ሽሬ
#ቆይቶ እንደሚገባኝ #የገባኝ #ራሱ ቆይቶ ነው
ካለፈ ወዲያ ጤዛው ከደረቀ፣በኔ ምሽት ላይ ንጋት ከተንሰራፋ፣ወፎች ከዘመሩ፣ ፀሐይ ከተጋጋለች ወዲያ የጨለማ ሚስጥር ቢገለጥልኝ ምን ፋይዳ አለው።
ያለፉትን አዳጋች ጊዜ ባለበሌለ አቅም ሲታገሉ
በትግል ላይ እያሉ ያጠትን ሲያስታውሱ እንደሚቆጭ፣የፊት ላይ ጠባሳ ለመሽቀርቀር ሲያስቡ እንደሚታወስ የገባኝ እኔ ከጨለማ ሳልወጣ ለምድሩ ከነጋ በኋላ ነው!
ሕይወት ጨዋታ እንደሆነችና ተሸናፊ ሌላ ዕድል እንደማያገኝ የገባኝ ዘግይቶ ነው፣ሞትን የመሰለ እረፍት እንደማይገኝ የገባኝ ቆይቶ ነው።
አግኝቼሽ እንደማላውቅ ያጣሁሽ ቀን ነው፤ የገባኝ ባንቺ ተመርኩዤ ያለኝን ሁሉ እንደጠላሁ የጠላሁትንም ሁሉ ባንቺ እንደተካሁ፣ ጊዜዬንና ጊዜሽን ከማምከን ውጪ ምንም እንዳላተረፍኩ የገባኝ ዘግይቶ ነው።
ቀን ሲጥል ሁሉም ፈራጅ እንደሚሆን፣ጊዜን
ተከትሎ ከወዳቂ ሰው ሕይወት ውስጥ ሁሉም
እንደሚወጣ የተገለጠልኝ ቆይቶ ነው።"ሁሉም
አለኝ" ከማለት "ባይተዋር ነኝ!" ለማለት ቅጽበት እንደማይፈጅ የገባኝ ቆይቶ ነው።
ጥሩ ወዳጅ ታማኝ ጠላት እንደሚሆን፣
ያስለመዱት ውሻ ሲራብ ባለቤቱን እንደሚነክስ ቀኑ የከፋ ዕለት መርዶ ነጋሪ ለቀባሪው እንደሚያረዳ ያወቅኩት ቆይቼ ነው!
ሰው መለያየትን ሲፈልግ ምክንያት እንደማያጣ በመንገድህ ካልተሳካልህ በመንገዳቸው እንደማያራምዱህ የገባኝ ከረፈደ በ ኋላ ነው።
ላንተ ካንተ ሌላ ማንም እንደሌለህ ሳትዘግይ
ተረዳ።ስትወድቅ ተራምደውብህ ቢያልፉ እንጂ
ማንም ላንተ ሲል ማንም እንደማይወድቅ
ከወፎች ዝማሬ ቀድመህ ዕወቅ።
አጎንብሶ የሚያነሳህም የራስህ እጅ ብቻ መሆኑን
ሳይረፍድ ይግባህ!
You Are Not Poor Because You Don't Have Money.
You Are Poor If You Don't Have A Dream.
0 Comments:
Post a Comment
Subscribe to Post Comments [Atom]
<< Home