አፄ_ቴድሮስ
አፄ_ቴድሮስ
የአፄ ቴዎድሮስ ታሪክ በአጭሩ፡-
አፄ ቴዎድሮስ ጥር 6/ 1811 ዓም በጎንደር- ቋራ ተወለዱ። አባታቸው ደጃዝማች ሀይለ ጊወርጊስ በሡዳኖች በ1813 ዓ.ም ስለተገደሉ፣ እናታቸው አትጠገብ ወንድ ወሠን ከቋራ በመሸሽ ወደ ጎንደር ከተማው በሁለት አመታቸው ይዛቸው መጠች። ወይዘሮ አትጠገብ የጎንደር ከተማ መስራች የአፄ ፋሲለደስ ዘመድ ናቸው። አፄ ቴወድሮስ በናታቸው በኩል ምንም ወንድም እህት አልነበራቸውም። እናታቸው ባለቤታቸው እንደሞተ ወዲያው ቆርበው ስለነበር ከቴዲ ውጭ ልጅ አልወለዱም። ለዚህም ቴወድሮስ አንድ ለናቱ ይባላል።
አፄ ቴወድሮስ በፈረስ ስማቸው አባ ታጠቅ ፣
በትውልድ ስማቸው ካሳ ሀይሉ፣ በውትድርና ስማቸው ደግሞ መይሳው ካሳ ሲባሉ የዙፋን ስማቸው ዳግማዊ ቴወድሮስ ነው።
ቀዳማዊ ቴወድሮስ በፍካሬ እየሡስ፣ በ 15ኛው መቶ ክፈለ ዘመን የነበረ ተወዳጅ ንጉስ ነው። ይህ ንጉስ በ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ዳግም እንደሚነሳ ትንቢት ተነግሯል።
ይሄን ትንቢት በመያዝ ካሳ ሀይሉ እራሡን ዳግማዊ ቴወድሮስ ንጉሠ ነገስት ዘኢትዮጵያ ብሎ የካቲት 11/ 1847 ሾመ። ቴወድሮስ ጣዎስ ድሮስ ከሚል የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን የአምላክ ስጦታ ማለት ነው። ምን አልባት መፅሃፍ ቅዱስን በደንብ ስላነበበ የቴወድሮስ ሹርባ ምንጩ መፅሃፍ ቅዱስ ሊሆን ይችላል። በመፅሃፍ ቅዱስ በሹርባው ሀይልን የታደለ ሳምሶን የሚባል ሠው ነበርና።
በእርግጥ በቴወድሮስ ዘመን ፀጉር ማሳደግ የጀግንነት ምልክት ነው። አፄ ቴወድሮስ አራት ግዜ አግብተው 6 ወንድ 3 ሴቶችን ልጆች ወልደዋል። እራስ እንግዳ ፣ ራስ መሸሻ፣ ሀይለ ማርያም፣ አልጣሽ (የሚኒልክ
የመጀመሪያ ሚስት) ፣ ልዑል አለማየሁ ቴወድሮስ ወዘተ) ብዙዎች በመቅደላ ጦርነት ተገለዋል። ስልጣነ መንግስቱን ልዑል አለማየሁ እንዲረከብ ይፈልጉ ነበር
ሪቻሪድ ፓንከረስት። አፄ ቴወድሮስ ሩሲያና እንግሊዝ ግብፆችና ቱርኮችን ከሀገር ለማስወጣት እንዲረዷቸው ደብዳቤ ቢፅፉም ምላሽ አጡ። እንግሊዝ ከቱርክ ጋር እሩሲያ በክሪምያ ጦርነት ወገቻት። አፄ ቴወድሮስም እልህ ተጋብተው እንግሊዛውያንን አስረው ሴባስቶፓል መድፍን አሠሩና ስያሜውን
ለሩሲያ የጦር ሜዳ ሠጡ። አፄ ቴወድሮስ በ13 አመት የንግስና ግዚያቸውን የባሪያ ንግድን፣ ጎጠኝነትን፣ ከወገብ በላይ ያለ መልበስ ባህልን፣ ወዘተ አስቀርተዋል።
ዘመናዊ አትዮጵያን ለመፍጠር ሙከራ አድርገዋል። ዘመናዊ ጦር፣ ዘመናዊ
ምሽግ፣ ዘመናዊ፣ ሙዚየም አቋቁመዋል።
መፅሃፍ ቅዱስን በብዛት በአማረኛ እንዲተረጎም ከማድረግ ባለፋ ፣ስነ ፁህፍ
፣ፍልስፍና እንዲያድግ ጥረዋል። የመንገድ ዝርጋታ አስጀምረዋል። ብሄራዊነትን ሠብከዋል። የዘመናዊ የኢትዮጵያ
ታሪክ የአንድነት መነሻ ናቸው ፓውል ሄንዝ።
ሚያዝያ ወር መግቢያ በእለተ አርብ ፣ ፋሲካን ሳይገድፉ በስቅለቱ በ 1860 ዓ.ም እራሳቸውን መቅደላ አፋፋ ላይ ለሀገራቸው ገደሉ።
መቅደላ ካፋፉ ጩኸት በረከተ የሴቱን አናውቅም ወንድ አንድ ሰው ሞተ>>።
በወቅቱ እንግሊዛውያን ወደ መቅደላ ሲመጡ 6 ሚሊዮን ፓውንድ መድበው፣ 32
ሺ ዘመናዊ ወታደር ይዘው እንደመጡ ታሪክ ይዘግባል። በምናብ ተወልዶ በምናብ የሞተ!!!! በትንሽ ዘመን ትልቅ የሆነ ፣ ከመለያየት አንድነት የሠበከ ፣ የአንድነት ሀዋሪያ (ተጓዥ ) ንጉስ ዳግማዊ ቴወድሮስ በዚች ምድር ላይ የኖሩ ለ 49 አመታት ብቻ ነበር። ዳሩ ቁም ነገር በእድሜ አይሠፈርም። በገነነ ስራቸው ከዘመናቸው በላይ አስበው ከእድሚያቸው በላይ ኖሩ። ዛሬም ነገም ክብር ለመቅደላው ሞት ደፋሪ!!! ምስጋና ለጋፋቱ የቴክኖሎጅ ጥመኛ!

Labels: ታሪክ