<$ambachewmulat5.blogspot.com$> <$pub-7470502258870845$>

Wednesday, February 17, 2021

አፄ ቴዎድሮስ

አፄ ቴዎድሮስ
(ከታሪክ ማኅደር)
፨፨፨
ከ201 ዓመት በፊት ጥር 6 ቀን 1811 ዓ/ም በጎንደር-ቋራ
ተወለዱ ፡፡ በፈረስ ስማቸው አባ ታጠቅ ፤ በትውልድ
ስማቸው ካሳ ሀይሉ ፤ በውትድርና ስማቸው ደግሞ
መይሳው ካሳ ሲባሉ የዙፋን ስማቸው ደግሞ ዳግማዊ
ቴዎድሮስ ይባላል ፡፡
በትውፊት እንደሚነገረው በ15 ኛው መቶ ክፍለዘመን
ቀዳማዊ ቴዎድሮስ የተባለ ተወዳጅ ኢትዮጵያዊ ንጉስ ነበር
ይባላል፡፡ ይህ ንጉስ በ19 ኛው መቶ ክፍለዘመን ዳግም
ይመጣል ተብሎ በተነገረው ትንቢት መሠረት ካሳ ሀይሉ
ራሳቸውን ዳግማዊ ቴዎድሮስ ንጉሰ ነገስት ዘ ኢትዮጵያ
ብለው የካቲት 11/1847 ዘውድ ደፉ፡፡ ቴዎድሮስ የሚለው
ስያሜ "ጣዎስ ድሮስ" ከሚል የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን
ትርጉሙም የአምላክ ስጦታ ማለት ነው፡፡
አጼ ቴዎድሮስ፣ ይህ "የአገሪቱን የታሪክ አቅጣጫ
የሚቀይር" የሚመጣው ንጉስ ነኝ ብለው ያምኑ እንደነበር
ለማመን አይከብድም ። በስርዓተ ንግሳቸው ላይ ባደርጉት
ንግግር አገሪቷን አንድ ለማድረግና እንደገና ለመገንባት
ያላቸውን ከፍተኛ ፍላጎት ገልጸዋል። የቴወድሮስን የህይወት
ታሪክ የጻፈው ስቬን ሩቤንሰን አፄ ቴወድሮስ ስልጣን ላይ
ሲወጡ በአይምሮአቸው ውስጥ የነበረውን ዕቅድ እንዲህ
ሲል ይዘግባል ።
"የቴዎድሮስ ስሜት እንደቀደሙት ነገስታት ሳይሆን የተለየ
ነበር ፤ ለእርሱ የባላባቶች ትርምስ ፣ የግብረገብ መላሸቅ ፣
የቴክኖሎጂ ኋላቀርነት የአገሪቱን መኖር ጥያቄ ውስጥ
የጣሉ ጉዳዮች ነበሩ። ያወጃቸው ለውጦች፣ የተከተላቸውና
ሊተገብራቸው የፈለጋቸው ፖሊሲወች፣ እያንዳንዱን ችግር
ለመፍታት ያሳየው እልከኝነት ፣ የሚያሳዩት የንጉሱ አላማ
ብሔራዊ ተሃድሶና አገሪቱን ወደ ዘመናዊ አገር ማሻገር
እንደነበር ነው" ይላል ።

አፄ ቴዎድሮስ የንግስና ጊዜያቸው የባሪያ ንግድን ፣
ጎጠኝነትን ፣ ከወገብ በላይ ተራቁቶ በብዛት ባህልን. ..
ወዘተ አስቀርተዋል ፡፡ ዘመናዊ ኢትዮጵያን ለመፍጠር ጥረት
ያደረጉት ቴዎድሮስ የወቅቱን ዘመናዊ ጦር ፣ ዘመናዊ
የመከላከያ ምሽግ እና ዘመናዊ ሙዚየም አቋቁመዋል፡፡
ከውትድርናው ውጪ መፅሀፍ ቅዱስን በአማርኛ በብዛት
እንዲተረጎም ከማድረግ ባለፈ ስነፁሁፍ እና ፍልስፍና
እንዲያድግ የቻሉትን ያህል ጥረዋል ፡፡ የመንገድ ዝርጋታ
በማስጀመርም ሆነ ብሔራዊ ፍቅርን በመስበክ ለዘመናዊ
የኢትዮጵያ ታሪክ የአንድነት መነሻ ሆነዋል (ፓውል
ሄንዝ ) .።
አፄ ቴዎድሮስ የዘመናዊ ስልጣኔን በር ከፋች ሲሆኑ
"እንደገና አንድ የሆነችና ጠንካራ ኢትዮጵያም" ምልክት
ናቸው ። የአገሪቱን ፖለቲካዊና ሃይማኖታዊ አንድነት
ለመመለስ ታላቁ ምኞታቸው ነበር ፣ ያገሪቱን ጥንታዊ
ድንበርም ለማስመለስ እንዲሁ ። የቴዎድሮስ መነሳት
የዘመናዊ ኢትዮጵያ ታሪክ መጀመሪያ ነው ። ለዚህም
ምክንያቱ ደግሞ የፈጸሟቸው ለውጦች ናቸው ።

አጼ ቴዎድሮስ ብዙ የጓጉለትን ለውጥ ማምጣት ሳይችሉ
ከውስጥና ከውጭ በተቀሰቀሰባቸው ተቃውሞ ምክኒያት
የእንግሊዝ ወራሪ ጦርን ተፋልመው በሚያዝያ ወር 1860
ዓ.ም መቅደላ አምባ ላይ ለሀገራቸው መስዋዕት የሆኑ
ታላቅ ንጉስ ነበሩ ፡፡
በፈረስ ስማቸው ከተገጠመላቸው ግጥሞች፦
ታጠቅ ብሎ ፈረስ ካሣ ብሎ ስም ፤
ዓርብ ዓርብ ይሸበራል ኢየሩሳሌም ።
አባ ታጠቅ ካሳ ነገር ሲያሰላስል ፤
ባህሩን ያስባል መረብ ጣይ ይመስል ።
ትልቅ ነበርን ትልቅም እንሆናለን
፨ ዛሬ የጀግናው 201ኛ ዓመት ነው...እንኳን ተወለዱልን
ጊዜውን የቀደሙ እንቁ መሪ ነበሩና

ያድራል በየቦታው ለነብሱም አይሳሳ
ብለው ይሻለኛል አንድ አርጋቸው ካሳ
አንድ ቀን ሳይደላው ሁሌ እንደዋተተ
ለአገሩ ተፈጥሮ ለአገሩ የሞተ
(ትዕግስት አፈወርቅ_አልረሳ አለኝ...ከሚለው ሙዚቃ)
ዋቢ መጽሐፍት ፦
1. ጳውሎስ ኞኞ (አፄ ቴዎድሮስ)
2. ባህሩ ዘውዴ

2 Comments:

At March 4, 2021 at 7:33 PM , Blogger Ambachew said...

አፄ_ቴድሮስ

 
At March 4, 2021 at 7:35 PM , Blogger Ambachew said...

አፄ_ቴድሮስ

 

Post a Comment

Subscribe to Post Comments [Atom]

<< Home