡ
አባቶቻችን ሁሉ ተምሳሌ ናቸው።በየትውልዱ ብዙ አባ
ዲዲሞሶች ተፈጥረው አልፈዋል፤ዛሬም በዚህ ትውልድ ውስጥ
የናዚስት ህወሃት አገልጋይየሆኑ አያሌ አባ ዲዲሞስ ምሁራንም
ተናኝተው ይገኛሉ…
የሞሳዷ ሲጳራ የአባ ፊንሐስ ልጅ ናት። ሲጳራ ግን በአባቷወንጀል
አልኖረችም። ጌራ እና ሞረዳ የአባ ዠንበሩን ራዕይአንግበዋል።
ሚራዥ በአባቱ ፈለግ ተተክቷል። ሁሉምየሳይንቲስት ሻጊዝን
አርማ አንስተዋል። ነገ ሌላ ቀን ነው፤ነገ በኢትዮጵያ አዲስ ቀን
ይወጣል…
እኒህ ምርጥ ወጣቶች በዴርቶጋዳ የምናገኛቸው የዚህትውልድ
ተምሳሌት ናቸው። እኒህ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ ገንቢወጣቶች
በአባቶቻቸው ሀጢያት አይኖሩም። በአባቶቻቸውራዕይ እንጂ!!
ኢትዮጵያን ዛሬ ናዚስት ህወሃትና በ አምሳሉ የፈጠራቸው
ህወሃታውያን ከከተቷት መቀመቅየሚያወጣትም ይህ ወጣት
ትውልድ ነው። ይነሳል ክንዱንአጠንክሮ፤ በኢትዮጵያዊነቱ
ተባብሮ! ያውለበልባልአረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራውን ከፍ አርጎ!
ይዘምራልበህብረ ድምፅ፤ ከአድማስ አድማስ ያስተጋባል…ይላል
ኦርያኢትዮጵያ!…ማሔር ሻላል ሐሽ ባዝ!!
መሸበቢያ
ክብር የእግዚአብሄር ነው። ምሥጋናም በእግዚአብሄርይሰምራል።
አስጀምሮ ላስጨረሰኝ ዴርቶጋዳ – ለብላቴናውይስማዕከ ወርቁ
– ክብር ምሥጋናዬ በላይኛው ፈጣሪ ስምባለህበት ይድረስህ።
በነገይቷ ኢትዮጵያ መፃዒ ዕድልበወጣቱ ትውልድ ራዕይ ተስፋ
ሰጥተኸናልና…ፀሎታችንእውን ይሆን ዘንድ እንማልዳለን።
እነሆ ተስፋችንን በዴርቶጋዳ ከውስጣችንእንደቀሰቀስከው፤
የላይኛው መልዕክተኛ መልዐክምበውድቅት ሌሊት፤ በድቅድቅ
ጨለማ ከተኛህበት መጥቶደግሞ ደጋግሞ ይቀስቅስህ።
ከራስጌህም ቆሞ መለኮታዊብርሃኑን ያብራልህ። ከክንፉም ላባ
ነቅሎ፤ እንደ ብዕርምቀርፆ በእጅህ ያስጨብጥህ። መለኮታዊ
የኢትዮጵያ ትንሳዔመልዕክቱም በመላዕክት ልሳን ይገለጥልህ።
በብራናህምትከትበው ዘንዳ – ተስፋ ላጣው ለተስፋይቱ ምድር
ህዝብተስፋ ትናኝም ተስፋም ታዳርስ ዘንዳ ደግመህ
ደጋግመህፃፍ። ዛሬም ነገም ለዘለዓለሙ – አሜን!
risingethio

Friday, February 12, 2021

አድዋ



ምኒሊክ ተወልዶ ባያነሣ ጋሻ
ግብሩ እንቀላል ነበር ይሄን ጊዜ አበሻ፤
***
ገበየሁ ቢሞት ተተካ ባልቻ
መድፍ አገላባጭ ብቻለብቻ፤
***
የአድዋ ሥላሴን ጠላት አረከሰው
ገበየሁ በሞቴ ግባና ቀድሰው፤
የአድዋ ድል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ክብር ማኅተም፤
የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ተጋድሎ ቀንዲል ነው፡፡ የመላው
ዓለም ተፈጥሮአዊ ግብር እና ሰብአዊ ክብር የታደሠው፤
በእውነትና በፍትህ ህልውናና ምልዓት ላይ የተሰካ ትልቅ
ጥርስ የተነቀለው … በአድዋ የታላቅ ህዝቦች ታላቅ ድል
ነው፡፡
ከአዲስ አበባ ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ ስንሄድ 1066 ኪሎ
ሜትር ርቀት ላይ ታላቁ ጦርነት የተደረገበትና ታላቁ ድል
የተገኘበት ሥፍራ አድዋ ከተማና የከተማው ግድም
ገመገሞች ይገኛሉ፡፡ በኢትዮጵያውያን አቡሻኽር (Julian
calendar) የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም፤ ወይም
በአውሮጳውያን የዘመን አቆጣጠር (Gregorian
Calendar) February (የካቲት) መጨረሻ እና March
(መጋቢት) መጀመሪያ ላይ 1896. ለጦርነቱ መነሻ
የሆነው ውል የተፈፀመው በዚሁ ዘመን ከአዲስ አበባ
በስተሰሜን 468 ኪሎ ሜትር ርቀት ግድም ከውጫሌ
ከተማ ግርጌ ከአምባሰል ተራራ ሥር ወሎ ውስጥ ንጉሥ
ይስማ እየተባለ በሚጠራ ሥፍራ ነው፡፡
ሸልዶ ተራራ ወይም (ሶሎዳ ተራራ)፤ ማርያም ሸዊቶ፤
አዲ ተቡን፤ ረቢ አርእየኒ (እግዚሃር አሳየኝ)… በመሠኘት
የሚታወቁት እነዚህ ገመገሞችና ተራራማ ሥፍራዎች
ዋነኞቹ የጦር ግንባሮች ናቸው፡፡ በመቶ ሺህ የሚሠላ
የኢትዮጵያ ገበሬ ሠራዊት ከአንድ ቀን ባልበለጠ ጊዜ
ውስጥ የአውሮጳ ቅኝ ገዢ ወራሪዎችን ድባቅ ከመታና
ረግጦ ካስወጣ በኋላ ከምሽቱ አራት ሰዓት ግድም
(የካቲት 23 ቀን) እንዳማርያም ላይ ተሰባስቦ በአንድ
እግሩ ቆሞ ቀኙን (ድሉን) ለሰጠው አምላክ ምሥጋና
አቅርቧል፡፡ አባት ሆይ፤ ንቀውን የመጡ የአገራችንን
ድንበርና ልዕልና የደፈሩ የአውሮጳ ኮሎኒያሊስት
ወራሪዎችን እንድናሸንፍ (ድል እንድናደርግ) ስለረዳኸን
እናመሰግንሃለን ...
ሃያ ዘጠኝ ሺህ ፈረሰኞችን ጨምሮ ከመቶ ሺህ እስከ መቶ
ሃያ ሺህ የሚገመት አንድ ሺህ ኪሎ ሜትር በባዶ እግሩ
የተጓዘ የኢትዮጵያ የገበሬ ሠራዊት በወታደራዊ አካዳሚ
የሠለጠነውን የአውሮጳ ወራሪ ጦር የካቲት 23 ማለዳ
አሥራ አንድ ሰዓት ግድም ገጥሞ ከረፋዱ አራት ሰዓት
ላይ ማሸነፉን አረጋግጧል ይለናል የታሪክ ተመራማሪው
ጆርጅ በርክሌይ የአድዋ ጦርነትና ዳግማዊ አፄ ምኒሊክ
በተሰኘና ዳኘው ኃይለሥላሴ ወደ አማርኛ በተረጐሙት
መጽሐፉ ላይ፡፡ የኢትዮጵያ ገበሬ ሠራዊት ፈረሱ ላይ ሆኖ
የጋሻውን እምብርት መሬት ላይ እያጠቀሰ ጐራዴውን
አየር ውስጥ እየቀዘፈ ባበደ መንፈስ (በተቆጣና በቆረጠ
መንፈሥ) በጀግንነት ተዋግቷል፡፡
ጦርነቱ በተጀመረ ከአምስት ሰዓት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ
ሃምሣ ስድስቱም የኢጣሊያ መድፎች ሙሉ ለሙሉ
ተማርከዋል፤ የቅኝ ገዢውን ወራሪ ሠራዊት ከመሩት
ጀኔራሎች ጄኔራል አልቤርቶኒ ሲማረክ የሠራዊቱ ዋና
አዛዥ ጄኔራል ባራቴሪ ከጥቂት አጃቢዎቹና በሽንፈት
ከተበታተኑ የኢጣሊያ ወታደሮች ጋር ሸሽቷል፡፡
በዚህ ድብልቅልቅ ያለ ውጊያ ከሃምሣ ስድስቱ የኢጣሊያ
መድፎች በተጨማሪ ብዙ ሺህ ቀላልና ከባድ መትረየሶች
እንዲሁም የነፍስ ወከፍ ጠመንጃዎች በአሥር ሺሆችና
በመቶ ሺዎች ከሚቆጠሩ መሰል ጥይቶቻቸው ጋር
ተማርከዋል፡፡ በአጠቃላይ ምርኮው ወደ አዲስ አበባ
የተጓጓዘው በአምስት መቶ አጋሰሶች ተጭኖ ነው፡፡
በማግስቱ የካቲት 24 ቀን 1888 ዓ.ም ከጠዋቱ አራት
ሰዓት ላይ የኢጣሊያ ምርኮኞች በምኒሊክ ድንኳን ፊት
ሲያልፉ የኢትዮጵያ ጀግና የገበሬ ሠራዊት እየፎከረ
እየሸለለ አሳልፉዋቸዋል፡፡ ጄኔራል አልቤርቶኒ
በምርኮኛነት ኢትዮጵያ ውስጥ ቆይቶ አገሩ ከተመለሰ
በኋላ በፃፈው መጽሐፍ ላይ ከሚፎክሩት ጥቁር የነፃነት
ተዋጊዎች መሃከል አንዱ እንደ እኛው ነጭ አውሮጳዊ ነው
ብሎአል፡፡ ይህ ሰው ከፈረንሣይ አገር ወደ ኢትዮጵያ
ለጦር መሣሪያ ጥገና የመጣ ካፒቴን ኦርዲናንስ ሲሆን፤
አሁን ጊዜው የጦርነት ስለሆነ ወደ አገርህ ተመለስ ቢባል
ቢሠራ አሻፈረኝ ብሎ ከእኛ ጋር አድዋ ድረስ የዘመተ ነው፡፡
ኢትዮጵያ በአድዋ ጦርነት ላይ ከተዋጋችባቸው የጦር
መሣሪያዎች ሠማንያ ሺህ የሚሆኑት አሮጌ ጠመንጃዎች
የተገዙት ከፈረንሳይ አገር በምሥጢር ነው፡፡
ጠመንጃዎቹን ገዝተው ወደ ኢትዮጵያ ያስገቡት
ለመጀመሪያ ጊዜ መኪና ወደ ኢትዮጵያ ያስገቡት በሥጋ
በደምና በትውልድ አርመናዊ በነፍስና በመንፈስ
በዜግነትና በልብ ፍቅር ኢትዮጵያዊ የሆኑት የኢትዮጵያ
የልብ ወዳጅ ሰርኪስ ቴሪዝያን ናቸው፡፡
አሁን በመዲናችን የሚገኘው የአርሾ ላቦራቶሪ ባለቤትና
በዓለም ላይ ኢትዮጵያን የመሰለ ውብ አገር የለም ያሉኝ
ዶክተር አርሻቪር ቴሪዝያን ኢትዮጵያ ውስጥ አርመናዊ
ትውልድ ኖሮት ኢትዮጵያዊ ዜግነት የሌለው (ኢትዮጵያዊ
ያልሆነ) አርመን ያለመኖሩን ያጫወቱኝ ከአሥራ አምስት
ዓመታት በፊት ነው፡፡ የሠማንያ ሺህ ጠመንጃዎቹን አገዛዝ
ሁናቴ የሚያውቁት ደግሞ ከአርሾ ቀደም የሚሉትና
ከአሥራ ስድስት ዓመታት በፊት ለሪፖርተር ጋዜጣ ይሄንኑ
በአንደበታቸው የገለፁት አቬዲስ ቴሪዝያን ናቸው፡፡
ሠርኪስ ቴሪዝያን ጠመንጃዎቹን ከገዙ በኋላ ወደ
ኢትዮጵያ ያስገቡት በጅቡቲ በኩል ነፋስ ባህሩን ሲያነሳና
እንደ ግድግዳ ሲያቆም በዚያ ተፈጥሮአዊ ክንውን
በመጠቀም ደብቀውና ሸሽገው ነው፡፡
የአድዋ ድል ለመጀመሪያ ጊዜ የተከበረው በሠባተኛ
ዓመቱ በ1895 ዓ.ም (እ.ኤ.አ በ1903) ከአንድ መቶ
ዘጠኝ ዓመታት በፊት አሁን ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን
ያለበት ሥፍራ ምኒሊክ አደባባይ ነው፡፡ በክብረ በዓሉ
(በድል በዓሉ) ላይ ዲፕሎማቶችና የውጪ አገር
መንግሥታት ተወካዮች አርበኞች የመንግስት
ባለሥልጣኖች ብዙ ሺህ ፈረሰኞችና ሥፍር ቁጥር (ወፈ
ሠማይ የሆኑ) ኢትዮጵያውያን ከሊቅ እስከ ደቂቅ
መገኘታቸውን፤ ከፈረሰኞቹ ብዛት የተነሳ ፀሐይ በአቧራ
እስከመጋረድ መድረሷን ጳውሎስ ኞኞ የኢጣሊያና
የኢትዮጵያ ጦርነት በተሰኘ መጽሐፉ ላይ ጽፎአል፡፡
እንዲሁም ተክለፃዲቅ መኩሪያን የመሳሰሉ ኢትዮጵያውያን
የታሪክ ተመራማሪዎችና የውጪ አገር ዜግነት ያላቸው
ፀሐፍትና ተመራማሪዎች በተለያዩ መፃሕፍቶቻቸው ይሄንን
አሣምረው ጽፈውታል፡፡
ታላቁ የጥቁር ህዝቦች ድል (የአድዋ ድል) በመላው
ዓለም ፖለቲካ ላይ ከፍተኛና ዋነኛ ለውጦች
አምጥቶአል፡፡ የእንግሊዝ ጋዜጦች በአድዋ ድል ማግስት
የዓለም ታሪክ ተገለበጠ ታላቅ የትውልድ ኃይል በአፍሪቃ
ተቀሰቀሰ … ብለው ፃፉ፡፡ በኢንሳይክሎፒዲያ ብሪታኒካ፡-
ዘመናዊት ኢትዮጵያን የፈጠረ የተባሉት ዳግማዊ ዓፄ
ምኒሊክ በሌሉበት (እርሳቸው በአካል ባልተገኙበት
የነፃነት ተጋድሎ መሪዎች ጉባኤ) የአፍሪቃና የመላው
ዓለም ጥቁር ህዝቦች የነፃነት ተጋድሎ መሪ ተደርገው
ተመረጡ፡፡
ጦርነቱ ከመደረጉ በፊት እ.ኤ.አ በ1880ዎቹ መጀመሪያ
ጀርመን አገር በርሊን ከተማ ላይ በተደረገው የአውሮጳ ቅኝ
ገዢ (ኮሎኒያሊስት) መንግስታት ሥልጣናትና ልሂቃን
የጦር ጄኔራሎችና ሊቃውንት ስብሰባ ላይ ጥቁር ትልቅ
ትል ነው ቅንቡርስ ነው እንጂ ነፍስ ያለው ሰው አይደለም
ብለው የነበሩ አፈሩ፤ እውነትና ፍትህ ኢትዮጵያና አፍሪቃ
ከበሩ፡፡ ከሲግመንድ ፍሮይድ የሳይኮ አናላይሲስ ጥናትና
ምርምር በፊት፡- ጥቁር ህዝብ ትልቅ ትል ላይሆን ነፍስ
ያለው ሰው ከሰውም ሰው ጀግና መሆኑን በተጨባጭ
ያስመሰከረ የኢትዮጵያ ገበሬ ሠራዊት ነው፡፡
ከፈረንጅ የአውሮጳ መንግሥታት ሩሲያና ፈረንሳይ
የአድዋን ድል ከልብ ደገፉ፡፡ ጀኔራል ባራቴሪ በአገሩ
በኢጣሊያ ጦር ፍርድ ቤት ቀርቦ ማዕረጉ ተገፈፈ፡፡
የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሲኞር ክሪስፒ በፈቃዳቸው
ሥልጣናቸውን ለቀቁ፡፡
የኢጣሊያዊው ንጉሥ አማኑኤል ኡምቤርቶ የልደት ቀን
የሀዘን ቀን እንዲሆን ተወሰነ፡፡ ሮማ (ሮም)ን ፍሎሬንስን
ሚላኖ (ሚላን)ን ቬነስን…የመሳሰሉ የኢጣሊያ ከተሞች
ምኒሊክ ለዘላለም ይኑር በሚሉ የተቆጡ አውሮጳውያን
ትዕይንተ ህዝብ አድራጊዎች ተጥለቀለቁ፡፡ ኢትዮጵያ
በአድዋ ጦርነት ወቅት በዋናው የጦር ግንባር ገጥማ
በፍልሚያ ድል ማድረግ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ በአራት
መስክ ሠለጠነች በምትባለው አውሮጳዊት አገር ኢጣሊያ
ላይ ድል ተቀዳጅታለች፡፡ ይኸውም፡- በጦርነት እና
በወታደራዊ መረጃ (Military Security
intellegence)፤ በዲፕሎማሲና በፖለቲካ ጥበብ ነው፡፡
በፖለቲካ ጥበብ በኢጣሊያ ቅኝ ገዢ ብልጣብልጥ
የመንግሥት ሥልጣን ላይ ድል የተቀዳጀችው ገና ጦርነቱ
ሳይጀመር ለጦርነቱ መጀመር መነሻ የሆነው የውጫሌ
ውል በተደረገበት ሥፍራ ነው፡፡
የውጫሌ ውል አንቀጽ አሥራ ሰባት የጣሊያንኛው፡-
ኢትዮጵያ ከአውሮጳ መንግሥታት ጋር ማድረግ
የምትፈልገውን ግንኙነት በኢጣሊያ መንግስት በኩል
ማድረግ አለባት ሲል፤ አማርኛው ደግሞ ኢትዮጵያ
ከአውሮጳ መንግሥታት ጋር ማድረግ የምትፈልገውን
ግንኙነት በኢጣሊያ መንግሥት በኩል ማድረግ ትችላለች
ይላል፡፡
የአማርኛው የኢትዮጵያን ሉአላዊነትና ልዕልና ያከብራል፤
የጣሊያንኛው የኢትዮጵያን ሉአላዊነትና ልዕልና መድፈር
ብቻ ሳይሆን ብሔራዊ ክብሯንና ጥቅሟን ይነካል፡፡ ይሄን
የተገነዘቡት የኢትዮጵያ መሪዎች የውሉ አንቀጽ አሥራ
ሰባት የጣሊያንኛ ትርጓሜ የኢትዮጵያን ክብርና ጥቅም
በማይነካና ሉአላዊነቷን በሚያከብር መልኩ
እንዲስተካከል በተደጋጋሚ ወተወቱ፡፡ መወትወቱ ውጤት
ሳያመጣ ቢቀር፤ ምኒሊክ፡- መዘግየት አደገኛ ነው ጣይቱ
አሉ፤ ስለዚህ ጉዞ ወደ ወሳኙ ጦርነት (ማድረግ) የግድ
ነበር፡፡
የኢትዮጵያን አገራዊ ክብርና ጥቅም ህልውናና ልዕልና
ሲሆን ሲሆን በውድ ካልሆነ ደግሞ ሳይወድ በግድ
ማስከበርና ማስጠበቅ የአንድ አገር መንግሥት ዋነኛ
ግዴታና ኃላፊነት ነው፡፡
ስለዚህ አባቶቻችን (የጥንት ወላጆቻችን) ውትወታቸው
አልሰማ ቢል ጦር እንግጠም አሉ፡፡
ይሄ የፖለቲካ ጥበብ ብልጫ ወይም ድል ነው፡፡
በወታደራዊ መረጃ (Military Security
intellegence) ብልጫ የኢንቲጮ ተወላጅ በሆኑት
ባሻዬ አውአሎም ሀረጐት አማካይነት ኢትዮጵያ ሠለጠነ
የተባለውን የአውሮጳ ኃይል አሸንፋ ጣሊያኖች ባልፈለጉት
ቦታና ባልመረጡት ጊዜ ወደ ጦርነት እንዲገቡ
አድርጋለች፡፡
በወታደራዊ ሣይንስ (Military Science) አገባብ
ለጦርነት የተንቀሳቀሰ አንድ ሠራዊት ወዲያውኑ ወደ ጦር
ግንባር መግባት አለበት፡- ይሄ አንድ ነጥብ ነው፡፡ ሌላው
ነጥብ አንድ ለግዳጅ የተንቀሣቀሠ ሠራዊት ለመሰናዶም
ሆነ ለመከላከል ውጊያ በአንድ የመከላከያ ወረዳ ከሠፈረ
በዚያ መከላከያ ወረዳ ከስድስት ወራት በላይ መቆየት
የለበትም፡፡ በአንድ ቦታ ላይ ከስድስት ወራት በላይ ከቆየ
ሊደርስ የሚችል የወታደራዊ ሥነልቦና (Military
Psychology) ጉዳት አለ፡፡ የመሸገበትን የመከላከያ
ወረዳ እየተለመማመደ ሲሄድ ስለሚዘናጋና የውጊያ
ስሜቱ እየቀነሰ (እየቀዘቀዘ) ስለሚመጣ ጉዳት አለው፡፡
ከሎጂስቲክ አኳያ የውጊያ ዝግጁነቱም አደጋ ላይ
ስለሚወድቅ (በሌላ አነጋገር ስንቅ እየጨረሰ ስለሚሄድ)
በነዚህ ምክንያቶች በአፋጣኝ ወደ ጦርነት መግባት
ለሠራዊቱ ድል አድራጊነት ትልቅ ጥቅም አለው፡፡
የኢትዮጵያ በሠላም ጊዜ ገበሬ በጦርነት ጊዜ ጀግና
ተዋጊ እንጂ ዘመናዊ ወታደራዊ መሠረት ያለው
Professional Army ባልነበራት በዚያ ዘመን ለአንድ
መቶ ሃያ ሺህ ሠራዊት የሎጂስቲክ አገልግሎት እየሰጡ
ለረጅም ጊዜ መቆየት አስቸጋሪ ነው፡፡ ስለዚህ የጀግንነት
ግለት ሳይበርድ የሎጂስቲክ (ስንቅ ትጥቅ መድሃኒት)
አቅም ሳይዳከም በፍጥነት ጦር መግጠም እጅግ
አስፈላጊ ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ሠራዊት ጦርነቱን ፈጥኖ
ለመግጠም ጣሊያኖች ወደ አድዋ መምጣት አለባቸው፤
ወይም ደግሞ የእኛ ሠራዊት ጣሊያኖች ወደመሸጉበት
የኤርትራ ከፍተኛ ቦታዎች መሄድ አለበት፡፡ ከነዚህ ሁለት
ሁኔታዎች የአንደኛው መሆን የግድ ነበር፡፡ ወደ ጣሊያኖች
መሄድ ከፖለቲካ ሁኔታዎች ባሻገር ከወታደራዊ ሳይንስ
አንፃር የሚመረጥ አይደለም፡፡ በምሽግ ውስጥ ሆኖ
የሚከላከል ሠራዊትና ከምሽግ ወጥቶ የሚያጠቃ
ሠራዊት መስዋዕትነት የመክፈል ዕድሉ እኩል አይደለም፤
ለሚከላከል አንድ ወታደር ሶስት የሚያጠቃ ወታደር ነው
የሚያስፈልገው፡፡
ስለዚህ ጣሊያኖች ወደ አድዋ እንዲመጡ ማድረግ የግድ
ሆነና የአድዋ ድል ቁልፍ የምላቸው የአርባ ዓመቱ
ጐልማሣ ባሻዬ አውአሎም ሀረጐት ተጠሩና ለአንድ ታላቅ
አገራዊ ኃላፊነት እንዲሠናዱ ተደረገ፡፡ ይሄ ሁሉ
በምሥጢር ነው የተከወነው፡፡ በሚቀጥሉት ቀናት
አውአሎም ለኢጣሊያ ኮሎኒያሊስት ወራሪዎች
ከሚሠልሉ የአገር ተወላጆች (ፌርማቶሪዎች) ጋር ወደ
ባራቴሪ ተላኩ፡፡ ከመሄዳቸው በፊት ስንቅ ማለቁና ተስቦ
በሽታ በሠራዊቱ ውስጥ መግባቱ ፌርማቶሪዎች ባሉበት
ተለፈፈ፡፡ አውአሎምና ፌርማቶሪዎቹ ወደ ኤርትራ ዘልቀው
ለጄነራል ባራቴሪ ይሄንኑ ነገሩት፡፡
ባራቴሪ ጊዜው አሁን ነው አለና የካቲት 22 አመሻሽ ላይ
በአውአሎም መሪነት ሠራዊቱን ይዞ ወደ አድዋ ተመመ፡፡
የካቲት 21 እንዳይነሣ ዝናብ ስለያዘው እንጂ ታላቁ
ጦርነት የካቲት 22 ሊደረግ ይችል ነበር፡፡ ስለዚህ ጄነራል
ባራቴሪ በዝናብ በመያዙ ምክንያት ዘመቻውን በማግሥቱ
አደረገና የካቲት 22 ቀን 1888 ዓ.ም ሌሊቱን ሙሉ ሲጓዝ
አድሮ ሊነጋ ሲል የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም አድዋ ጦር
ግንባር ደረሠ፡፡ አውአሎም ከፊት ለፊታቸው የጀግናው
የቱርክ ፓሻ የአፍሪቃ ጀኔራል አሉላ አባነጋ የገበሬ ሠራዊት
ምሽግ እንደታያቸው መሮጥ ጀመሩ፡፡ ባራቴሪ፡-
አውአሎም አውአሎም ብሎ ተጣራ፡፡ እስሀ ዝዋአልካዮ
አያውለና ብለውት ዘለው አሉላ ምሽግ ውስጥ ገቡ፡፡ ዛሬ
አንተን አያድርገኝ ማለታቸው ነው በአማርኛ፡- እስሀ
ዝዋአልካዮ አያውለና፡፡
ከጥቂት ደቂቆች በኋላ ምድር ቁና የሆነችበት ድብልቅልቅ
ያለው ጦርነት ተጀመረ፡፡ የኢትዮጵያ ጀግና የገበሬ ሠራዊት
ከጠዋቱ አራት ሠዓት ግድም ታላቁን የአድዋ ድል
መቀዳጀቱን አረጋገጠ ፡፡ ብዙ ሺህ የኢጣሊያ ወታደሮች
በጦር ሜዳ ተገደሉ፡፡ ብዙ ሺዎች ደግሞ ቁስለኛና ምርኮ
ሆኑ፡፡ የተቀረውንና ድል ተመትቶ የተበታተነውን የኢጣሊያ
ወታደር እያሣደደና እያባረረ አፍሪቃዊው ኃይል ፈጀው
ብሎ ፅፎአል ጆርጅ በርክሌይ፡፡ ከሚሸሹት መሃከል አንዱ
የአውሮጳዊው ወራሪ ሠራዊት ዋና አዛዥ ጄኔራል ባራቴሪ
ነው፡፡
ይሄ (በአውአሎም ብስለትና ሥልጡንነት መስዋዕትነትና
ኢትዮጵያዊ ፍቅር የተገኘው) ሰለጠነ በሚባለው
የአውሮጳ ኃይል ላይ አልሰለጠነም በሚባለው አፍሪቃዊ
ኃይል የተጨበጠ ትልቅ የወታደራዊ መረጃ (Military
Security intelligence) ብልጫ ወይም ድል ነው፡፡
በወታደራዊ ሣይንስ ደግሞ ወታደራዊ መረጃ ለወታደራዊ
ግጃጅ አፈፃፀም ዋነኛና ወሣኝ ጠቀሜታ አለው፡፡ በዚህች
ዓለም ላይ ከተደረጉ አብዛኞቹ ጦርነቶች ድል ያደረጉት
የወታደራዊ መረጃ ብልጫ የነበራቸውና ፍትህና እውነትን
ፖለቲካዊ መሠረት ያደረጉት ናቸው፡፡ እኛ ሁለቱንም
ነበረን፤ ዓላማችን የአገራችንን ጥቅምና ክብር ህልውናና
ልዕልና ማስከበር ነፃነታችንን ማስጠበቅ ሲሆን፡- ይህም
የፍትህና የእውነት ነፍሥ ነው፡፡ በአገር ወዳዱ ባሻዬ
አውአሎም ሀረጐት አማካይነት ደግሞ በአውሮጳ ላይ
የወታደራዊ መረጃ ብልጫን ተቀዳጀን፡፡ ኢትዮጵያ በረጅም
ዘመን ታሪኳ ከውጪ ወራሪዎች ጋር ባደረገቻቸው
ጦርነቶች ሁሉ፡- እውነትና ፍትህን መሠረት አድርጋለች፡፡
የዲፕሎማሲያዊ ድሉን የተቀዳጀችው ኢትዮጵያ፡- አውሮጳ
ውስጥ ባስቀመጠቻቸው የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ወላጅ
አባት ራስ መኮንንና ግራዝማች ዮሴፍ በተሰኙ
ዲፕሎማቶቿ አማካይነት ነው፡፡ ጣሊያኖች ኢትዮጵያውያን
ያልሰለጠኑ በመሆናቸው በምርኮኞች ላይ ሠብአዊነት
የጐደለው ድርጊት ይፈፅማሉ ብለው ያስወራሉ፡፡
ግራዝማች ዮሴፍ በተለያዩ ቋንቋዎች እየፃፈ ለአውሮጳ
ጋዜጦች ይሄን ያስተባብላሉ፡፡ ከጥቂት ጊዜያት በኋላ
ደግሞ ኢትዮጵያ ልክ ዲፕሎማቶቿ እንዳሉት ምርኮኞችን
ግብር አብልታ አካላቸዉም ምቾታቸውም ሳይጓደል ወደ
አገራቸው ሰደደች፡፡
በዚህም ዲፕሎማሲያዊ ሥልጣኔዋን ለመላው አውሮጳ
እና ለመላው ዓለም በተጨባጭ አሳየች፡፡ ከመቶ ዓመታት
በላይ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላት ብቸኛ አፍሪቃዊት
አገር፡- ኢትዮጵያ ነች፡፡ የአብዛኞቹ የአፍሪቃ አገሮች
ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ረጅም ዕድሜ ከስድሣ ዓመት
አይዘልም፡፡ ኢትዮጵያ፡- ከኢጣሊያና ከፈረንሣይ ከአሜሪካ
(USA) እና ከእንግሊዝ ከሩሢያና ከጀርመን (ከስድስት
አገራት) ጋር ከመቶ ዓመታት ለሚበልጥ ጊዜ
ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን አዳብራ እና አፅንታ ቆይታለች፡፡
በአድዋ ድል፡-
ዋነኛው ድል በጦር ግንባር ፍልሚያ የተገኘው ድል ነው፤
ታላቁ የአድዋ ድል፡፡
የአድዋ ጦርነት(የጥቁሮች የነፃነት ተምሳሌት) የተደረገው
በሁዳዴ ፆም ውስጥ ነው፡፡ ከዚያ በፊት በአፄ ቴዎድሮስ
ዘመነ መንግሥት የተደረገው የመቅደላ ጦርነትም በሁዳዴ
ፆም ውስጥ ነው የተካሄደው፡፡ በአድዋ ጦርነት ፆምና
ውጊያ አብሮ ስለማይሄድ ግብፃዊውን ጳጳስ ሠራዊቱን
ይፍቱትና እንደ ልቡ ይዋጋ ቢባሉም ባለመፍታታቸው
ከኢትዮጵያ የገበሬ ሠራዊት ጿሚ የሆነው እየፆመ
ለመዋጋት ተገዶአል፡፡ በመቅደላ ውጊያ ዓፄ ቴዎድሮስ
[ካሣ ኃይሉ ወልደጊዮርጊስ (አባ ታጠቅ ካሣ) (መዩሣው
ካሣ) (ወሬሣው ካሣ)] ሊወጋቸው ለመጣው
እንግሊዛዊው ጄኔራል ናፒዬርና ሠራዊቱ ፆምህን ፈትተህ
ከእኔ ጋር ውጊያ ግጠም ብለው አንድ ሺህ በጐች
ልከውለታል፡፡
ከአድዋ ጦርነት በፊት ባሉት ጥቂት ወራትና ሣምንታት
መቀሌና አምባላጌ ላይ የተደረጉ ጦርነቶች አሉ፡፡
የመቀሌን ከተማ በኢጣሊያዊው ኮሎኔል ጋሊያኖ
ከሚመራው አውሮጳዊ ሠራዊት ለማስለቀቅ መስዋዕትነቱ
የበዛ በመሆኑ፡- መቀሌ የተለቀቀችው በፈረንጆች
ሚሊኒየም BBC (British Broadcasting
Corporation) የሚሊኒየሙ ምርጥ ሠብዕና ብሎ
ከአህጉር አፍሪቃ ባጫቸው ከጐንደር ኦሮሞ ቤተሠብ
በሚወለዱት እቴጌ ጣይቱ ብጡል ሥልጡን ወታደራዊ
መላ ነው፡፡
ዝርዝሩን እዚህ አላወሣውም እንጂ መቀሌ በጣይቱ ልዩ
ወታደራዊ ብቃት መያዝዋን መግለፅ ይጠቅማል፡፡ በኋላ
ላይ ኮሎኔል ጋሊያኖ በአድዋ ጦርነት ተማርኮ፡-
የምንሊክን ፊት ከማይ ግደሉኝ ብሎአል፡፡ በአምባላጌው
ጦርነት ሊቀ መኳስ አባተ መድፍ ተኩሠው በጣሊያን
መድፍ አፍ ውስጥ እስከ መክተት የዘለቀ
አነጣጣሪነታቸውን አሣይተዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት
ሥልጣናት፡- ማዕከል ወሎ ውጫሌ በነበረበት ሁናቴ፤
ዳግማዊ ዓፄ ምኒሊክ (አባ ዳኘው) ለህዝባቸው የክተት
ጥሪ ካደረጉ በኋላ ከዳር እስከ ዳር የተንቀሣቀሠው
የተቆጣ ኢትዮጵያዊ ሠራዊት ሢተም፤ ሲገባኝ ከሠሜን
ኢትዮጵያ ከጐንደር ከጐጃም ከወሎና ከትግራይ …
የተንቀሳቀሰው አትንኩኝ ያለ ኢትዮጵያዊ ጀግና
ከሚተምመው ሠራዊት የተገናኘው በትውልድ
አቅራቢያው ሆኖ ነው፡፡
መጓጓዣ በሌለበት ዘመን የሠሜኑን የኢትዮጵያ ጀግና
የገበሬ ሠራዊት ወደ ሰሜን ለማዝመት ሲባል በመሀል
አገር ማሰባሰብ የሚያስፈልግበት ሁኔታ አልነበረም፡፡

Thursday, February 11, 2021

፩•እውነትን በደጋፊ ብዛት እንዳትመዝናት ተጠንቀቅ ።
፪•ለእውነታ እንጂ ለይሉኝታ አትኑር ፤ ያንስልህ የምትኖርበት ሕዝብናባሕል
ከእውነት ጋር እስካልተጋጨ መጋፋት
የለብህም። ሠዎች የሚቀበሉህ
ባሕላቸውን ስታውቅና ስታከብርላቸው ነው 
፫•ልጅነት የለሰለሰ መሬት ፣ ወጣትነት የአዝመራ ዘመን ፣ ሽምግልና ደግሞ የአጨዳ ዘመን መሆኑን አስተውል ።
በሽምግልናህ የምታጭደው የወጣትነትህን አዝመራ ነውና ዛሬ ለምትዘራው ተጠንቀቅ ።
፬•የሰዎችን ያለማወቅ አግዝ ፤ ዕውቀትህ ባላወቁት ላይ እንድትኮራና እንድትፈርድ
አያድርግህ የአዋቂ ኩሩ ቁጥሩ ካላዋቂዎች ነውና ማወቅ ባለዕዳነት እንዳይሆን አላዋቂዎችን እርዳቸው 
፭•ሁሉን ወሬ ላውራ አትበል ፣ የደበቁህን ምስጢር አታውጣጣ ፣ የሰማኽውን ወሬና የተገለጠልህን ምስጢር ምን መፍትሔ ሰጠኸውና  ያየህውን ሥራ ሁሉ እሰራለሁ የሰማኸውን ትምህርት ሁሉ እማራለሁ አትበል ። ይህ የተሰወረው የቅንዓት ጠባይ ነውና ሁሉን ልያዝ ማለትም ዝንጉ አድረጎ እንዳያስቀርህ ሁሉም ውስጥ ልኑር አትበል ።
፮•ቆንጆዎች ቁንጅናቸው ሁሉን የሚተካ እየመሰላቸው ከዕውቀትና ከትሕትና ይርቃሉ ። ሁሉንም ሰው በመልካቸው የሚማርኩት ስለሚመስላቸው ኩሩና ተንኮለኞች ይሆናሉ ። አንተ ግን ቆንጆ ወዳጅን እንጂ ቆንጆ ቁመናን አትሻ ፤ቆንጆ ትዳርን እንጂ ቆንጆ ሴትን አትመኝ ፤የላይ ነገር ከንቱና ኀላፊ ነውናበሚፈርስ አካል ፣ ኑሮ በሚለውጠው መልክ አትደለል ።
፯•እወድሃለሁ ብለህ የምትናገረውን ቃል ውለታ አታድርገው ፣ መውደድህን የምትናገረው እንወድሃለን እንዲሉህ አይሁን ሠላም ያለው አፍቃሪ የራሱን
ፍቅር ያለ ምክንያት መፈፀም የሚችል ብቻ እንደሆነ እወቅ ። መወደድህን ለመስማት አትጠብቅ 
፰•የሰዎችን ያለማወቅ አግዝ ፤ ዕውቀትህ ባላወቁት ላይ እንድትኮራና እንድትፈርድ አያድርግህ የአዋቂ ኩሩ ቁጥሩ ካላዋቂዎች ነውና ማወቅ ባለዕዳነት እንዳይሆን አላዋቂዎችን እርዳቸው 
፱•ዛሬ የመዝራት ዘመንህ ነገ መከርህ ነውና በእምነት እውነትን ዝራ በምታውቀው ቦታ ላይ አገልጋይ
በማታውቀው መልካም ተግባር ላይ ደጀን ሁን ፤
፲•በቦታህ መምህር ያለቦታህ ተማሪ
ሁን ፤ ክብሩ እንዳይቀንስብህ ከዕቃ
ትምክህት ፣ ከዕውቀት ሙግት ራቅ!
ሲያለቅሱልህም ቃልህ ማርኳቸው
ሳይሆን የሞተ ዘመዳቸው ትዝ
ብሏቸው ሊሆን ይችላልና አለቀሱ ብለህ ንግግርህን ድንበር አታሳጣው